-
አንድ ሳምራዊ መልካም ባልንጀራ ሆኖ ተገኘመጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 1
-
-
ኢየሱስ ምሳሌውን በመቀጠል “አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ” አለ። ስለ አንድ ሳምራዊ መጠቀሱ የሕግ አዋቂው ጉጉት እንዲጨምር ሳያደርግ እንደማይቀር እሙን ነው። ኢየሱስ ስለዚህ ዘር ተስፋፍቶ የነበረውን አሉታዊ አመለካከት መደገፉን ይገልጽ ይሆን? ከዚህ በተቃራኒ ሳምራዊው አደጋ የደረሰበትን መንገደኛ ሲመለከት “አዘነለት።” ኢየሱስ እንዲህ አለ:- “ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቊስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፣ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።b በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና:- ጠብቀው፣ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ አለው።”—ሉቃስ 10:33-35
-