-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
16. ሉቃስ 21:24 በኢየሱስ ትንቢት ላይ ምን ይጨምራል? ይህስ ምን ትርጉም አለው?
16 ማቴዎስ 24:15–28ንና ማርቆስ 13:14–23ን ከሉቃስ 21:20–24 ጋር እያወዳደርን ብንመለከት የኢየሱስ ትንቢት ከኢየሩሳሌም ጥፋት በኋላ ብዙ ቆይቶ የሚፈጸሙ ሁኔታዎችን የሚጨምር መሆኑን የሚያመለክት ሁለተኛ ምክንያት እናገኛለን። ስለ ቸነፈር የጠቀሰው ሉቃስ ብቻ እንደነበረ ሁሉ ይህን የኢየሱስ ትንቢት ክፍል “የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም [የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት እስኪያበቁ አዓት] ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች” በሚሉት ቃላት የደመደመው ሉቃስ ብቻ ነው።e (ሉቃስ 21:24) ባቢሎናውያን የመጨረሻውን የአይሁድ ንጉሥ ከሥልጣን ያስወገዱት በ607 ከዘአበ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የአምላክን መንግሥት የምትወክለው ኢየሩሳሌም እንደተረገጠች ቆይታ ነበር። (2 ነገሥት 25:1–26፤ 1 ዜና መዋዕል 29:23፤ ሕዝቅኤል 21:25–27) ኢየሱስ በሉቃስ 21:24 ላይ ይህ ሁኔታ አምላክ መንግሥቱን እንደገና እስከሚያቋቁምበት ጊዜ ድረስ እንደሚቀጥል አመልክቷል።
-
-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
e ብዙዎች የሉቃስ ዘገባ ከሉቃስ 21:24 ጀምሮ ሌላ ዓይነት ሐሳብ ይገልጻል ይላሉ። ዶክተር ሊየን ሞሪስ እንዲህ ሲሉ አስገንዝበዋል፦ “ኢየሱስ በመቀጠል ስለ አሕዛብ ዘመን ይናገራል። . . . እንደ አብዛኞቹ ምሑራን አስተያየት ከዚህ በኋላ የኢየሱስ ትንቢት የሚያተኩረው የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ ላይ ነው።” ፕሮፌሰር አር ጊንስ “የሰው ልጅ መምጣት (ማቴ 24:29–31፤ ማር 13:24–27)” በሚለው ንዑስ ርዕሳቸው ሥር እንዲህ ብለው ጽፈዋል፦ “‘የአሕዛብ ዘመን’ የሚለው አባባል መጠቀሱ ለዚህ አዲስ ርዕስ መግቢያ ሆኖ ያገለግላል። [ሉቃስ] የትኩረት አቅጣጫውን በመቀየር ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት መናገር ያቆምና ወደፊት ስለሚመጣው ዘመን ይገልጻል።”
f ፕሮፌሰር ዎልተር ኤል ሌይፌልድ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፦ “የኢየሱስ ትንቢት ሁለት ክፍል አለው ብሎ ማሰብ ይቻላል። እነሱም፦ (1) በቤተ መቅደሱ ላይ የደረሱትን ጨምሮ በ70 ዓ. ም. የተፈጸሙት ነገሮችና (2) ወደፊት ከረዥም ጊዜ በኋላ የሚፈጸሙትና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት አነጋገሮች ጋር ተመሳሳይ በሆኑ ቃላት የተናገራቸው ነገሮች ናቸው።” በጄ አር ደሜሎ የተዘጋጀው ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦ “ጌታችን የተናገረው ስለ አንድ ነገር ሳይሆን ስለ ሁለት ነገሮች እንደሆነና የመጀመሪያው ለሁለተኛው ጥላ እንደሚሆንለት ከተገነዘብን ይህንን ታላቅ ንግግሩን ለመረዳት አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ አብዛኞቹ ይወገዳሉ። . . . በተለይ ‘ስለ አሕዛብ ዘመን’ የሚናገረው [ሉቃስ] 21:24 . . . ኢየሩሳሌም ከጠፋችበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ባለው ጊዜ መሐል ረዥም ዘመን እንዳለ በግልጽ ያሳያል።”
-