-
ትንሣኤ—አስተማማኝ ተስፋ!መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ታኅሣሥ
-
-
ኢየሱስ ትንሣኤ አግኝተው ወደ ሰማይ ከሄዱ በርካታ ሰዎች የመጀመሪያው ነው (ከአንቀጽ 15-16ን ተመልከት)b
15. “ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ” ከተባሉት መካከል እነማን ይገኙበታል?
15 ጳውሎስ “ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ” እንዳለ ልብ እንበል። (1 ቆሮ. 15:22) ጳውሎስ ደብዳቤውን የጻፈው በቆሮንቶስ ለሚኖሩ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ሲሆን እነዚህ ክርስቲያኖች ደግሞ ተስፋቸው ትንሣኤ አግኝተው ወደ ሰማይ መሄድ ነው። እነዚህ ክርስቲያኖች ‘ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባላቸው አንድነት የተቀደሱ እና ቅዱሳን ለመሆን የተጠሩ’ ናቸው። እንዲሁም ጳውሎስ “ከክርስቶስ ጋር አንድነት ኖሯቸው በሞት [ስላንቀላፉ]” ሰዎች ተናግሯል። (1 ቆሮ. 1:2፤ 15:18፤ 2 ቆሮ. 5:17) ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት በጻፈው ሌላ ደብዳቤ ላይ፣ ‘ሞቱን በሚመስል ሞት ከኢየሱስ ጋር አንድ የሆኑ ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእሱ ጋር አንድ እንደሚሆኑ’ ገልጿል። (ሮም 6:3-5) ኢየሱስ መንፈስ ሆኖ ከሞት ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ ሄዷል። ስለዚህ “ከክርስቶስ ጋር አንድነት” ያላቸው ሁሉ ማለትም ሁሉም ቅቡዓን ክርስቲያኖች ከሞት ተነስተው ወደ ሰማይ ይሄዳሉ።
-
-
ትንሣኤ—አስተማማኝ ተስፋ!መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ታኅሣሥ
-
-
17. ‘ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያላቸው’ ክርስቲያኖች ሰማያዊ ሽልማታቸውን የሚያገኙት መቼ ነው?
17 ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ደብዳቤውን በጻፈበት ወቅት ‘ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያላቸው’ ክርስቲያኖች የሚያገኙት ሰማያዊ ትንሣኤ አልጀመረም ነበር። ጳውሎስ ይህ ትንሣኤ የሚከናወነው ወደፊት እንደሆነ ጠቁሟል። እንዲህ ብሏል፦ “እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፦ ክርስቶስ በኩራት ነው፤ በመቀጠል ደግሞ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ የእሱ የሆኑት ሕያዋን ይሆናሉ።” (1 ቆሮ. 15:23፤ 1 ተሰ. 4:15, 16) አሁን የምንኖረው ጳውሎስ “ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ” ብሎ በጠቀሰው ዘመን ውስጥ ነው። ሐዋርያትም ሆኑ በሞት ያንቀላፉ ሌሎች በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች፣ ሰማያዊ ሽልማታቸውን ለማግኘትና ‘የኢየሱስን ትንሣኤ በሚመስል ትንሣኤ ከእሱ ጋር አንድ ለመሆን’ ‘የክርስቶስ መገኘት’ እስኪጀምር ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው።
-