-
ዳግመኛ መወለድ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሚያዝያ 1
-
-
ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ዳግመኛ መወለድ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የገለጸበትን መንገድ ልብ በል። “ማንም ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የአምላክን መንግሥት ሊያይ አይችልም” ብሏል። (ዮሐንስ 3:3) “በቀር” እና “አይችልም” የሚሉት ቃላት እንደ አዲስ መወለድ ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን የሚያጎሉ ናቸው። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ አንድ ሰው “ፀሐይ ካልወጣች በቀር ብርሃን ሊኖር አይችልም” ቢል ብርሃን እንዲኖር ፀሐይ መውጣቷ የግድ አስፈላጊ መሆኑን መግለጹ ነው። በተመሳሳይም ኢየሱስ የአምላክን መንግሥት ለማየት ዳግመኛ መወለድ የግድ አስፈላጊ መሆኑን መናገሩ ነበር።
-
-
ዳግመኛ መወለድ በእኛ ምርጫ ላይ የተመካ ነው?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሚያዝያ 1
-
-
ኢየሱስ የተናገረውን ሐሳብ ልብ ብለን ካነበብን ዳግመኛ መወለድ፣ በግለሰቦች ምርጫ ላይ የተመካ መሆኑን እንዳላስተማረ መገንዘብ እንችላለን። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? “ዳግመኛ መወለድ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ሐረግ “ከላይ መወለድ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል።a በዚህ አተረጓጎም መሠረት አንድ ሰው እንደ አዲስ መወለድን ማግኘት የሚችለው “ከላይ” ማለትም በሰማይ ከሚኖረው “አባት” ነው። (ዮሐንስ 19:11፤ ያዕቆብ 1:17) አዎን፣ አንድ ሰው ዳግመኛ እንዲወለድ የሚያደርገው አምላክ ነው።—1 ዮሐንስ 3:9
-