የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሙታን ያላቸው አስተማማኝ ተስፋ
    የምትወዱት ሰው ሲሞት
    • ኢየሱስ አልዓዛር በሞተበት ጊዜ ያደረገው ነገር በጣም ሩኅሩኅ መሆኑን ያሳያል። በዚህ ጊዜ ያሳየው ጥልቅ ስሜት፣ ሙታንን ለማስነሳት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በግልጽ ያመለክታል። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “ማርያምም ኢየሱስ የነበረበት ቦታ ደርሳ ባየችው ጊዜ እግሩ ላይ ተደፋች፤ ከዚያም ‘ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር’ አለችው። ኢየሱስ እሷ ስታለቅስና አብረዋት የመጡት አይሁዳውያን ሲያለቅሱ ሲያይ እጅግ አዘነ፤ ተረበሸም። እሱም ‘የት ነው ያኖራችሁት?’ አለ። እነሱም ‘ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ’ አሉት። ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ። በዚህ ጊዜ አይሁዳውያኑ ‘እንዴት ይወደው እንደነበር ተመልከቱ!’ አሉ።”—ዮሐንስ 11:32-36

      “እጅግ አዘነ፣” “ተረበሸ” እና “እንባውን አፈሰሰ” የሚሉት ሦስት መግለጫዎች ኢየሱስ ከልብ የመነጨ ርኅራኄ እንዳሳየ ይጠቁማሉ። ሐዋርያው ዮሐንስ ይህን ልብ የሚነካ ትዕይንት ለመመዝገብ የተጠቀመባቸው የበኩረ ጽሑፉ ቃላት፣ ኢየሱስ በጣም በሚወደው ጓደኛው በአልዓዛር ሞት እንዲሁም የአልዓዛር እህት ስታለቅስ በማየቱ ስሜቱ በጣም ተነክቶ እንባው እንደፈሰሰ ያመለክታሉ።a

      በጣም የሚያስገርመው ነገር ኢየሱስ ቀደም ሲል ሌሎች ሁለት ሰዎችን ከሞት አስነስቶ የነበረ መሆኑ ነው። አሁንም ቢሆን አልዓዛርን ለማስነሳት አቅዶ ነበር። (ዮሐንስ 11:11, 23, 25) ያም ሆኖ ‘እንባውን አፍስሷል።’ ስለዚህ ኢየሱስ ሙታንን የሚያስነሳው ግዴታውን ለመወጣት ሲል አይደለም። በዚህ ጊዜ ያሳየው ከአንጀት የመነጨ የርኅራኄ ስሜት፣ ሞትን ፈጽሞ ለመሻር ጥልቅ የሆነ ፍላጎት እንዳለው በግልጽ ያመለክታል።

      ኢየሱስ አልዓዛርን ባስነሳበት ጊዜ ያሳየው ልባዊ ርኅራኄ፣ ሞትንና ሞት ያስከተላቸውን ውጤቶች ፈጽሞ ለማስወገድ ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ያሳያል

  • ሙታን ያላቸው አስተማማኝ ተስፋ
    የምትወዱት ሰው ሲሞት
    • a “እጅግ አዘነ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ጥልቅ የሐዘን ስሜትን ከሚያመለክት ግስ (ኤምብሪማኦሜ) የተወሰደ ነው። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር “እዚህ ላይ ቃሉ የሚያመለክተው ኢየሱስ የጠለቀ የሐዘን ስሜት ተሰምቶት ከልቡ እንደቃተተ ነው” ብለዋል። “ተረበሸ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል መታወክን ከሚያመለክት ቃል (ታራሶ) የተወሰደ ነው። አንድ የመዝገበ ቃላት አዘጋጅ እንዳሉት ቃሉ “አንድ ሰው ውስጡ እንደተረበሸ እንዲሁም ከፍተኛ ሥቃይ ወይም ሐዘን እንደተሰማው” ይጠቁማል። “እንባውን አፈሰሰ” የሚለው አገላለጽ “ምንም ድምፅ ሳያሰሙ ማልቀስ” የሚል ትርጉም ካለው የግሪክኛ ግስ (ዳክሪኦ) የተወሰደ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ