የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • 17 በዚህ ጊዜ በቦታው ከቆሙት መካከል አንዳንዶቹ ደነገጡ! የደነገጡት ግን ጳውሎስ በመመታቱ ሳይሆን በሰጠው መልስ ነበር። “የአምላክን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህ?” አሉት። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ፣ የሰጠው መልስ በትሕትናና ለሕጉ አክብሮት በማሳየት ረገድ ጥሩ ትምህርት የሚሆናቸው ነው። “ወንድሞች፣ እኔ እኮ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅኩም። ምክንያቱም ‘በሕዝብህ ገዢ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ ተብሎ ተጽፏል” አላቸው።d (ሥራ 23:4, 5፤ ዘፀ. 22:28) አሁን ጳውሎስ ለየት ያለ ዘዴ ተጠቀመ። የሳንሄድሪን አባላት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን መሆናቸውን ስላወቀ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ። ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው።”—ሥራ 23:6

      አንድ ወንድም ለአንድ ቄስ እየመሠከረ ነው፤ ቄሱ በራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንድን ጥቅስ በትኩረት እየተመለከተ ነው።

      ከእኛ የተለየ ሃይማኖታዊ አመለካከት ካላቸው ሰዎች ጋር ስንወያይ እንደ ጳውሎስ በጋራ የሚያስማሙንን ነጥቦች እናነሳለን

      18. ጳውሎስ ፈሪሳዊ ነኝ ያለው ለምንድን ነው? እኛስ ከሰዎች ጋር ስንወያይ ተመሳሳይ ዘዴ ልንጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

      18 ጳውሎስ ፈሪሳዊ ነኝ ያለው ለምንድን ነው? ‘ከፈሪሳውያን ስለተወለደ’ ማለትም የፈሪሳውያን ሃይማኖታዊ ቡድን አባል ከሆነ ቤተሰብ ስለመጣ ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙዎች አሁንም የሚያዩት እንደ ፈሪሳዊ ነው።e ይሁን እንጂ ጳውሎስ ይህን ሲል ፈሪሳውያን ስለ ትንሣኤ ያላቸውን አመለካከት ይቀበላል ማለት ነው? ፈሪሳውያን፣ ሰው ሲሞት ነፍሱ እንደማትሞት እንዲሁም የጻድቅ ነፍስ እንደገና ሥጋዊ አካል ለብሳ እንደምትኖር ያምናሉ። ጳውሎስ እንዲህ ያለ አመለካከት አልነበረውም። እሱ የሚያምነው ኢየሱስ ያስተማረውን ትንሣኤ ነው። (ዮሐ. 5:25-29) ይሁንና ጳውሎስ ከፈሪሳውያን ጋር የሚያስማማው ነገር አለ፤ ከሰዱቃውያን በተቃራኒ ከሞት ባሻገር የመኖር ተስፋ እንዳለ ያምናል። እኛም የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖቶችን ከሚከተሉ ሰዎች ጋር ስንወያይ ተመሳሳይ ዘዴ መጠቀም እንችላለን። ልክ እንደ እነሱ እኛም በአምላክ እንደምናምን ልንገልጽላቸው እንችላለን። እርግጥ እነሱ የሚያምኑት በሥላሴ ሊሆን ይችላል፤ እኛ ደግሞ የምናምነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሰው አምላክ ነው። ይሁንና እነሱም እኛም በአምላክ ማመናችን ያመሳስለናል።

  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
    • e በ49 ዓ.ም. ሐዋርያትና ሽማግሌዎች፣ ‘አሕዛብ የሙሴን ሕግ ማክበር አለባቸው ወይም የለባቸውም’ በሚለው ጉዳይ ላይ ተወያይተው ነበር፤ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ “ከፈሪሳውያን ሃይማኖታዊ ቡድን መካከል አማኞች የሆኑ” ተብለዋል። (ሥራ 15:5) እንዲህ የተባለው እነዚህ አማኞች ከዚህ ቀደም ፈሪሳዊ ስለነበሩ ሊሆን ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ