የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውቀት የሚጻረርን ማንኛውንም የተሳሳተ ሐሳብ አፍርሱ!
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | ሰኔ
    • 1. ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ለተቀቡ ክርስቲያኖች ምን ማሳሰቢያ ሰጥቷል?

      “አትፍቀዱ።” ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። ጳውሎስ “ይህ ሥርዓት እንዲቀርጻችሁ አትፍቀዱ” ብሏል። (ሮም 12:2) ጳውሎስ ይህን ሐሳብ የተናገረው በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩ ክርስቲያኖች ነው። ይሁን እንጂ ራሳቸውን ለአምላክ ለወሰኑና በመንፈስ ቅዱስ ለተቀቡ ወንዶችና ሴቶች እንዲህ ያለ ጠንካራ ማሳሰቢያ መስጠት ያስፈለገው ለምንድን ነው?—ሮም 1:7

      2-3. ሰይጣን እኛን ከይሖዋ ለማራቅ የሚጥረው እንዴት ነው? እንደ “ምሽግ” ጠንካራ የሆኑና ሥር የሰደዱ አስተሳሰቦችን ለማስወገድ የሚረዳን ምንድን ነው?

      2 አንዳንድ ክርስቲያኖች የሰይጣን ዓለም በሚያስፋፋቸው የተሳሳቱ ሐሳቦችና ፍልስፍናዎች እየተማረኩ የነበረ ይመስላል፤ ይህ ሁኔታ ደግሞ ጳውሎስን አሳስቦት ነበር። (ኤፌ. 4:17-19) ማናችንም ብንሆን እንዲህ ባለው ተጽዕኖ ልንሸነፍ እንችላለን። የዚህ ሥርዓት አምላክ የሆነው ሰይጣን እኛን ከይሖዋ ለማራቅ የሚጠቀምባቸው የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። ለምሳሌ፣ ከፍ ያለ ቦታ ወይም እውቅና የማግኘት ፍላጎት ካለን በዚህ ይጠቀማል። በሌላ በኩል ደግሞ ያሳለፍነው ሕይወት፣ ባሕላችን እንዲሁም የቀሰምነው ትምህርት በእኛ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በመጠቀም አስተሳሰባችንን በራሱ መንገድ ለመቅረጽ ይጥራል።

  • ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውቀት የሚጻረርን ማንኛውንም የተሳሳተ ሐሳብ አፍርሱ!
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | ሰኔ
  • ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውቀት የሚጻረርን ማንኛውንም የተሳሳተ ሐሳብ አፍርሱ!
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | ሰኔ
    • “አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ”

      4. ብዙዎቻችን እውነትን ስንቀበል ምን ዓይነት ለውጥ ማድረግ አስፈልጎናል?

      4 መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና እና ይሖዋን ለማገልገል ስትወስን ምን ለውጦች ማድረግ አስፈልጎህ እንደነበረ እስቲ መለስ ብለህ አስብ። ብዙዎቻችን፣ እንፈጽማቸው የነበሩ መጥፎ ድርጊቶችን መተው አስፈልጎናል። (1 ቆሮ. 6:9-11) ይሖዋ እንዲህ ያሉ የኃጢአት ድርጊቶችን እንድንተው ስለረዳን አመስጋኞች ነን!

      5. በሮም 12:2 ላይ የተጠቀሱትን የትኞቹን ሁለት እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልገናል?

      5 ይሁንና እስካሁን ባደረግነው ለውጥ ረክተን መቀመጥ የለብንም። ከተጠመቅን በኋላ፣ ቀደም ሲል እንፈጽማቸው የነበሩ ከባድ ኃጢአቶችን አንፈጽም ይሆናል፤ ያም ቢሆን ወደ ቀድሞው አኗኗራችን እንድንመለስ ሊፈትኑን የሚችሉ ነገሮችን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለብን። ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ጳውሎስ “ይህ ሥርዓት እንዲቀርጻችሁ አትፍቀዱ፤ ከዚህ ይልቅ . . . አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ” በማለት መልሱን ይሰጠናል። (ሮም 12:2) ስለዚህ ሁለት እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልገናል። አንደኛ፣ ይህ ዓለም ‘እንዲቀርጸን መፍቀድ’ የለብንም። ሁለተኛ፣ አእምሯችንን በማደስ ‘መለወጥ’ ይኖርብናል።

      መለወጥ ወይስ መምሰል?

      ጺሙን ያሳደገና የተዝረከረከ አንድ ወጣት፣ ጺሙንና ፀጉሩን በደንብ ተስተካክሎ እንዲሁም ሸሚዝና ከረባት አድርጎ የሚያሳየውን የራሱን ምስል በእጁ ይዞ

      በሮም 12:2 ላይ “ተለወጡ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል፣ አባጨጓሬ ወደ ቢራቢሮ እንደሚለወጠው ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተለውጦ ሌላ ነገር መሆንን ያመለክታል። መለወጥ ሲባል ውስጣዊ ማንነታችንን ይኸውም አስተሳሰባችንን እና ዝንባሌያችንን መቀየር ማለት ነው። ከዚህ በተቃራኒ ግን በ2 ቆሮንቶስ 11:13-15 ላይ የሚገኘው “መምሰል” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል፣ ላይ ላዩን ብቻ ወይም ለታይታ የሚደረግ ለውጥን ያመለክታል።

      6. ኢየሱስ በማቴዎስ 12:43-45 ላይ የተናገረው ሐሳብ ምን ትምህርት ይዟል?

      6 ጳውሎስ ‘መለወጥ’ ሲል ላይ ላዩን የሚደረግ ለውጥን ብቻ ማመልከቱ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ ማንነታችንን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ለውጥን ማመልከቱ ነበር። (“መለወጥ ወይስ መምሰል?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።) አእምሯችንን ይኸውም አመለካከታችንን፣ ስሜታችንን እና ውስጣዊ ዝንባሌያችንን ሙሉ በሙሉ መለወጥ ያስፈልገናል። እንግዲያው ሁላችንም እንደሚከተለው ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን፦ ‘ክርስቶስን ለመምሰል ስል የማደርገው ለውጥ እንዲሁ የታይታ ነው? ወይስ ሥር ነቀል ለውጥ እያደረግኩ ነው?’ በሁለቱ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። ኢየሱስ በማቴዎስ 12:43-45 ላይ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልገን ተናግሯል። (ጥቅሱን አንብብ።) ይህ ጥቅስ አንድ አስፈላጊ ትምህርት ይዞልናል፦ የተሳሳቱ ሐሳቦችን ከአእምሯችን ማስወገድ ብቻውን በቂ አይደለም፤ በምትኩ አእምሯችን አምላክን በሚያስደስቱ ሐሳቦች እንዲሞላ ማድረግ ያስፈልገናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ