የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 4. (ሀ) በክርስቲያናዊው የግንባታ ሥራ ውስጥ ጳውሎስ የነበረው ሚና ምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስም ሆነ አድማጮቹ የጥሩ መሠረትን አስፈላጊነት ያውቁ ነበር ሊባል የሚቻለው ለምንድን ነው?

      4 አንድ ሕንፃ ምንም ሳይሆን ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ ከተፈለገ ጥሩ መሠረት ሊኖረው ይገባል። በመሆኑም ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ [“የሥራ፣” NW] አለቃ መሠረትን መሠረትሁ” ሲል ጽፏል። (1 ቆሮንቶስ 3:​10) ኢየሱስ ክርስቶስም ጠንካራ መሠረት መርጦ ቤቱን ስለገነባ ሰው የሚገልጽ ተመሳሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ይህ ቤት በጠንካራ መሠረት ላይ ስለተገነባ በማዕበል ከመወሰድ ሊተርፍ ችሏል። (ሉቃስ 6:​47–49) ኢየሱስ መሠረት ምን ያህል ወሳኝነት ያለው ነገር መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። ይሖዋ ምድርን በመሠረተ ጊዜ አብሮት ነበር።a (ምሳሌ 8:​29–31) የኢየሱስ አድማጮችም ቢሆኑ ጥሩ መሠረት አስፈላጊ መሆኑን ያውቁ ነበር። በፍልስጤም ምድር አልፎ አልፎ የሚከሰቱትን የጎርፍና የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ለመቋቋም የሚችሉት በጥሩ መሠረት ላይ የተገነቡ ቤቶች ብቻ ነበሩ። ሆኖም ጳውሎስ በአእምሮው ይዞት የነበረው መሠረት ምን ነበር?

  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 7. ጳውሎስ ራሱን ለመግለጽ ከተጠቀመበት ‘ብልሃተኛ የሥራ አለቃ’ ከሚለው አነጋገር ምን ለመማር እንችላለን?

      7 ጳውሎስ የማስተማሩን ሥራ የሚያካሂደው “እንደ ብልሃተኛ የአናጺ [“የሥራ፣” NW] አለቃ” መሆኑን ገልጿል። ይህ አነጋገሩ ራሱን ከመጠን በላይ ከፍ ከፍ ማድረጉን የሚያሳይ አልነበረም። ይሖዋ ሥራውን የማደራጀት ወይም የመምራት አስደናቂ ስጦታ እንደሰጠው መግለጹ ነበር። (1 ቆሮንቶስ 12:​28) እኛ ዛሬ እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ተአምራዊ ስጦታዎች እንደሌሉን የታወቀ ነው። እንዲሁም ልዩ የማስተማር ተሰጥኦ እንደሌለን ይሰማን ይሆናል። ሆኖም ይህ ተሰጥኦ አለን ለማለት ይቻላል። እስቲ አስቡት፤ ይሖዋ እኛን ለመደገፍ ቅዱስ መንፈሱን ይሰጠናል። (ከሉቃስ 12:​11, 12 ጋር አወዳድር።) እንዲሁም የይሖዋ ፍቅርና በቃሉ ውስጥ የሚገኙ መሠረታዊ ትምህርቶች እውቀት አለን። እነዚህ ነገሮች ሌሎችን ለማስተማር ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ድንቅ ስጦታዎች ናቸው። ትክክለኛውን መሠረት ለመጣል በእነዚህ ስጦታዎች ለመጠቀም ቁርጥ ውሳኔያችን ይሁን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ