የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የክርስቶስን ፍቅር ማወቅ’
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • “አባት ሆይ፣ . . . ይቅር በላቸው”

      16. ኢየሱስ ተሰቅሎ እያለም እንኳ ይቅር ባይ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

      16 ኢየሱስ ‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ በመሆንም የአባቱን ፍቅር ፍጹም በሆነ ሁኔታ አንጸባርቋል። (መዝሙር 86:5) ተሰቅሎ እያለም እንኳ ይቅር ባይ መሆኑን አሳይቷል። እጆቹና እግሮቹ በሚስማር ተቸንክረው ክብርን በሚነካ ሁኔታ እንዲሞት በተደረገበት ወቅት የተናገረው ቃል ምን ነበር? ይሖዋ፣ የሰቀሉትን ሰዎች እንዲቀስፍለት ተማጽኗል? በፍጹም፤ እንዲያውም “አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው” ሲል አባቱን ለምኗል።—ሉቃስ 23:34b

  • ‘የክርስቶስን ፍቅር ማወቅ’
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • b የሉቃስ 23:34 የመጀመሪያ ክፍል በአንዳንድ የጥንት ቅጂዎች ላይ አይገኝም። ሆኖም ተአማኒነት ባላቸው በሌሎች ብዙ ቅጂዎች ላይ ስለሚገኝ በአዲስ ዓለም ትርጉም እና በሌሎች በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ ተካትቷል። እዚህ ላይ ኢየሱስ ስለሰቀሉት የሮም ወታደሮች እየተናገረ ሳይሆን አይቀርም። ስለ ኢየሱስ ትክክለኛ ማንነት የሚያውቁት ነገር ስላልነበረ የሚያደርጉትን አያውቁም ሊባሉ ይችላሉ። በተጨማሪም እንዲገደል የጠየቁትን በኋላ ግን በእሱ ያመኑትን አይሁዳውያን አስቦም ሊሆን ይችላል። (የሐዋርያት ሥራ 2:36-38) እርግጥ ነው፣ ሞት እንዲፈረድበት ያደረጉት የሃይማኖት መሪዎች ይህን ተግባር የፈጸሙት የኢየሱስን ማንነት አውቀውና በክፋት ተነሳስተው በመሆኑ በምንም ዓይነት ከተጠያቂነት ነፃ ሊሆኑ አይችሉም። ከእነሱ መካከል አብዛኞቹ ይቅር ሊባሉ አይችሉም።—ዮሐንስ 11:45-53

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ