-
“አምላክ ተብለው የሚጠሩ አማልክት”ንቁ!—2005 | ሐምሌ 8
-
-
ይሁንና አንድ ሰው ‘ኢየሱስ “ኀያል አምላክ” ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ሐዋርያው ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ አልተናገረም?’ የሚል ጥያቄ ሊያነሳ ይችላል። ዮሐንስ 1:1 “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” ይላል። አንዳንዶች በምድር ላይ ሕፃን ሆኖ ተወልዶ ኢየሱስ የተባለው “ቃል” ራሱ ሁሉን የሚችለው አምላክ ነው ብለው ይከራከራሉ። ይህ አባባላቸው እውነት ነው?
“ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” የሚለው ሐሳብ ኢየሱስ ራሱ ሁሉን የሚችለው አምላክ እንደሆነ ያሳያል ከተባለ “ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ” ከሚለው ቀደም ሲል ካለው ሐሳብ ጋር ይጋጫል። ከአንድ ሰው “ጋር” ያለ ግለሰብ ያንኑ ሰው ሊሆን አይችልም። እንዲሁም ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመጀመሪያ የተጻፈው በግሪክኛ ቋንቋ እንደነበር ልብ ማለት ያስፈልጋል። “ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ” የሚለው ጥቅስ በመጀመሪያ ሲጻፍ “ከእግዚአብሔር” ከሚለው ቃል በፊት፣ ቃሉ ሁሉን ቻይ አምላክን እንደሚያመለክት የሚጠቁም አመልካች መስተኣምር ገብቷል። ይሁንና “ቃልም እግዚአብሔር [a god] ነበረ” በሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ ከተጠቀሰው “እግዚአብሔር” ከሚለው ቃል በፊት አመልካች መስተኣምር አልገባም። በመሆኑም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ጥቅሱን “ሎጎስም [ቃልም] መለኮት ነበረ” በማለት ተርጉመውታል። (ኤ ኒው ትራንስሌሽን ኦቭ ዘ ባይብል)a
በግሪክኛው ጽሑፍ፣ በዮሐንስ 1:1 ላይ የሚገኘው “እግዚአብሔር” ተብሎ የተተረጎመው “አምላክ [a god]” የሚለው አገላለጽ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችም ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል። ለምሳሌ ያህል ቀዳማዊ ሄሮድስ አግሪጳ ንግግር ሲያቀርብ ተሰብስቦ ያዳምጥ የነበረው ሕዝብ ‘ይህስ የአምላክ [a god] ድምፅ ነው’ ብሎ ጮኾ ነበር። እንዲሁም ሐዋርያው ጳውሎስ መርዘኛ እባብ ነድፎት እንዳልሞተ የተመለከቱ ሰዎች “ይህስ አምላክ [a god] ነው” ብለዋል። (የሐዋርያት ሥራ 12:22፤ 28:3-6) ቃል እግዚአብሔር ሳይሆን “አምላክ [a god]” መባሉ ከግሪኩ ሰዋስውም ሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚስማማ ነው።—ዮሐንስ 1:1
እስቲ ዮሐንስ በጻፈው ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ስለ “ቃል” ምን ብሎ እንደገለጸ ተመልከት። “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም . . . ከአባቱ ዘንድ የመጣውን [የእግዚአብሔርን ሳይሆን] የአንድያ ልጅን ክብር አየን” ብሎ ጽፏል። ስለዚህ ሥጋ የሆነው “ቃል” ኢየሱስ የሚባል ሰው ሆኖ በምድር ላይ ኖሯል፤ ሰዎችም አይተውታል። ዮሐንስ “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም” በማለት ስለተናገረ ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ሊሆን አይችልም።—ዮሐንስ 1:14, 18
-