-
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”“ተከታዬ ሁን”
-
-
5. ኢየሱስ ከተጠቀመባቸው ቀላል ሆኖም ጥልቅ ትርጉም ያላቸው አገላለጾች መካከል አንዳንድ ምሳሌዎችን ጥቀስ።
5 ኢየሱስ ጥልቅ ትርጉም ያላቸውን ሐሳቦች ቀላልና አጫጭር አገላለጾች በመጠቀም ያስተምር ነበር። በዚያ ዘመን አድማጮቹ የተናገረውን ነገር መልሰው ሊያነብቡት ስለማይችሉ ትምህርቱ በአእምሯቸውና በልባቸው ውስጥ በማይፋቅ ሁኔታ እንዲታተም አድርጓል። እስቲ አንዳንዶቹን እንደ ምሳሌ እንመልከት፦ “እንዳይፈረድባችሁ በሌሎች ላይ አትፍረዱ።” “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።” “መንፈስ ዝግጁ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው።” “የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ ስጡ።” “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።”b (ማቴዎስ 7:1፤ 9:12፤ 26:41፤ ማርቆስ 12:17፤ የሐዋርያት ሥራ 20:35) የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ የተነገሩት እነዚህ አባባሎች ዛሬም ትልቅ ትርጉም አላቸው።
-
-
“ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም”“ተከታዬ ሁን”
-
-
b መጨረሻ ላይ የተጠቀሰውን በሐዋርያት ሥራ 20:35 ላይ የሚገኘውን አባባል ያሰፈረው ሐዋርያው ጳውሎስ ብቻ ነው። ጳውሎስ ይህን ሐሳብ የጻፈው በቃል ተነግሮት (ማለትም ኢየሱስ ይህን ሲናገር የሰማ ሰው ወይም ትንሣኤ ያገኘው ኢየሱስ ራሱ ነግሮት) አሊያም በመለኮታዊ ራእይ ተገልጦለት ሊሆን ይችላል።
-