-
“ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
14, 15. (ሀ) መላእክቱ የክርስቶስን መመለስ አስመልክተው ምን አሉ? ይህን ሲሉስ ምን ማለታቸው ነበር? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።) (ለ) ክርስቶስ የተመለሰው ‘በዚያው በሄደበት ሁኔታ’ ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?
14 በዚህ ምዕራፍ መግቢያ ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ ከምድር ከፍ ከፍ ካለ በኋላ ከእይታ ተሰውሯል። አሥራ አንዱ ሐዋርያት ግን ወደ ሰማይ እየተመለከቱ እዛው በቆሙበት ቀርተዋል። በመጨረሻም ሁለት መላእክት ተገልጠው ደግነት በተሞላበት መንገድ የሚከተለውን ተግሣጽ ሰጧቸው፦ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የተወሰደው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመጣል።” (ሥራ 1:11) መላእክቱ ይህን ሲሉ አንዳንድ ሃይማኖቶች እንደሚያስተምሩት ኢየሱስ ያንኑ አካል ይዞ ዳግመኛ እንደሚመጣ መናገራቸው ነበር? በፍጹም! እንዲህ ማለታቸው አልነበረም። ይህን እንዴት እናውቃለን?
15 መላእክቱ ኢየሱስ “በዚሁ ሁኔታ” እንጂ “በዚሁ አካል” ተመልሶ ይመጣል አላሉም።b ታዲያ ኢየሱስ የሄደው በምን ዓይነት ሁኔታ ነው? መላእክቱ ሐዋርያቱን ባነጋገሩበት ጊዜ ኢየሱስ ከእይታ ተሰውሮ ነበር። ኢየሱስ ምድርን ለቆ በሰማይ ወደሚገኘው አባቱ በመሄድ ላይ መሆኑን ያስተዋሉት በዚያ የነበሩት ጥቂት ሰዎች ይኸውም ሐዋርያቱ ብቻ ነበሩ። ክርስቶስ የሚመለሰውም ከዚህ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ መሆን ነበረበት። ደግሞም ክርስቶስ የተመለሰው በዚሁ ሁኔታ ነው። በዛሬው ጊዜ ኢየሱስ በንጉሣዊ ሥልጣኑ እንደተገኘ የሚገነዘቡት መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው። (ሉቃስ 17:20) በመሆኑም እኛ የኢየሱስን መገኘት የሚያሳየውን ማስረጃ ማስተዋል ይኖርብናል፤ እንዲሁም ማስረጃውን ለሌሎች በመንገር እነሱም የጊዜውን አጣዳፊነት መገንዘብ እንዲችሉ መርዳት አለብን።
-
-
“ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
b እዚህ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀመው አካላዊ “ቅርጽ” የሚል ትርጉም ያለውን ሞርፊ የተባለውን የግሪክኛ ቃል ሳይሆን “ሁኔታን” የሚያመለክተውን ትሮፖስ የሚለውን የግሪክኛ ቃል ነው።
-