የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ሂዱና . . . ደቀ መዛሙርት አድርጉ”
    “ተከታዬ ሁን”
    • 12 በተጨማሪም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ትኩረታቸውን የሚከፋፍሉ አላስፈላጊ ነገሮችን እንዲያስወግዱ አስተምሯቸዋል። “በመንገድም ላይ ቆማችሁ ከማንም ጋር ሰላምታ አትለዋወጡ” ብሏቸዋል። (ሉቃስ 10:4) ኢየሱስ እንዲህ ሲል ሰዎችን አይተው እንዳላዩ ሆነው እንዲያልፉ መናገሩ ነበር? በፍጹም። በዘመኑ የነበረው ሰላምታ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ ነገር ነበር። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዲህ ብለዋል፦ “በምሥራቁ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሰላምታ የሚለዋወጡት እኛ እንደምናደርገው በትንሹ አንገት ሰበር በማድረግ ወይም በመጨባበጥ አልነበረም፤ ሰላምታቸው ደጋግሞ መተቃቀፍንና ጎንበስ ቀና ማለትን እንዲሁም መሬት ላይ ተደፍቶ መስገድን ይጨምር ነበር። ይህ ሁሉ ረጅም ጊዜ ይወስዳል።” ታዲያ ኢየሱስ የተለመደውን ዓይነት ሰላምታ እንዳይሰጡ ለደቀ መዛሙርቱ ሲነግራቸው ምን ማለቱ ነበር? “የያዛችሁት መልእክት እጅግ አጣዳፊ ስለሆነ ጊዜያችሁን በአግባቡ ልትጠቀሙበት ይገባል” ማለቱ ነበር።b

  • “ሂዱና . . . ደቀ መዛሙርት አድርጉ”
    “ተከታዬ ሁን”
    • b ነቢዩ ኤልሳዕ በአንድ ወቅት ተመሳሳይ መመሪያ ሰጥቷል። አገልጋዩን ግያዝን ልጇ ወደሞተባት ሴት ቤት በላከው ጊዜ “መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል” ብሎት ነበር። (2 ነገሥት 4:​29) ተልእኮው አጣዳፊ ስለነበር አላስፈላጊ በሆነ ነገር መዘግየት አልነበረበትም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ