የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘እውነት ምንድን ነው?’
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሐምሌ 1
    • ‘እውነት ምንድን ነው?’

      ፊት ለፊት የሚተያዩት ሁለቱ ሰዎች በጣም የተለያዩ አመለካከቶች ነበሯቸው። አንደኛው ብስጩ፣ ታዋቂ ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ያለው፣ ሀብታምና ሥልጣኑን ከፍ ለማድረግ ሲል ማንኛውንም ነገር ከማድረግ የማይመለስ የፖለቲካ ሰው ነበር። ሌላኛው ሀብትና ክብር የማይፈልግ ከመሆኑም በተጨማሪ የሌሎችን ሕይወት ለማዳን ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት ለማድረግ የተዘጋጀ መምህር ነበር። እነዚህ ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት አመለካከት እንደሌላቸው ምንም ጥርጥር የለውም! በተለይ በአንድ ጉዳይ ላይ በፍጹም አልተስማሙም ነበር። ይኸውም እውነትን በተመለከተ ነበር።

      ሰዎቹ ጴንጤናዊው ጲላጦስና ኢየሱስ ክርስቶስ ናቸው። ኢየሱስ ወንጀለኛ ነህ ተብሎ ጲላጦስ ፊት ቆሟል። ለምን? ኢየሱስ ወደ ምድር እንዲመጣና አገልግሎቱን እንዲያከናውን ያደረገውን ምክንያት ሲናገር ለአንድ ነገር ይኸውም ለእውነት እንደመጣ ገልጿል። “እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ” በማለት ተናግሯል።—ዮሐንስ 18:37

      ጲላጦስ “እውነት ምንድር ነው?” በማለት የሰጠው ምላሽ ልብ ሊባል የሚገባው ጥያቄ ነበር። (ዮሐንስ 18:38) በእርግጥ ለጥያቄው መልስ ማግኘት ፈልጎ ነበርን? አልነበረም። ኢየሱስ በቅንነት የተጠየቀውን ማንኛውንም ጥያቄ መመለስ የሚችል ዓይነት ሰው ቢሆንም ለጲላጦስ ግን አልመለሰለትም። ከዚህም በተጨማሪ ጥያቄውን ከጠየቀ በኋላ ጲላጦስ ወዲያውኑ የፍርድ ቤቱን አዳራሽ ጥሎ እንደወጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የሮማው አገረ ገዢ ጥያቄውን ያቀረበው አለመቀበሉን በሚያሳይ ብስጭት ሳይሆን አይቀርም። ጥያቄው “እውነት? እውነት ደግሞ ምንድን ነው? እንዲህ ብሎ ነገር የለም!” እንደማለት ነበር።a

  • ‘እውነት ምንድን ነው?’
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሐምሌ 1
    • a የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት አር ሲ ኤች ሌንስኪ እንደተናገሩት የጲላጦስ “አጠያየቅ ሃይማኖታዊ እውነት አለ ብሎ መናገር ከንቱ ግምታዊ ሐሳብ ነው የሚል ስሜት በውስጡ የያዘ ሲሆን ለእውነት ምንም ግድ የሌለውን ዓለማዊ አመለካከት ያንጸባርቃል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ