የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • 19, 20. ኢየሱስ የስብከቱ ሥራ አጣዳፊ መሆኑን በምሳሌ ያስረዳው እንዴት ነው?

      19 ሦስተኛ፣ ኢየሱስ አገልግሎቱን በጥድፊያ ስሜት አከናውኗል። በሲካር አቅራቢያ ባለው የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር ያደረገውን ውይይት አስታውስ። የኢየሱስ ሐዋርያት በዚያ ወቅት ምሥራቹን ለሌሎች መናገር አጣዳፊ እንደሆነ የተሰማቸው አይመስልም። በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ መከር ሊገባ ገና አራት ወር ይቀረዋል ትሉ የለም? እነሆ እላችኋለሁ፣ ዓይናችሁን ወደ ማሳው አቅንታችሁ አዝመራው እንደነጣ ተመልከቱ።”​—⁠ዮሐንስ 4:​35

      20 ኢየሱስ ይህን ምሳሌ የተናገረው ከነበሩበት ወቅት ጋር አያይዞ ነው። ወሩ ኪስሌው (ኅዳር/ታኅሣሥ) እንደነበር ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። የገብስ መከር የሚጀምረው ከአራት ወር በኋላ ይኸውም የፋሲካ በዓል በሚከበርበት በኒሳን 14 አካባቢ ነው። በመሆኑም በዚህ ወቅት ገበሬዎች አዝመራ ለመሰብሰብ የሚጣደፉበት ምክንያት አልነበራቸውም። ገና ብዙ ጊዜ አላቸው። ስለ ሰዎች አዝመራስ ምን ማለት ይቻላል? ለመሰብሰብ ደርሷል? ብዙዎች ለመስማት፣ ለመማር፣ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆንና ይሖዋ የዘረጋላቸውን ድንቅ ተስፋ ለማግኘት ዝግጁ ነበሩ። ኢየሱስ በምሳሌያዊ ሁኔታ ለመሰብሰብ የደረሰውን ነጣ ያለ አዝመራ ነፋሱ ዘንበል ቀና ሲያደርገው እያየ ያለ ያህል ነው።c መከር ደርሷል፤ ሥራውም አጣዳፊ ነው! በመሆኑም ኢየሱስ የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ከእነሱ ጋር እንዲቆይ ለማድረግ በፈለጉ ጊዜ “ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው” ብሏቸዋል።​—⁠ሉቃስ 4:​43

  • “የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • c አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ ይህን ጥቅስ ሲያብራራ “ሰብል በሚደርስበት ጊዜ ከአረንጓዴነት ወደ ቢጫነት አሊያም ነጣ ወዳለ ቀለም ይለወጣል፤ ይህም ለመሰብሰብ መድረሱን ይጠቁማል” ይላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ