-
“በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
16. የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ ያሳዩት እንዴት ነበር?
16 ይሖዋ እነዚህን ሰዎች እንደባረካቸው በግልጽ ታይቷል። ዘገባው እንደሚከተለው ይላል፦ “ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውም ነገር ሁሉ የጋራ ነበር፤ በተጨማሪም ያላቸውን ሀብትና ንብረት በመሸጥ ገንዘቡን ለሁሉም አከፋፈሉ። ለእያንዳንዱም ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ሰጡ።”f (ሥራ 2:44, 45) እውነተኛ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ዓይነቱን የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ የሚንጸባረቅበት ፍቅር መኮረጅ እንደሚፈልጉ እሙን ነው።
-