የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም”
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | መስከረም 1
    • 6. ኢየሱስ ቀላል ሆኖም ጥልቅ ትርጉም ያላቸው አባባሎችን ይናገር እንደነበር የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ጥቀስ።

      6 ኢየሱስ ብዙውን ጊዜ ግልጽና አጠር፣ አጠር ያሉ ሐረጎችን በመጠቀም ቀላል ሆኖም ጥልቅ ትርጉም የነበራቸውን ሐሳቦች ያስተላልፍ ነበር። መጻሕፍት በማይታተሙበት በዚያ ዘመን መልእክቱን በአድማጮቹ አእምሮና ልብ ላይ እንዲታተም አድርጓል። እስቲ አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት:- “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ . . . ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።” “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ።” “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።” “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም።” “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ።” “የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ።” ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው።’c (ማቴዎስ 6:24፤ 7:1, 20፤ 9:12፤ 26:52፤ ማርቆስ 12:17፤ ሥራ 20:35) ኢየሱስ እነዚህን ኃይል ያላቸው አባባሎች ከተናገረ ወደ 2, 000 የሚጠጉ ዓመታት ያለፉ ቢሆንም እንኳ ትምህርቶቹን በዛሬው ጊዜም በቀላሉ ማስታወስ ይቻላል።

  • “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም”
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | መስከረም 1
    • c ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው’ የሚለው በሐዋርያት ሥራ 20:​35 ላይ የሚገኘው አባባል ሐሳቡ በወንጌሎች ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም እንኳ ዓረፍተ ነገሩን በቀጥታ ጠቅሶ የተናገረው ሐዋርያው ጳውሎስ ብቻ ነው። ጳውሎስ ይህን ዓረፍተ ነገር የሰማው (ኢየሱስ ሲናገር ካዳመጠ አንድ ደቀ መዝሙር ወይም ትንሣኤ ካገኘው ኢየሱስ) ወይም በራእይ ተነግሮት ሊሆን ይችላል።​—⁠ሥራ 22:6-15፤ 1 ቆሮንቶስ 15:6, 8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ