የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቲያን ሴቶችን ደግፏቸው
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | መስከረም
    • ኢየሱስ ቁጭ ብሎ ሲያስተምር። ማርታና ማርያም እግሩ ሥር ተቀምጠው ሲያዳምጡ። ፎቶግራፎች፦ 1. አንድ ባልና ሚስት አቅመ ደካማ የሆኑ አረጋዊት እህትን ቤታቸው ሄደው ሲጠይቋቸው። ሚስትየው የገዛቻቸውን ምግቦች ስታስቀምጥ ባልየው እህትን እያዋራቸው ነው። 2. አንድ ባልና ሚስት ከአንዲት እህትና ከልጇ ጋር የቤተሰብ ጥናት ሲያደርጉ። 3. አንድ ወንድም ለሁለት እህቶች የመኪናቸውን ጎማ ሲቀይርላቸው።

      እንደ ኢየሱስ ሁሉ እኛም ለታማኝ እህቶቻችን ፍቅርና አሳቢነት እናሳይ (ከአንቀጽ 6-9⁠ን ተመልከት)e

      6. በሉቃስ 10:38-42 ላይ እንደተጠቀሰው ኢየሱስ ማርያምንና ማርታን የረዳቸው እንዴት ነው?

      6 ኢየሱስ ከመንፈሳዊ እህቶቹ ጋር ጊዜ ያሳልፍ ነበር፤ እውነተኛ ወዳጅም ሆኖላቸዋል። ከማርያምና ከማርታ ጋር የነበረውን ወዳጅነት እንደ ምሳሌ እንመልከት፤ ሁለቱም ነጠላ የነበሩ ይመስላል። (ሉቃስ 10:38-42⁠ን አንብብ።) ኢየሱስ በንግግሩም ሆነ በድርጊቱ ነፃነት ተሰምቷቸው እንዲቀርቡት አድርጓቸው መሆን አለበት። ማርያም አንድ ደቀ መዝሙር እንደሚያደርገው ሳትፈራ እግሩ ሥር ተቀምጣለች።c ማርታም ብትሆን ማርያም ስላላገዘቻት በተበሳጨችበት ወቅት፣ ስሜቷን ለኢየሱስ በነፃነት ነግራዋለች። በዚህ ግብዣ ላይ ኢየሱስ ሁለቱንም ሴቶች በመንፈሳዊ ለመርዳት አጋጣሚውን ተጠቅሞበታል። በተጨማሪም እነዚህን ሴቶችም ሆነ ወንድማቸውን አልዓዛርን በሌሎች አጋጣሚዎችም ሄዶ በመጠየቅ እንደሚያስብላቸው አሳይቷል። (ዮሐ. 12:1-3) አልዓዛር በጠና በታመመበት ወቅት ማርያምና ማርታ የኢየሱስን እርዳታ ለመጠየቅ ያልተሳቀቁት ለዚህ ነው።—ዮሐ. 11:3, 5

  • ክርስቲያን ሴቶችን ደግፏቸው
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | መስከረም
    • c አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “ደቀ መዛሙርት በአስተማሪዎቻቸው እግር ሥር ይቀመጡ ነበር። እነዚህ ሰዎች በቁም ነገር ትምህርታቸውን የሚከታተሉት አስተማሪ ለመሆን ነበር፤ ይህ ደግሞ ለሴቶች የሚፈቀድ ነገር አልነበረም። . . . ማርያም በባሕሉ ከሴቶች የሚጠበቀውን ድርሻ . . . ከመወጣት ይልቅ ኢየሱስ እግር ሥር መቀመጧና ከእሱ ለመማር የነበራት ጉጉት አብዛኞቹን አይሁዳውያን ወንዶች የሚያስደነግጥ ነበር።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ