የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 5 ጳውሎስ በንግግሩ መሃል፣ ከአውሮፓ ይዞ ስለመጣው መዋጮ ሳይጠቅስ አይቀርም። ርቀው በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ ወንድሞች ስላሳዩት አሳቢነት ሲሰሙ እነዚያ ሽማግሌዎች ልባቸው በደስታ ተሞልቶ መሆን አለበት። ዘገባው የጳውሎስን ሪፖርት ካዳመጡ በኋላ “አምላክን አመሰገኑ” ይላል። (ሥራ 21:20ሀ) ዛሬም በተመሳሳይ አደጋ የደረሰባቸው ወይም በጠና የታመሙ ክርስቲያኖች፣ የእምነት ባልንጀሮቻቸው በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ሲረዷቸውና ሲያጽናኗቸው ልባቸው በጥልቅ ይነካል።

      ብዙዎች አሁንም “ለሕጉ ቀናተኞች ናቸው” (የሐዋርያት ሥራ 21:20ለ, 21)

      6. ጳውሎስ ምን ችግር መከሰቱን ሰማ?

      6 ከዚያም ሽማግሌዎቹ ጳውሎስን በቀጥታ የሚመለከት ችግር በይሁዳ መከሰቱን ገለጹለት። እንዲህ አሉት፦ “ወንድም፣ ከአይሁዳውያን መካከል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማኞች እንዳሉ ታውቃለህ፤ ደግሞም ሁሉም ለሕጉ ቀናተኞች ናቸው። እነሱም አንተ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁዳውያን ሁሉ ልጆቻቸውን እንዳይገርዙም ሆነ የቆየውን ልማድ እንዳይከተሉ በመንገር የሙሴን ሕግ እንዲተዉ ስታስተምር እንደቆየህ ስለ አንተ የሚወራውን ወሬ ሰምተዋል።”a—ሥራ 21:20ለ, 21

      7, 8. (ሀ) በይሁዳ የነበሩ ብዙ ክርስቲያኖች ምን የተሳሳተ አመለካከት ነበራቸው? (ለ) አንዳንድ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች የነበራቸው የተሳሳተ አስተሳሰብ እንደ ክህደት ሊቆጠር የማይችለው ለምንድን ነው?

      7 የሙሴ ሕግ ከተሻረ ከ20 ዓመት በላይ አልፎታል፤ ታዲያ አሁንም ለሕጉ የሚቀኑ ብዙ ክርስቲያኖች ሊኖሩ የቻሉት እንዴት ነው? (ቆላ. 2:14) በ49 ዓ.ም. ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በኢየሩሳሌም ከተሰበሰቡ በኋላ ለጉባኤዎች ደብዳቤ ልከው ነበር፤ በደብዳቤው ላይም ከአሕዛብ የመጡ አማኞች መገረዝም ሆነ የሙሴን ሕግ መጠበቅ እንደማያስፈልጋቸው ገልጸዋል። (ሥራ 15:23-29) ይሁን እንጂ ደብዳቤው አይሁዳውያን አማኞችን በተመለከተ የሚጠቅሰው ነገር የለም፤ ደግሞም አብዛኞቹ የሙሴ ሕግ እንደተሻረ አልገባቸውም።

      8 እነዚህ አይሁዳውያን አማኞች እንዲህ ዓይነት የተሳሳተ አስተሳሰብ ስላላቸው ክርስቲያኖች አይደሉም ማለት ነው? በፍጹም። እነዚህ ሰዎች ከባዕድ አምልኮ የመጣን ሃይማኖታዊ ልማድ መከተላቸውን ለመቀጠል እየሞከሩ አይደለም። እነዚህ አይሁዳውያን አማኞች ከፍ አድርገው የሚመለከቱትን ሕግ ቀድሞውንም ቢሆን የሰጣቸው ይሖዋ ነው። በሕጉ ውስጥ ከአጋንንት ጋር ንክኪ ያለው ወይም የተሳሳተ ነገር የለም። ሆኖም ሕጉ ከተሻረው ቃል ኪዳን ጋር የተያያዘ ነበር፤ ክርስቲያኖች ደግሞ በአዲሱ ቃል ኪዳን ሥር ናቸው። በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አምልኮ ለማቅረብ የሕጉን ቃል ኪዳን ማክበር አስፈላጊ መሆኑ ቀርቷል። ለሕጉ የሚቀኑት ዕብራውያን አማኞች፣ የክርስቲያን ጉባኤን በተመለከተ ያልገቧቸው ነገሮች ነበሩ፤ ከዚህም ሌላ ይሖዋ ለጉባኤው ባደረገው አዲስ ዝግጅት ላይ እምነት አልነበራቸውም። ደረጃ በደረጃ እየተገለጠ ከሚሄደው እውነት ጋር አስተሳሰባቸውን ማስማማት ያስፈልጋቸው ነበር።b—ኤር. 31:31-34፤ ሉቃስ 22:20

  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • a በወቅቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ነበሩ፤ የሁሉንም መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላት በግል መኖሪያ ቤቶች የሚሰበሰቡ በርካታ ጉባኤዎች ማቋቋም ሳያስፈልግ አልቀረም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ