የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/95 ገጽ 1
  • ሁልጊዜ ሥራ ይብዛላችሁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሁልጊዜ ሥራ ይብዛላችሁ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሥራ በጣም ይበዛብሃልን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ብዙ ሥራ እያለብህ ደስተኛ ልትሆን ትችላለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ጊዜያችሁ የተያዘው በሞቱ ሥራዎች ነው ወይስ በይሖዋ አገልግሎት?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ለስብከቱ ሥራ እንቅፋት ይሆናልን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 1/95 ገጽ 1

ሁልጊዜ ሥራ ይብዛላችሁ

1 የይሖዋ ሕዝቦች በሥራ የተጠመዱ ሕዝቦች ናቸው። ከቤተሰባችን፣ ከሥራችንና ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ ብዙ ግዴታዎች አሉብን። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁልጊዜ ‘የጌታ ሥራ የበዛልን’ ነን። (1 ቆሮ. 15:58) ለሳምንታዊ የጉባኤ ስብሰባዎች መዘጋጀትና በስብሰባዎቹ ላይ መገኘት አለብን። ትንሽም እንኳ ቢሆን በመስክ አገልግሎት ተሳትፎ ሳናደርግ አንድም ሳምንት እንዳያልፍብን ማበረታቻ ይሰጠናል። ዘወትር ለግልና ለቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በቂ ጊዜ መመደብ አለብን። ሽማግሌዎችና ዲያቆናት ብዙ የጉባኤ ሥራዎች አሏቸው። አንዳንዴ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች እንድንረዳ እንጠየቃለን።

2 አልፎ አልፎ አንዳንዶቻችን በሥራ እንደተዋጥን ይሰማን ይሆናል። ሆኖም ሥራ በጣም የሚበዛባቸው ሰዎች ሚዛናዊ ከሆኑና ትክክለኛ አመለካከት ከያዙ በጣም ደስተኞች ከሆኑት ሰዎች መካከል ሊሆኑ ይችላሉ።— መክ. 3:12, 13

3 ሐዋርያው ጳውሎስ ሥራ ከበዛላቸው ሰዎች አንዱ ነበር። ድንኳን ሰፊ በመሆን ሥጋዊ ሥራ እየሠራ ለራሱ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማግኘት ሲጥር ከሌሎች ሐዋርያት የበለጠ ደክሟል። የመንጋው እረኛ የመሆን ኃላፊነቱን ሳይዘነጋ በአደባባይና ከቤት ወደ ቤት በመመሥከር ደከመኝ ሳይል በወንጌላዊነት አገልግሎ ነበር። (ሥራ 20:20, 21, 31, 34, 35) ፕሮግራሙ በሥራ የተጣበበ ቢሆንም ጳውሎስ ሁልጊዜ በይሖዋ አገልግሎት የበለጠ ለመሥራት ይጓጓ ነበር።— ከሮሜ 1:13–15 ጋር አወዳድር።

4 ጳውሎስ ይሖዋ በሚሰጠው ኃይል በመታመን ሚዛኑንና የልብ ደስታውን ጠብቋል። አገልግሎቱን የሚክስና አስደሳች ሆኖ አግኝቶታል። (ፊልጵ. 4:13 አዓት ) አምላክ ሥራውን እንደማይረሳ ያውቅ ነበር። (ዕብ. 6:10) ሌሎች ይሖዋን እንዲያውቁ በመርዳት ያገኘው ደስታ ኃይሉን አድሶለታል። (1 ተሰ. 2:19, 20) በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ተስፋው እንደሚፈጸም እርግጠኛ መሆኑ በታታሪነቱ እንዲቀጥል ገፋፍቶታል።— ዕብ. 6:11

5 እኛም ጠንክረን በመሥራታችን የሚገኙትን ጥቅሞች ማሰብ አለብን። በሳምንታዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘታችንና መሳተፋችን ሌሎችን የሚያንጽና የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10:24, 25) ምሥራቹን ለማዳረስ የምናደርገው ልባዊ ጥረት የሰዎችን ፍላጎት በኮተኮትንና አዲሶች ከእኛ ጋር በተሰበሰቡ መጠን ለጉባኤው እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል። (ዮሐ. 15:8) እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች መርዳታችን በጉባኤው ውስጥ የቤተሰብ ዓይነት ትስስር ይፈጥራል። (ያዕ. 1:27) ከዚህም በተጨማሪ እንደ ጳውሎስ ጠቃሚ በሆኑ ተግባራት መጠመድ ይሖዋ አምላክን እንደሚያስደስተው በጭራሽ መዘንጋት የለብንም። እሱን ማገልገልን እንደ ትልቅ መብት አድርገን እንመለከተዋለን። ለእኛ ከዚህ የተሻለ ሕይወት የለም!

6 ሥራ የበዛልን መሆናችን የሚያስገኝልን ተጨማሪ ጥቅም አለ። አንድን ጤናማ መንፈሳዊ ልማድ በመከታተል ስንጠመድ ጊዜው ሳናውቀው ይሄዳል። እያንዳንዱ ቀን ማለፉ ወደ አዲሱ ዓለም ይበልጥ እንደሚያቀርበን በመገንዘብ አሁን ያለንን በሥራ የተጠመደና ዓላማ ያለው ሕይወት በደስታ እንቀበላለን። በሥራ ስንጠመድ ከንቱ በሆኑ ዓለማዊ ተግባራት ለመሳተፍ የሚኖረን ጊዜ ጥቂት ስለሚሆን በሥራ መጠመዳችን ጥበብ መሆኑን እንገነዘባለን።— ኤፌ. 5:15, 16

7 ብዙ የሚሠራ የጌታ ሥራ እንዳለ የተረጋገጠ ነው። ይሁን እንጂ አገልግሎታችንን የሚክስና የሚያረካ በሚያደርጉት በይሖዋ አምላክና በኢየሱስ ክርስቶስ መታመናችንን ከቀጠልን ምን ጊዜም ደስታችንን አናጣም።— ማቴ. 11:28–30፤ 1 ዮሐ. 5:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ