የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 9. ጳውሎስ ዋነኛ ሥራው መሠረት መጣል ቢሆንም እሱ ያስተማረውን እውነት ለተቀበሉ ሰዎች እንደሚያስብላቸው ያሳየው እንዴት ነበር?

      9 ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፣ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።” (1 ቆሮንቶስ 3:​12, 13) ጳውሎስ ምን ማለቱ ነበር? ይህን የተናገረበትን ምክንያት ተመልከቱ። የጳውሎስ ተቀዳሚ ተግባር መሠረት መጣል ነበር። ባደረጋቸው የሚስዮናዊ ጉዞዎች ከከተማ ወደ ከተማ በመጓዝ ስለ ክርስቶስ ሰምተው ለማያውቁ ብዙ ሰዎች ሰብኳል። (ሮሜ 15:​20) ሰዎች የሚያስተምረውን እውነት ሲቀበሉ ጉባኤዎች ይመሠረቱ ነበር። ጳውሎስ ለእነዚህ የታመኑ ሰዎች ከልብ ያስብ ነበር። (2 ቆሮንቶስ 11:​28, 29) ይሁን እንጂ ሥራው ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወርን ይጠይቅበት ነበር። ስለዚህ በቆሮንቶስ መሠረት በመጣል 18 ወራት ያህል ከቆየ በኋላ በሌሎች ከተሞች ለመስበክ ሄደ። ያም ሆኖ ግን እሱ ጀምሮት የሄደውን የስብከት ሥራ ሌሎች እንዴት እያከናወኑት እንዳሉ ለማወቅ ይፈልግ ነበር።​—⁠ሥራ 18:​8–11፤ 1 ቆሮንቶስ 3:​6

  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 11 እሳት በሚነሣበት ጊዜ እነዚህ ሕንፃዎች ምን ይሆናሉ? መልሱ ለእኛም ሆነ በጳውሎስ ዘመን ለነበሩ ሰዎች ግልጽ ነው። እንዲያውም መሚየስ የተባለው የሮማ ጄኔራል በ146 ከዘአበ ቆሮንቶስን ድል ካደረገ በኋላ ከተማዋን በእሳት አቃጥሏት ነበር። በእንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ የተሠሩ ብዙ ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ የተረጋገጠ ነው። በድንጋይ ተሠርተው በብርና በወርቅ ያጌጡት ጠንካራ ሕንፃዎችስ? እነዚህ ከጥፋት እንደተረፉ ምንም አያጠራጥርም። በቆሮንቶስ የነበሩ የጳውሎስ ተማሪዎች በአካባቢያቸው የነበሩትን ጥንካሬ የሌላቸውን ቤቶች ያወደመውን ጥፋት የተቋቋሙትን ሕንፃዎች በየዕለቱ ሲያልፉ ሲያገድሙ ያዩ እንደነበር አያጠራጥርም። ስለዚህ ጳውሎስ ሊያጎላ የፈለገውን ነጥብ ግሩም በሆነ መንገድ ገልጾታል! በምናስተምርበት ጊዜ ራሳችንን እንደ ግንበኞች አድርገን ልንመለከት ይገባል። በተቻለ መጠን ምርጥና ጠንካራ በሆኑ ቁሳቁሶች ልንጠቀም እንፈልጋለን። በዚህ መንገድ ሥራችን ዘላቂነት ያለው የመሆን አጋጣሚ ሊኖረው ይችላል። ጠንካራ ቁሳቁስ የተባሉት ምንድን ናቸው? እነሱን መጠቀምስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 12. አንዳንድ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ግዴለሽነት የሚታይበት የግንባታ ሥራ በማከናወን ላይ የነበሩት በምን መንገዶች ነው?

      12 በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ጳውሎስ በቆሮንቶስ የሚገኙ አንዳንድ ክርስቲያኖች መናኛ የሆኑ ግንባታዎችን እያካሄዱ እንዳሉ ተሰምቶት ነበር። ችግሩ ምን ነበር? የጥቅሱ ሐሳብ እንደሚያሳየው የጉባኤውን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል ቢሆንም እንኳ የሰዎችን ስብዕና በሚያወድሱ ግለሰቦች ጉባኤው ተከፋፍሎ ነበር። አንዳንዶች “እኔ የጳውሎስ ነኝ” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “እኔስ የአጵሎስ ነኝ” ይሉ ነበር። አንዳንዶች በራሳቸው ጥበብ ከሚገባው በላይ ተመክተው የነበሩ ይመስላል። በውጤቱም የሥጋዊ አስተሳሰብ አየር እንዲሰፍን፣ መንፈሳዊ ጉልምስና እንዳይኖር እንዲሁም “ቅናትና ክርክር” እንዲበራከት ማድረጉ ምንም አያስደንቅም። (1 ቆሮንቶስ 1:​12፤ 3:​1–4, 18) እነዚህ አስተሳሰቦች በጉባኤና በአገልግሎት በሚሰጡ ትምህርቶች ላይ እንደሚንጸባረቁ አያጠራጥርም። በመሆኑም መናኛ በሆኑ ቁሳቁሶች እንደሚሠራ የግንባታ ሥራ ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራቸው ግዴለሽነት የሚታይበት ነበር። ‘እሳቱን’ ሊቋቋም የማይችል ነበር። ጳውሎስ እዚህ ላይ የተናገረው እሳት ምንድን ነው?

      13. በጳውሎስ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው እሳት ምን ያመለክታል? ሁሉም ክርስቲያኖች ንቁ መሆን ያለባቸውስ ለምን ነገር ነው?

      13 ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመን እሳት አለ። ይህም በእምነታችን ላይ የሚደርሱ ፈተናዎች ናቸው። (ዮሐንስ 15:​20፤ ያዕቆብ 1:​2, 3) የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች፣ እውነትን የሚያስተምሩት እያንዳንዱ ሰው ወደፊት እንደሚፈተን ማወቅ አስፈልጓቸው ነበር። እኛም ብንሆን ይህን ማወቅ አለብን። በጥሩ ሁኔታ የማናስተምር ከሆነ ውጤቱ አሳዛኝ ይሆናል። ጳውሎስ እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል:- “ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጐዳበታል፣ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።”c​—⁠1 ቆሮንቶስ 3:​14, 15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ