-
የጥንት ክርስቲያኖችና የሙሴ ሕግመጠበቂያ ግንብ—2003 | መጋቢት 15
-
-
አይሁዳውያን ክርስቲያኖችን በተመለከተስ ምን ለማለት ይቻላል?
12. መልስ ሳያገኝ የቀረው የትኛው ጥያቄ ነው?
12 የአስተዳደር አካሉ አሕዛብ ክርስቲያኖች መገረዝ እንደማያስፈልጋቸው በግልጽ አመልክቷል። ሆኖም አይሁዳውያን ክርስቲያኖችስ? የአስተዳደር አካሉ ባስተላለፈው ውሳኔ ውስጥ ይህን በተመለከተ የተጠቀሰ ነገር የለም።
13. ለመዳን የሙሴን ሕግ መጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ መከራከር ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?
13 ‘ለሕጉ ይቀኑ የነበሩ’ አንዳንድ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ልጆቻቸውን መግረዝና ከሕጉ ውስጥ አንዳንድ ክፍሎችን መጠበቃቸውን ቀጥለውበት ነበር። (ሥራ 21:20) ሌሎች ደግሞ አልፈው በመሄድ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ለመዳን ሕጉን መጠበቅ እንዳለባቸው እስከመከራከር ደርሰው ነበር። ይህም ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ አመለካከት እንደነበራቸው ያሳያል። ለምሳሌ ያህል አንድ ክርስቲያን የኃጢአት ይቅርታ ለማግኘት የእንስሳት መሥዋዕት እንዴት ሊያቀርብ ይችላል? የእንስሳት መሥዋዕት በክርስቶስ መሥዋዕት ተተክቷል። አይሁዳውያን ከአሕዛብ ጋር እንዳይቀራረቡ ስለሚያዝዘው ሕግስ ምን ለማለት ይቻላል? ቀናተኛ ክርስቲያን ወንጌላውያን ከዚህ ሕግ ነፃ ካልሆኑ ኢየሱስ አሕዛብን ሁሉ እንዲያስተምሩ የሰጣቸውን ተልእኮ እንዴት መፈጸም ይችላሉ? (ማቴዎስ 28:19, 20፤ ሥራ 1:8፤ 10:28)a የአስተዳደር አካሉ ባደረጋቸው ስብሰባዎቸ ላይ ይህ ጉዳይ እንደተነሳ የሚጠቁም ምንም ማስረጃ የለም። ሆኖም ጉባኤው በራሱ ፍላጎት እንዲመራ አልተተወም።
-
-
የጥንት ክርስቲያኖችና የሙሴ ሕግመጠበቂያ ግንብ—2003 | መጋቢት 15
-
-
[በገጽ 23, 24 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
ጳውሎስ ያጋጠመውን ፈተና በትሕትና ተወጣ
ጳውሎስ የተሳካ ሚስዮናዊ ጉዞ ካደረገ በኋላ በ56 እዘአ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። እዚያም ያልጠበቀው አንድ ፈተና ገጠመው። ጳውሎስ ሕጉ በክርስቲያኖች ላይ አይሠራም ብሎ እንዳስተማረ የሚገልጸው ዜና ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ጉባኤ ደርሶ ነበር። ሽማግሌዎች በቅርቡ ክርስትናን የተቀበሉ አይሁዳውያን ጳውሎስ ሕጉን በማስመልከት የሰጠውን ግልጽ ትምህርት ሲሰሙ ክርስቲያኖች ለይሖዋ ዝግጅቶች አክብሮት እንደሌላቸው አድርገው በማሰብ ይሰናከሉ ይሆናል የሚል ፍርሃት አድሮባቸው ነበር። በጉባኤው ውስጥ ስለት ምናልባትም የናዝራዊነትን ስለት የተሳሉ አራት አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ነበሩ። በሕጉ መሠረት የተሳሉትን ለመፈጸም ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ ነበረባቸው።
ሽማግሌዎቹ ጳውሎስ ከእነዚህ አራት ሰዎች ጋር ወደ ቤተ መቅደስ አብሯቸው እንዲሄድና ወጪያቸውን እንዲሸፍን ጠየቁት። ጳውሎስ ለመዳን ሕጉን መጠበቅ እንደማያስፈልግ የሚያብራሩ ቢያንስ ሁለት ደብዳቤዎች በመንፈስ አነሳሽነት ጽፎ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ለሌሎች ሰዎች ሕሊና ያስብ ነበር። ከዚያ ቀደም ሲል “ከሕግ በታች ያሉትን እጠቅም ዘንድ፣ . . . ከሕግ በታች ላሉት ከሕግ በታች እንዳለሁ ሆንሁ” በማለት ጽፎ ነበር። (1 ቆሮንቶስ 9:20-23) ጳውሎስ ወሳኝ የሆኑ ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶችን እንደሚጥስ ሆኖ ስላልተሰማው ሽማግሌዎቹ በሰጡት ሐሳብ መሠረት ከሰዎቹ ጋር አብሮ ለመሄድ ተስማማ። (ሥራ 21:15-26) ሽማግሌዎቹ ያሉትን ቢያደርግ ምንም ስህተት የለውም። የስለት ሥርዓት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ አልነበረም። ቤተ መቅደሱም የጣዖት አምልኮ ሳይሆን ንጹሕ አምልኮ የሚካሄድበት ሥፍራ ነው። ስለዚህም ጳውሎስ ለሌሎች እንቅፋት እንዳይሆን ሲል እንደተባለው አደረገ። (1 ቆሮንቶስ 8:13) ጳውሎስ እንዲህ ለማድረግ ትሕትና እንደጠየቀበት ምንም ጥርጥር የለውም። ይህም ለእርሱ ያለንን አድናቆት ከፍ ያደርገዋል።
-