የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ልድያ እንግዳ ተቀባይ የነበረችው የአምላክ አገልጋይ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መስከረም 15
    • ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ያከናወነው ስብከት

      ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ አውሮፓን የረገጠውና በፊልጵስዩስ መስበክ የጀመረው በ50 እዘአ አካባቢ ነበር።a ጳውሎስ ወደ አንድ አዲስ ከተማ በሚደርስበት ጊዜ ለአይሁድና ወደ አይሁድ እምነት ለተለወጡ ሰዎች ለመስበክ በመጀመሪያ ሰዎች ወደሚሰበሰቡበት ምኩራብ የመሄድ ልማድ ነበረው። (ከሥራ 13:4, 5, 13, 14፤ 14:1 ጋር አወዳድር።) ሆኖም አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት “ቅዱስ ክልል” ተብላ በምትታወቀው በፊልጵስዩስ አይሁዶች ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን እንዳያከናውኑ የሮም ሕግ ይከለክል ነበር። ስለዚህ ሚስዮናውያኑ “ጥቂት ቀኖች” ካሳለፉ በኋላ በሰንበት ቀን ከከተማው ውጪ ባለው ወንዝ አጠገብ ‘የጸሎት ቦታ ነው ብለው የገመቱትን’ አንድ ቦታ አገኙ። (ሥራ 16:12, 13) ይህ ወንዝ ጋንጊተስ የሚባለው ወንዝ ሳይሆን አይቀርም። እዚያም ሚስዮናውያኑ ያገኙት ሴቶችን ብቻ ነበር። ከእነርሱም መሃል አንዷ ልድያ ነበረች።

  • ልድያ እንግዳ ተቀባይ የነበረችው የአምላክ አገልጋይ
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መስከረም 15
    • a በወታደራዊ ቅኝ ግዛት ሥር የነበረችውና በዩስ ኢታሊከም (በኢጣሊያ ሕግ) የምትተዳደረው ፊልጵስዩስ ከመቄዶንያ ታላላቅ ከተሞች ጋር ስትወዳደር አንጻራዊ ብልጽግና የነበራት ከተማ ነች።—ሥራ 16:9, 12, 21

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ