የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ተቃውሞ ቢኖርም “የይሖዋ ቃል . . . እየተስፋፋና እያሸነፈ ሄደ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • “ታላቅ ሁከት ተፈጠረ” (የሐዋርያት ሥራ 19:23-41)

      ድሜጥሮስ የአርጤምስን ቤተ መቅደስ የብር ምስል ይዟል፤ በኤፌሶን ባለ የብር አንጥረኞች ሱቅ ለሚሠሩ ባልደረቦቹ በቁጣ ተሞልቶ እየተናገረ ነው። ማዶ ላይ ጳውሎስ በገበያ ቦታ ለተሰበሰቡ ሰዎች ሲሰብክ ይታያል።

      “እናንተ ሰዎች፣ መቼም ብልጽግናችን የተመካው በዚህ ሥራ ላይ እንደሆነ ታውቃላችሁ።”—የሐዋርያት ሥራ 19:25

      16, 17. (ሀ) ድሜጥሮስ በኤፌሶን ረብሻ እንዲቀሰቀስ ያደረገው እንዴት ነው? (ለ) የኤፌሶን ነዋሪዎች ጽንፈኛ መሆናቸውን ያሳዩት እንዴት ነው?

      16 አሁን ደግሞ ሰይጣን የተጠቀመበትን ሌላ ዘዴ እንመልከት፤ ሉቃስ “የጌታን መንገድ በተመለከተ ታላቅ ሁከት ተፈጠረ” ብሏል። ሉቃስ ይህን ሲል እያጋነነ አልነበረም።e (ሥራ 19:23) ሁከቱን የቀሰቀሰው ድሜጥሮስ የተባለ የብር አንጥረኛ ነው። በመጀመሪያ፣ የሙያ ባልደረቦቹን ትኩረት ለመሳብ ብልጽግናቸው የተመካው የጣዖት ምስሎችን በመሸጥ ላይ እንደሆነ ጠቀሰላቸው። ቀጥሎም ክርስቲያኖች ጣዖታትን ስለማያመልኩ ጳውሎስ የሚሰብከው መልእክት የገቢ ምንጫቸውን እንደሚያደርቅባቸው ገለጸ። ከዚያም የአገር ፍቅር ስሜታቸውን ለመቀስቀስ ሞከረ፤ ድሜጥሮስ፣ የኤፌሶን ሰዎች በከተማቸውና በዜግነታቸው እንደሚኮሩ ያውቃል፤ በመሆኑም አምላካቸው አርጤምስም ሆነች በዓለም ሁሉ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ቤተ መቅደሷ ‘ዋጋ ቢስ ሆነው እንደሚቀሩ’ በመግለጽ ክብራቸው እንደተነካ እንዲሰማቸው አደረገ።—ሥራ 19:24-27

  • ተቃውሞ ቢኖርም “የይሖዋ ቃል . . . እየተስፋፋና እያሸነፈ ሄደ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • e አንዳንዶች፣ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ “በሕይወት የመትረፍ ተስፋችን እንኳ ተሟጦ ነበር” ያለው ይህን ገጠመኝ አስቦ እንደሆነ ይናገራሉ። (2 ቆሮ. 1:8) ይሁን እንጂ ከዚህም የከፋ አደገኛ ሁኔታ ያጋጠመውን ጊዜ መጥቀሱ ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ “በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር [እንደታገለ]” ሲጽፍ በመወዳደሪያ ቦታዎች ከጨካኝ አራዊት ጋር መታገሉን መግለጹ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም ደግሞ ከሰዎች ኃይለኛ ተቃውሞ እንዳጋጠመው እየተናገረ ይሆናል። (1 ቆሮ. 15:32) ሐሳቡ ቃል በቃል አሊያም ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ሊወሰድ ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ