የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp22 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
  • 2 | አትበቀል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 | አትበቀል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦
  • ምን ማለት ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ በቀል ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ሰዎች ሲያናድዱህ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ሕይወት የመረረውና ዓመፀኛ ሰው ነበርኩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • መበቀል ስሕተት ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
wp22 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
የተቆጡ ሁለት ሰዎች በአንድ ዛፍ ሁለት ቅርንጫፎች ላይ ተቀምጠዋል። ሁለቱም የተቀመጡበትን ቅርንጫፍ በመጋዝ እየቆረጡ ነው።

የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ የሚቻለው እንዴት ነው?

2 | አትበቀል

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

‘ለማንም በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ። ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ። ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ይሖዋ” ተብሎ ተጽፏል።’—ሮም 12:17-19

ምን ማለት ነው?

ስንበደል መበሳጨታችን የማይቀር ቢሆንም አምላክ እንድንበቀል አልፈቀደልንም። ከዚህ ይልቅ፣ እሱ በቅርቡ ሁሉንም ነገር ስለሚያስተካክል እስከዚያ ጊዜ ድረስ በትዕግሥት እንድንጠባበቅ አሳስቦናል።—መዝሙር 37:7, 10

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች ሲበቀሉ የጥላቻ ሰንሰለት እየረዘመ ይሄዳል። በመሆኑም አንድ ሰው ቅር ካሰኘህ ወይም ከጎዳህ አጸፋውን አትመልስ። ራስህን ለመቆጣጠርና ሰላማዊ ምላሽ ለመስጠት ጥረት አድርግ። አንዳንድ ጊዜ ጉዳዩን ችላ ብሎ ማለፉ የተሻለ ሊሆን ይችላል። (ምሳሌ 19:11) እርግጥ ነው፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ትመርጥ ይሆናል። ለምሳሌ ወንጀል ተፈጽሞብህ ከሆነ፣ ወንጀሉን ለፖሊስ ወይም ለሌሎች ባለሥልጣናት ሪፖርት ለማድረግ ልትመርጥ ትችላለህ።

የበቀል ሰንሰለት ራስን መልሶ ይጎዳል

ሆኖም ጉዳዩን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት እንደማይቻል ቢሰማህስ? ወይም ደግሞ ጉዳዩን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት የምትችለውን ሁሉ አድርገህም ምንም መፍትሔ ባታገኝስ? የበቀል እርምጃ አትውሰድ። በቀል ችግሩን ማባባሱ አይቀርም። ከዚህ ይልቅ የጥላቻን ሰንሰለት በጥስ። አምላክ ችግሮችን የሚፈታበት መንገድ የተሻለ እንደሆነ መተማመን ትችላለህ። “በእሱ ታመን፤ እሱም ለአንተ ሲል እርምጃ ይወስዳል።”—መዝሙር 37:3-5

እውነተኛ ታሪክ—አድሪያን

የበቀል ስሜትን አሸንፏል

አድሪያን።

አድሪያን በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለ በጥላቻ የተሞላ ተደባዳቢ ነበር፤ ጉዳት ያደረሱበትን ሁሉ ለመበቀል ቆርጦ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “አብዛኛውን ጊዜ እንታኮስ የነበረ ሲሆን ደም በደም ሆኜ መንገድ ላይ ወድቄ ሲያዩኝ የሞትኩ መስሏቸው ትተውኝ የሄዱበት ጊዜ ነበር።”

አድሪያን 16 ዓመት ሲሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመረ። “በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቴ እየገፋሁ ስሄድ የባሕርይ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልገኝ ተገነዘብኩ” ብሏል። አድሪያን ጥላቻውን ማስወገድና ዓመፀኝነቱን መተው ነበረበት። በተለይም ሮም 12:17-19 በቀልን አስመልክቶ የሚናገረው ሐሳብ ልቡን ነካው። እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ እሱ ራሱ በፈለገው መንገድና በወሰነው ጊዜ የፍትሕ መዛባትን እንደሚያስወግድ አምኜ ተቀበልኩ። ቀስ በቀስ የዓመፀኝነት ባሕርዬን አሸነፍኩ።”

አንድ ምሽት የአንድ የወሮበሎች ቡድን አባላት በአድሪያን ላይ ጥቃት አደረሱበት፤ ይህ ቡድን ቀደም ሲል አድሪያን የነበረበት ቡድን ተቀናቃኝ ነበር። የቡድኑ መሪ “ራስህን ተከላከል!” በማለት አድሪያን ላይ ጮኸበት። አድሪያን ‘ሲመቱት መልሶ ለመማታት በጣም እንደተፈተነ’ ሳይሸሽግ ተናግሯል። ሆኖም አጸፋውን ከመመለስ ይልቅ ወደ ይሖዋ አጭር ጸሎት ካቀረበ በኋላ ትቷቸው ሄደ።

አድሪያን እንዲህ ብሏል፦ “በማግስቱ የቡድኑን መሪ ብቻውን አገኘሁት። ሳየው ብድሬን ለመመለስ ብገፋፋም ራሴን ለመቆጣጠር እንዲረዳኝ በድጋሚ ይሖዋን ለመንኩት። የሚገርመው ወጣቱ ቀጥ ብሎ ወደ እኔ መጣና ‘ትናንትና ማታ ለተፈጸመው ነገር ይቅርታ አድርግልኝ። እውነቱን ልንገርህ፣ እኔም እንዳንተ መሆን ብችል ደስ ይለኛል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እፈልጋለሁ’ አለኝ። ቁጣዬን መቆጣጠር በመቻሌ በጣም ተደሰትኩ! በመሆኑም ከእሱ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመርን።”

የአድሪያን ታሪክ በቁጥር 5 2016 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15 ላይ ወጥቷል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ