የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢየሱስ 70 ደቀ መዛሙርት ላከ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | መጋቢት 1
    • ወቅቱ 32 እዘአ የፀደይ ወራት ነበር። ኢየሱስ ሊገደል የቀረው ስድስት ወር ብቻ ነበር። ስለዚህ የስብከቱን ሥራ ለማፋጠንና ለአንዳንድ ተከታዮቹ ተጨማሪ ስልጠና ለመስጠት ኢየሱስ 70 ደቀ መዛሙርት መረጠና “ሁለት ሁለትም አድርጎ እርሱ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና ስፍራ ሁሉ በፊቱ ላካቸው።”​—⁠ሉቃስ 10:​1a

      ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ‘በፊቱ የላካቸው’ በኋላ እርሱ ራሱ ወደዚያ በሚሄድበት ጊዜ ሰዎቹ መሲሑን መደገፋቸውን ወይም መቃወማቸውን በተመለከተ በፍጥነት እንዲወስኑ ለማስቻል ነው። ሆኖም “ሁለት ሁለት” አድርጎ የላካቸው ለምንድን ነው? ተቃውሞ በሚያጋጥማቸው ጊዜ አንዱ ለሌላው የብርታት ምንጭ መሆን እንዲችሉ እንደሆነ ግልጽ ነው።

  • ኢየሱስ 70 ደቀ መዛሙርት ላከ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | መጋቢት 1
    • አብዛኛውን ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲያገለግሉ ይታያሉ። እያንዳንዳቸው ለየብቻቸው ሆነው ቢያገለግሉ ኖሮ የበለጠ ማከናወን አይቻልም ነበር? ምናልባት ይቻል ይሆናል። የሆነ ሆኖ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ከእምነት ጓደኞቻቸው ጋር ጎን ለጎን ሆነው የማገልገላቸውን ጥቅም ይገነዘባሉ። እንዲህ ማድረጋቸው አደገኛ በሆኑ አካባቢዎች በሚመሰክሩበት ጊዜ ጥበቃ ያስገኝላቸዋል። ከአገልግሎት ጓደኛ ጋር ሆኖ ማገልገል ይበልጥ ተሞክሮ ያላቸው የምሥራቹ አስፋፊዎች ካካበቱት ችሎታ አዳዲሶች ጥቅም እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። በእርግጥ አንዳቸው ለሌላው የማበረታቻ ምንጭ መሆን ይችላሉ።​—⁠ምሳሌ 27:​17

  • ኢየሱስ 70 ደቀ መዛሙርት ላከ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | መጋቢት 1
    • a አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችና ጥንታዊ የግሪክኛ ጽሑፎች ኢየሱስ “ሰባ ሁለት” ደቀ መዛሙርት እንደላከ ይናገራሉ። ሆኖም “ሰባ” ልኳል ብሎ ለመናገር የሚያበቃ በርካታ የብራና ጽሑፎች ማስረጃ አለ። ይህ ልዩነት ከዋናው ቁምነገር ማለትም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹን ለስብከት መላኩን ከሚናገረው ትኩረታችንን ሊያዞር አይገባም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ