የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነሱ ጋር ተወያየ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • ጳውሎስና ሲላስ በቁጣ ከተሞሉት ሰዎች ለማምለጥ ወደ አንድ ግቢ ሲገቡ። አንድ ሰው ከውጭ ያሉትን የተቆጡ ሰዎች በበሩ በኩል ሲያነጋግራቸው ይታያል።

      “ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ” ፈልገው ነበር።—የሐዋርያት ሥራ 17:5

      10 ሉቃስ ቀጥሎ የሆነውን ነገር እንደሚከተለው በማለት ይነግረናል፦ “አይሁዳውያን ቅናት ስላደረባቸው በገበያ ስፍራ የሚያውደለድሉ አንዳንድ ክፉ ሰዎችን አሰባስበው አሳደሙ፤ ከተማዋንም በሁከት አመሷት። ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ የያሶንን ቤት ሰብረው ገቡ። ባጧቸው ጊዜም ያሶንንና አንዳንድ ወንድሞችን እየጎተቱ ወስደው የከተማዋ ገዢዎች ፊት በማቅረብ እንዲህ እያሉ ጮኹ፦ ‘ዓለምን ሁሉ ያናወጡት እነዚያ ሰዎች እዚህም መጥተዋል፤ ያሶንም በእንግድነት ተቀብሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሳርን ሕግ የሚቃረን ነገር ያደርጋሉ።’” (ሥራ 17:5-7) ታዲያ ይህ የሕዝብ ዓመፅ በጳውሎስና በጉዞ ጓደኞቹ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳደረ?

      11. በጳውሎስና አብረውት ባሉት የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ላይ ምን ክስ ተመሠረተባቸው? ከሳሾቻቸው ይህን ክስ ሲሰነዝሩ የትኛውን ሕግ በአእምሯቸው ይዘው ሊሆን ይችላል? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      11 የሕዝብ ዓመፅ በጣም አደገኛ ነው። ድንገት ግልብጥ ብሎ እንደሚመጣ ጎርፍ ለመግታትና ለመቆጣጠር ያስቸግራል። አይሁዳውያን፣ ጳውሎስንና ሲላስን ለማስወገድ የተጠቀሙበት መሣሪያ ይህ ነበር። በመጀመሪያ አይሁዳውያኑ ‘ከተማዋን በሁከት አመሷት።’ ከዚያም ከባድ ወንጀል እንደተፈጸመ ገዢዎቹን ለማሳመን ሞከሩ። የመጀመሪያው ክስ፣ ጳውሎስና አብረውት ያሉት የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ‘ዓለምን ሁሉ አናውጠዋል’ የሚል ነው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በተሰሎንቄ ሁከት እንዲቀሰቀስ ያደረጉት ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ አይደሉም! ሁለተኛው ክስ ደግሞ ከዚህም ከበድ ያለ ነው። ‘ኢየሱስ ስለተባለ ሌላ ንጉሥ በማወጅ የንጉሠ ነገሥቱን ሕግ ጥሰዋል’ በማለት ሚስዮናውያኑን ወነጀሏቸው።a

      12. በተሰሎንቄ በነበሩት ክርስቲያኖች ላይ የተሰነዘረው ክስ ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችል እንደነበር የሚያሳየው ምንድን ነው?

      12 የሃይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ላይም ተመሳሳይ ክስ ሰንዝረው እንደነበር አስታውስ። ጲላጦስን “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያሳምፅ፣ . . . ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አግኝተነዋል” ብለውት ነበር። (ሉቃስ 23:2) ጲላጦስም፣ ንጉሠ ነገሥቱ ‘አገር የመክዳት ወንጀል ሲፈጸም እያየህ ዝም ትላለህ’ እንዳይለው በመስጋት ሳይሆን አይቀርም፣ ኢየሱስን እንዲገደል አሳልፎ ሰጠው። በተሰሎንቄ በሚገኙት ክርስቲያኖች ላይ የቀረበው ክስም ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችል ነበር። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “‘አንድ ሰው በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ክህደት ፈጽሟል ተብሎ ስለተወራበት ብቻ እንኳ ሊገደል ይችል ነበር’፤ በመሆኑም በክርስቲያኖች ላይ የቀረበው ይህ ክስ መዘዙ እጅግ የከፋ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።” ታዲያ አይሁዳውያን በጥላቻ ተነሳስተው የሰነዘሩት ይህ ጥቃት ያሰቡትን ውጤት አስገኝቶላቸው ይሆን?

  • “ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነሱ ጋር ተወያየ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • a አንድ ምሁር እንደገለጹት በዘመኑ በነበረው የቄሳር ሕግ መሠረት “አዲስ ንጉሥ ወይም መንግሥት እንደሚመጣ በተለይም በወቅቱ ያለውን ንጉሠ ነገሥት እንደሚተካ ወይም በእሱ ላይ እንደሚፈርድ” መተንበይ የተከለከለ ነው። ተቃዋሚዎች የጳውሎስን መልእክት በማጣመም ሳይሆን አይቀርም ይህን ሕግ የሚጥስ ነገር እንዳደረገ በመግለጽ ወንጅለውታል። “ቄሳሮችና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ