-
“በአንድ ልብ ወሰንን”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
9. ያዕቆብ ያቀረበው ሐሳብ ምን ጥቅሞች ነበሩት?
9 ያዕቆብ ያቀረበው ሐሳብ ጥሩ ነበር? በሚገባ! ምክንያቱም በኋላ ላይ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ውሳኔ አድርገው ያስተላለፉት እሱ ያቀረበውን ሐሳብ ነው። ምን ጥቅሞችስ ነበሩት? በአንድ በኩል ከአሕዛብ የመጡት ክርስቲያኖች ‘እንዲቸገሩ’ የሚያደርግ አይደለም፤ ምክንያቱም በሙሴ ሕግ ላይ የሰፈሩትን ደንቦች እንዲጠብቁ አያስገድድም። (ሥራ 15:19) በሌላ በኩል ደግሞ የአይሁዳውያን ክርስቲያኖችን ሕሊና ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፤ እነዚህ ወንድሞች ለዓመታት ‘በሰንበት ቀናት ሁሉ በምኩራቦች ውስጥ ከሙሴ መጻሕፍት ሲነበብ’ ሲሰሙ እንደኖሩ ይታወቃል።b (ሥራ 15:21) በእርግጥም የቀረበው ሐሳብ አይሁዳውያን በሆኑና ከአሕዛብ በመጡ ክርስቲያኖች መካከል ያለውን ወዳጅነት የሚያጠናክር ነው። ከሁሉ በላይ ደግሞ ይሖዋን የሚያስደስት ነው፤ ምክንያቱም ወደፊት ከሚገሰግሰው ዓላማው ጋር የሚስማማ ነው። መላውን የአምላክ ሕዝቦች ጉባኤ አንድነትና ደህንነት ስጋት ላይ ጥሎ የነበረው ጉዳይ እልባት ያገኘበት መንገድ አስደናቂ ነው! ዛሬ ላለው የክርስቲያን ጉባኤም እንዴት ያለ ግሩም ምሳሌ ነው!
-
-
“በአንድ ልብ ወሰንን”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
b ያዕቆብ ከሙሴ መጻሕፍት ላይም ማጣቀሱ ጥበብ የሚንጸባረቅበት ነው። እነዚህ መጻሕፍት ሕጉን ብቻ ሳይሆን ከሕጉ በፊት አምላክ ከሰዎች ጋር ስለነበረው ግንኙነት የሚገልጹ ዘገባዎችን ይዘዋል፤ ዘገባዎቹ፣ የሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት የአምላክ ፈቃድ ምን እንደነበረ ይጠቁማሉ። ለምሳሌ ያህል፣ አምላክ ስለ ደም፣ ስለ ምንዝርና ስለ ጣዖት አምልኮ ያለው አመለካከት በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ በግልጽ ሰፍሯል። (ዘፍ. 9:3, 4፤ 20:2-9፤ 35:2, 4) በመሆኑም ይሖዋ አይሁዳዊ፣ አሕዛብ ሳይል መላው የሰው ዘር ሊጠብቃቸው የሚገቡ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ሰጥቷል።
-