የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መጽናናትን ለማግኘት ይሖዋን ተስፋ አድርግ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
    • 14. (ሀ) ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ምን ቃል ገብቷል? (ለ) የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ከሚሰጠው ማጽናኛ ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንድንችል ምን ነገር አስፈላጊ ነው?

      14 ኢየሱስ ከሞተበት ቀን በፊት በነበረው ምሽት ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚለያቸውና ወደ አባቱ እንደሚመለስ ለታማኝ ሐዋርያቱ ገልጾላቸው ነበር። ይህን ሲሰሙ በጣም አዝነውና ተረብሸው ነበር። (ዮሐንስ 13:33, 36፤ 14:27-31) የማያቋርጥ ማጽናኛ እንደሚያስፈልጋቸው በመገንዘብ ኢየሱስ “እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል” ሲል ቃል ገብቶላቸዋል። (ዮሐንስ 14:16 አዓት የግርጌ ማስታወሻ) ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ ከ50 ቀናት በኋላ በደቀ መዛሙርቱ ላይ ስለፈሰሰው የአምላክ ቅዱስ መንፈስ መናገሩ ነበር።a የአምላክ መንፈስ ብዙ ነገሮች አድርጎላቸዋል፤ በፈተናዎች ወቅት አጽናንቷቸዋል፤ የአምላክን ፈቃድ በማድረግ እንዲቀጥሉም አጠንክሯቸዋል። (ሥራ 4:31) ይሁን እንጂ ይህ እርዳታ እንዲሁ የሚገኝ ነገር ተደርጎ መታየት የለበትም። ከዚህ እርዳታ ሙሉ ጥቅም ለማግኘት እያንዳንዱ ክርስቲያን አምላክ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት የሚሰጠውን የሚያጽናና እርዳታ ለማግኘት ዘወትር መጸለይ ይኖርበታል።—ሉቃስ 11:13

  • መጽናናትን ለማግኘት ይሖዋን ተስፋ አድርግ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
    • a የአምላክ መንፈስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ላይ ካከናወናቸው ዋና ዋና ነገሮች አንዱ የአምላክ መንፈሳዊ ልጆችና የኢየሱስ ወንድሞች አድርጎ መቀባት ነው። (2 ቆሮንቶስ 1:21, 22) ይህ ለ144,000 የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ብቻ የተወሰነ ነው። (ራእይ 14:1, 3) በዛሬው ጊዜ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በምድር ላይ በገነት ለዘላለም የመኖር ተስፋ በደግነት ተሰጥቷቸዋል። ቅቡዓን ባይሆኑም እንኳ እነርሱም የአምላክን ቅዱስ መንፈስ እርዳታና ማጽናኛ ያገኛሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ