-
“አይዞህ፣ አትፍራ!”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
10. በጳውሎስ ላይ የትኞቹ ከባድ ክሶች ተሰነዘሩ?
10 ጳውሎስ ከሳሾቹ ከኢየሩሳሌም እስኪመጡ ድረስ በቂሳርያ “[በሄሮድስ] ቤተ መንግሥት ውስጥ በጥበቃ ሥር ሆኖ እንዲቆይ” ተደረገ። (ሥራ 23:35) ከአምስት ቀን በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ ጠርጡለስ የሚባል ጠበቃና የተወሰኑ ሽማግሌዎች መጡ። ጠርጡለስ በመጀመሪያ፣ ፊሊክስ ለአይሁዳውያን እያደረገ ስላለው ነገር ምስጋና አቀረበ፤ ይህን ያደረገው እሱን ለመሸንገልና በእሱ ለመወደድ ብሎ እንደሆነ ግልጽ ነው።b ከዚያም ጠርጡለስ ወደ ጉዳዩ በመግባት ጳውሎስን እንዲህ ሲል ወነጀለው፦ “ይህ ሰው መቅሰፍት ሆኖብናል፤ በዓለም ባሉት አይሁዳውያን ሁሉ መካከል ዓመፅ ያነሳሳል፤ ከዚህም ሌላ የናዝሬታውያን ኑፋቄ ቀንደኛ መሪ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር ስላገኘነው ያዝነው።” የተቀሩት አይሁዳውያንም “የተባለው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን በመግለጽ በክሱ ተባበሩ።” (ሥራ 24:5, 6, 9) ዓመፅ ማነሳሳት፣ የአደገኛ ኑፋቄ ቀንደኛ መሪ መሆንና ቤተ መቅደሱን ማርከስ በሞት ሊያስቀጡ የሚችሉ ከባድ ክሶች ናቸው።
-
-
“አይዞህ፣ አትፍራ!”‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
-
-
b ጠርጡለስ፣ ለሕዝቡ “ብዙ ሰላም” በማምጣቱ ፊሊክስን አመስግኖታል። ይሁን እንጂ የፊሊክስን የግዛት ዘመን ያህል ሰላም የጠፋበት የሮም አገረ ገዢዎች ዘመን የለም፤ ከፊሊክስ ዘመን የከፋ ብጥብጥ የታየው በሮም ላይ ዓመፅ በተነሳበት ጊዜ ብቻ ነው። ጠርጡለስ፣ ፊሊክስ ላስገኘው መሻሻል አይሁዳውያን “ታላቅ ምስጋና” እንዳቀረቡ መናገሩም ዓይን ያወጣ ውሸት ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አብዛኞቹ አይሁዳውያን ፊሊክስን ይጠሉት ነበር፤ ፊሊክስ ጨቋኝ ገዢ ከመሆኑም ሌላ ዓመፅን ለማስቆም የሚወስደው እርምጃ ጭካኔ የተሞላበት ነበር።—ሥራ 24:2, 3
-