-
‘አምላክ አያዳላም’‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
1-3. ጴጥሮስ ምን ራእይ አየ? ትርጉሙን መረዳታችን አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?
ጊዜው 36 ዓ.ም. የመከር ወቅት ነው። የፀሐይዋ ሙቀት ደስ ይላል፤ ጴጥሮስ ያለው የወደብ ከተማ በሆነችው በኢዮጴ ነው፤ በአንድ ቤት ሰገነት ላይ ሆኖ እየጸለየ ነው። ወደዚህ ቤት በእንግድነት ከመጣ የተወሰኑ ቀናት አልፈዋል። የቤቱ ባለቤት ስምዖን የተባለ ቆዳ ፋቂ ነው፤ አብዛኞቹ አይሁዳውያን በእንዲህ ዓይነቱ ሰው ቤት ለማረፍ ፈቃደኛ አይሆኑም።a ጴጥሮስ እዚህ ቤት በእንግድነት ለማረፍ ፈቃደኛ መሆኑ በራሱ፣ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ጭፍን ጥላቻን እንዳሸነፈ የሚያሳይ ነው። ያም ቢሆን ጴጥሮስ ይሖዋ የማያዳላ አምላክ መሆኑን በተመለከተ ገና ሊማረው የሚገባ አስፈላጊ ትምህርት አለ።
-