-
“ትዕግሥትን ልበሱ”መጠበቂያ ግንብ—2001 | ኅዳር 1
-
-
“ፍቅር ይታገሣል”
9. ጳውሎስ “ፍቅር ይታገሣል” በማለት ለክርስቲያኖች የተናገረው ለምን ሊሆን ይችላል?
9 ጳውሎስ “ፍቅር ይታገሣል” ብሎ ሲናገር ፍቅርና ትዕግሥት እርስ በርስ የተሳሰሩ ባሕርያት መሆናቸውን አመልክቷል። (1 ቆሮንቶስ 13:4) አልበርት ባርንዝ የተባሉ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንደተናገሩት ጳውሎስ ይህን ጠበቅ አድርጎ እንዲገልጽ ያስገደደው ምክንያት ቆሮንቶስ በሚገኘው ክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ንትርክና ጭቅጭቅ ነው። (1 ቆሮንቶስ 1:11, 12) ባርንዝ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:- “እዚህ ላይ [ትዕግሥትን ለማመልከት] የገባው ቃል ቸኩሎ እርምጃ ከመውሰድ፣ በስሜት ገንፍሎ ከመናገርና አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ከግልፍተኝነት የሚቃረን ነው። የሚያስጨንቅ ወይም የሚያበሳጭ ሁኔታ በሚያጋጥምበት ጊዜ ለረዥም ጊዜ ችሎ የመኖርን ሐሳብ የሚያስተላልፍ ነው።” ፍቅርና ትዕግሥት የክርስቲያን ጉባኤን ሰላም በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
10. (ሀ) ፍቅር ታጋሽ እንድንሆን የሚረዳን በምን መንገድ ነው? ይህን በተመለከተ ጳውሎስ ምን ምክር ሰጥቷል? (ለ) አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የአምላክን ትዕግሥትና ደግነት በማስመልከት ምን ሐሳብ ሰጥተዋል? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)
10 “ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም [“ደግነትም፣” NW ] ያደርጋል፤ ፍቅር . . . የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም።” ስለዚህ ፍቅር በብዙ መንገዶች ታጋሽ እንድንሆን ይረዳናል።a (1 ቆሮንቶስ 13:4, 5) ፍቅር እርስ በርስ በትዕግሥት ተቻችለን እንድንኖር፣ ሁላችንም ፍጹማን አለመሆናችንንና ስህተት ልንሠራ እንደምንችል እንድናስታውስ ይረዳናል። ለሌሎች አሳቢና ይቅር ባይ እንድንሆን ይረዳናል። ሐዋርያው ጳውሎስ “በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ” በማለት ያበረታታናል።—ኤፌሶን 4:1-3
-
-
“ትዕግሥትን ልበሱ”መጠበቂያ ግንብ—2001 | ኅዳር 1
-
-
a ጎርደን ዲ ፌ የተባሉ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር “ፍቅር ይታገሣል ቸርነትንም ያደርጋል” በማለት ጳውሎስ በሰጠው ሐሳብ ላይ አስተያየታቸውን ሲገልጹ እንዲህ በማለት ጽፈዋል:- “በጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት መሠረት እነዚህ ባሕርያት [ትዕግሥትና ደግነት] አምላክ የሰው ልጆችን የሚመለከትባቸው ሁለት ገጽታዎች ናቸው። (ከሮሜ 2:4 ጋር አወዳድር።) አምላክ ዓመፀኛ በሆኑት ሰዎች ላይ ቁጣውን ከማውረድ በታቀበ ጊዜ በአንድ በኩል ፍቅራዊ ትዕግሥቱ ታይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ምሕረቱ በተገለጠባቸው በሺህ በሚቆጠሩ ቦታዎች ላይ ደግ መሆኑ ታይቷል። በዚህም የተነሳ ጳውሎስ ስለ ፍቅር ማብራሪያ ሲሰጥ ስለ አምላክ ሁለት መግለጫዎችን ሰጥቷል። አንደኛው በክርስቶስ አማካኝነት ትዕግሥት ማሳየቱንና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ መለኮታዊ የፍርድ ቅጣት ሊቀበሉ ለሚገባቸው ሰዎች ደግ መሆኑን አሳይቷል።”
-