የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 | አትበቀል
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
    • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

      ‘ለማንም በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ። ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ። ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ይሖዋ” ተብሎ ተጽፏል።’—ሮም 12:17-19

      ምን ማለት ነው?

      ስንበደል መበሳጨታችን የማይቀር ቢሆንም አምላክ እንድንበቀል አልፈቀደልንም። ከዚህ ይልቅ፣ እሱ በቅርቡ ሁሉንም ነገር ስለሚያስተካክል እስከዚያ ጊዜ ድረስ በትዕግሥት እንድንጠባበቅ አሳስቦናል።—መዝሙር 37:7, 10

  • 2 | አትበቀል
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
    • አድሪያን 16 ዓመት ሲሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመረ። “በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቴ እየገፋሁ ስሄድ የባሕርይ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልገኝ ተገነዘብኩ” ብሏል። አድሪያን ጥላቻውን ማስወገድና ዓመፀኝነቱን መተው ነበረበት። በተለይም ሮም 12:17-19 በቀልን አስመልክቶ የሚናገረው ሐሳብ ልቡን ነካው። እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ እሱ ራሱ በፈለገው መንገድና በወሰነው ጊዜ የፍትሕ መዛባትን እንደሚያስወግድ አምኜ ተቀበልኩ። ቀስ በቀስ የዓመፀኝነት ባሕርዬን አሸነፍኩ።”

      አንድ ምሽት የአንድ የወሮበሎች ቡድን አባላት በአድሪያን ላይ ጥቃት አደረሱበት፤ ይህ ቡድን ቀደም ሲል አድሪያን የነበረበት ቡድን ተቀናቃኝ ነበር። የቡድኑ መሪ “ራስህን ተከላከል!” በማለት አድሪያን ላይ ጮኸበት። አድሪያን ‘ሲመቱት መልሶ ለመማታት በጣም እንደተፈተነ’ ሳይሸሽግ ተናግሯል። ሆኖም አጸፋውን ከመመለስ ይልቅ ወደ ይሖዋ አጭር ጸሎት ካቀረበ በኋላ ትቷቸው ሄደ።

      አድሪያን እንዲህ ብሏል፦ “በማግስቱ የቡድኑን መሪ ብቻውን አገኘሁት። ሳየው ብድሬን ለመመለስ ብገፋፋም ራሴን ለመቆጣጠር እንዲረዳኝ በድጋሚ ይሖዋን ለመንኩት። የሚገርመው ወጣቱ ቀጥ ብሎ ወደ እኔ መጣና ‘ትናንትና ማታ ለተፈጸመው ነገር ይቅርታ አድርግልኝ። እውነቱን ልንገርህ፣ እኔም እንዳንተ መሆን ብችል ደስ ይለኛል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እፈልጋለሁ’ አለኝ። ቁጣዬን መቆጣጠር በመቻሌ በጣም ተደሰትኩ! በመሆኑም ከእሱ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመርን።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ