-
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነውለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
6. ሁሉም ሰው ሊያገኘው የሚችል መጽሐፍ
በታሪክ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በስፋት የተተረጎመና የተሰራጨ መጽሐፍ የለም። የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
አምላክ ቃሉ ይህን ያህል በስፋት እንዲተረጎምና እንዲሰራጭ የሚፈልገው ለምንድን ነው?
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ካነሳናቸው ነጥቦች መካከል ትኩረትህን የሳበው የትኛው ነው?
ወደ
100%
የሚጠጋ የዓለማችን ሕዝብ
መጽሐፍ ቅዱስን ሊገባው በሚችለው ቋንቋ ማግኘት ይችላል
ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል
ከ3,000
በሚበልጡ ቋንቋዎች
ይገኛል
ከ5,000,000,000
በላይ ቅጂዎች እንደታተሙ ይታመናል
በሕትመት ብዛት የትኛውም መጽሐፍ አይወዳደረውም
-
-
የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
ይሖዋ ሁሉንም ሰዎች ይወዳል፤ ‘የጠበቀ ወዳጅነት ያለው ግን ከቅኖች ጋር ነው።’ (ምሳሌ 3:32) ይሖዋ ወዳጆቹ በእሱ ፊት ጥሩ የሆኑትን ነገሮች እንዲያደርጉና በእሱ ፊት መጥፎ ከሆኑ ነገሮች እንዲርቁ ይፈልጋል። አንዳንዶች ይሖዋ ጥሩና መጥፎ የሆነውን ነገር በተመለከተ ያወጣውን መሥፈርት ፈጽሞ ሊያሟሉ እንደማይችሉ ይሰማቸው ይሆናል። ሆኖም ይሖዋ ያለብንን የአቅም ገደብ ይረዳል። ከልባችን እስከወደድነውና እሱን ለማስደሰት የምንችለውን ሁሉ እስካደረግን ድረስ ይቀበለናል።—መዝሙር 147:11፤ የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35
-
-
ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ አበርክትለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ጭፍን ጥላቻን አስወግድ
ሁሉንም ወንድሞቻችንን መውደድ እንዳለብን እናውቃለን። ሆኖም ከእኛ የተለየ ዘር ወይም ባሕል ያላቸውን ሰዎች መውደድ ከባድ ሊሆንብን ይችላል። በዚህ ረገድ ምን ይረዳናል? የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ምሥክሮቹ አድርጎ ይቀበላል። ይህን ማወቅህ ከአንተ የተለየ ዘር ወይም ባሕል ላላቸው ሰዎች ባለህ አመለካከት ላይ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይገባል?
በአካባቢህ የሚኖሩ በርካታ ሰዎች ምን ዓይነት ጭፍን ጥላቻ አላቸው? እንዲህ ያለውን ጭፍን ጥላቻ ማስወገድ ያለብህ ለምንድን ነው?
ሁለተኛ ቆሮንቶስ 6:11-13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ከአንተ የተለየ ባሕልና አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ለመቀራረብ ምን ይረዳሃል?
-