የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 10
  • ቁርጠኝነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቁርጠኝነት
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • ከኒቆዲሞስ ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ኒቆዲሞስን በምሽት አስተማረ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ እርምጃ እንዲወስዱ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ኒቆዲሞስን አስተማረ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 10

ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ኢየሱስና ኒቆዲሞስ በምሽት ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለው ሲወያዩ።

ዮሐ. 3:1, 2

ምዕራፍ 10

ቁርጠኝነት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “የአምላክን ምሥራች ለማካፈል ብቻ ሳይሆን ራሳችንን ጭምር ለእናንተ ለመስጠት ቆርጠን ነበር፤ ምክንያቱም እናንተ በእኛ ዘንድ እጅግ የተወደዳችሁ ነበራችሁ።”—1 ተሰ. 2:8

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስና ኒቆዲሞስ በምሽት ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለው ሲወያዩ።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን አስተማረው

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 3:1, 2ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ኒቆዲሞስ ኢየሱስ ጋ በምሽት መሄድ የመረጠው ለምን ሊሆን ይችላል?—ዮሐንስ 12:42, 43ን ተመልከት።

  2. ለ. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. ለሰዎች ፍቅር ካለን ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ለመርዳት ቁርጠኛ እንሆናለን።

ኢየሱስን ምሰል

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህ በሚመቸው ጊዜና ቦታ አጥኑ። የምታስጠናው ሰው የሚመርጠው ቀንና ሰዓት ይኖር ይሆን? የት ቢያጠናስ ይመቸዋል? በሥራ ቦታው፣ ቤቱ ወይስ ሌላ ቦታ? በተቻለህ አቅም ፕሮግራምህን ከእሱ ጋር ለማስማማት ጥረት አድርግ።

4. በቋሚነት አጥኑ። የማትኖርበት ሁኔታ ከተፈጠረ ጥናታችሁን አትሰርዝ። ከዚህ ይልቅ እንዲህ ማድረግ ትችል ይሆን?

  1. ሀ. በዚያው ሳምንት በሌላ ቀን ማጥናት

  2. ለ. በስልክ ወይም በቪዲዮ ኮንፈረንስ ማጥናት

  3. ሐ. ሌላ አስፋፊ ጥናቱን እንዲመራ ማመቻቸት

5. ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖርህ ጸልይ። ተማሪው በቋሚነት ለማጥናት ወይም የተማረውን ተግባራዊ ለማድረግ ቢቸገርም እንኳ ተስፋ እንዳትቆርጥበት ወደ ይሖዋ ጸልይ። (ፊልጵ. 2:13) መቼም ግለሰቡ ጥሩ ባሕርያት ይኖሩታል፤ እነዚያ ላይ ለማተኮር እንዲረዳህ ጸልይ።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ምሳሌ 3:27፤ ሥራ 20:35፤ 2 ቆሮ. 12:15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ