የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 55
  • ለጉባኤህ ድጋፍ ማድረግ የምትችልባቸው መንገዶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለጉባኤህ ድጋፍ ማድረግ የምትችልባቸው መንገዶች
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • ለምታሳዩት ፍቅር ይሖዋን እናመሰግናለን
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • “ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ”
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራና ስለ ገንዘብ ምን ይላል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የሁሉም ነገር ባለቤት ለሆነው አምላክ ምን ልንሰጠው እንችላለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
ለተጨማሪ መረጃ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 55
ምዕራፍ 55. ወንድሞችና እህቶች በስብሰባ አዳራሻቸው ጥገና ሥራ ሲካፈሉ

ምዕራፍ 55

ለጉባኤህ ድጋፍ ማድረግ የምትችልባቸው መንገዶች

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

በዓለም ዙሪያ በሺዎች በሚቆጠሩ ጉባኤዎች ውስጥ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይሖዋን በደስታ እያገለገሉ ይገኛሉ። የሚሰጣቸውን ትምህርትና መመሪያ በአድናቆት የሚቀበሉ ከመሆኑም ሌላ ጉባኤውን መደገፍ ያስደስታቸዋል። አንተስ እንዲህ ይሰማሃል?

1. ጊዜህንና ጉልበትህን ተጠቅመህ ጉባኤውን መደገፍ የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ሁላችንም ጉባኤውን በተለያዩ መንገዶች መርዳት እንችላለን። ለምሳሌ በጉባኤህ ውስጥ በዕድሜ የገፉ ወይም የታመሙ አሉ? ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ልትረዳቸው ትችላለህ? አሊያም የሚያስፈልጓቸውን ዕቃዎች ገዝቶ እንደማምጣት ወይም የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንደማገዝ ባሉ ሌሎች መንገዶች ድጋፍ ልታደርግላቸው ትችል ይሆን? (ያዕቆብ 1:27⁠ን አንብብ።) የስብሰባ አዳራሻችንን በማጽዳቱ ወይም በመጠገኑ ሥራም እርዳታ ልናበረክት እንችላለን። እነዚህን ነገሮች እንድናደርግ ማንም አያስገድደንም። ለአምላክና ለወንድሞቻችን ያለን ፍቅር ‘በገዛ ፈቃዳችን ራሳችንን እንድናቀርብ’ ያነሳሳናል።—መዝሙር 110:3

የተጠመቁ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤውን መርዳት የሚችሉባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ። ብቃቱን ያሟሉ ወንድሞች የጉባኤ አገልጋይ፣ በኋላም ሽማግሌ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ። ወንድሞችም ሆኑ እህቶች አቅኚ በመሆን የስብከቱን ሥራ በትጋት መደገፍ የሚችሉበት አጋጣሚ ተከፍቶላቸዋል። አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች የአምልኮ ቦታዎችን በመገንባቱ ሥራ ሊያግዙ ወይም እርዳታ ወደሚያስፈልግባቸው ጉባኤዎች ተዛውረው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

2. ገንዘባችንን እና ንብረታችንን ተጠቅመን ጉባኤውን መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?

‘ባሉን ውድ ነገሮች ይሖዋን ማክበር’ እንችላለን። (ምሳሌ 3:9) ገንዘባችንን እና ንብረታችንን ተጠቅመን ጉባኤውንም ሆነ ዓለም አቀፉን የስብከት ሥራ መደገፍ መቻላችን ትልቅ መብት እንደሆነ ይሰማናል። (2 ቆሮንቶስ 9:7⁠ን አንብብ።) የምናደርገው መዋጮ አደጋ የደረሰባቸውን ለመርዳትም ይውላል። ብዙ ወንድሞችና እህቶች በቋሚነት ‘የተወሰነ ገንዘብ በማስቀመጥ’ መዋጮ ያደርጋሉ። (1 ቆሮንቶስ 16:2⁠ን አንብብ።) መዋጮ ለማድረግ በአምልኮ ቦታዎቻችን የሚገኙ የመዋጮ ሣጥኖችን ወይም donate.jw.org​ን መጠቀም እንችላለን። ይሖዋ ገንዘባችንን እና ንብረታችንን ከምንጠቀምበት መንገድ ጋር በተያያዘ ለእሱ ያለንን ፍቅር የምናሳይበት አጋጣሚ ሰጥቶናል።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ለጉባኤው ድጋፍ ማድረግ የምትችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች እንመለከታለን።

3. ገንዘባችንን እና ንብረታችንን ተጠቅመን ጉባኤውን መደገፍ እንችላለን

ይሖዋና ኢየሱስ በደስታ የሚሰጡ ሰዎችን ይወዳሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ አቅሟ የፈቀደውን ያህል መዋጮ ላደረገች አንዲት ድሃ መበለት ያለውን አድናቆት ገልጿል። ሉቃስ 21:1-4⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋን ለማስደሰት ብዙ ገንዘብ መዋጮ ማድረግ አለብን?

  • ይሖዋና ኢየሱስ በራሳችን ተነሳስተን መዋጮ ስናደርግ ምን ይሰማቸዋል?

መዋጯችን ጥቅም ላይ የሚውለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ቪዲዮውን ተመልከቱ። ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ “ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ” (4:47)

  • የምናደርገው መዋጮ በዓለም ዙሪያ ያሉ ጉባኤዎችን ለመደገፍ የሚውለው እንዴት ነው?

በዕድሜ የገፉ አንዲት እህት በመዋጮ ሣጥን ውስጥ መዋጮ ሲያስገቡ

4. በፈቃደኝነት መርዳት እንችላለን

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበሩ የይሖዋ አገልጋዮች የአምልኮ ቦታቸውን ጥሩ አድርገው ለመያዝ የቻሉትን ሁሉ ያደርጉ ነበር። ይህን የሚያደርጉት ገንዘብ በማዋጣት ብቻ አልነበረም። ሁለተኛ ዜና መዋዕል 34:9-11⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • እያንዳንዱ እስራኤላዊ የአምልኮ ቦታውን ወይም የይሖዋን ቤት ጥሩ አድርጎ በመያዝ ረገድ ምን እርዳታ ያበረክት ነበር?

የይሖዋ ምሥክሮች የጥንቶቹን እስራኤላውያን ምሳሌ የሚከተሉት እንዴት እንደሆነ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ (3:31)

‘የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ’ ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ትዕይንት። ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች የስብሰባ አዳራሻቸውን ሲያጸዱ
  • የስብሰባ አዳራሻችንን በንጽሕና መያዛችንና መጠገናችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • አንተ መርዳት የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

የተወሰኑ የይሖዋ ምሥክሮች ፈቃደኛ ሠራተኞች በአንድ የስብሰባ አዳራሽ ግንባታ ሲካፈሉ

5. ወንድሞች በኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለማገልገል ጥረት ማድረግ ይችላሉ

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን ወንዶች አቅማቸው በፈቀደ መጠን ጉባኤውን ለመርዳት ጥረት እንዲያደርጉ ያበረታታል። እንዲህ ማድረግ የሚችሉበትን መንገድ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ። ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ ወንድሞች—ለመልካም ሥራ ተጣጣሩ (5:19)

  • በቪዲዮው ላይ ራያን ጉባኤውን ይበልጥ ለመርዳት ምን አድርጓል?

መጽሐፍ ቅዱስ ወንድሞች የጉባኤ አገልጋይና ሽማግሌ ሆነው ለማገልገል የትኞቹን ብቃቶች ማሟላት እንዳለባቸው ይናገራል። አንደኛ ጢሞቴዎስ 3:1-13⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የጉባኤ አገልጋይና ሽማግሌ ሆነው ማገልገል የሚፈልጉ ወንድሞች የትኞቹን ብቃቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል?

  • ከቤተሰባቸውስ ምን ይጠበቃል?—ቁጥር 4 እና 11⁠ን ተመልከት።

  • ወንድሞች እነዚህን ብቃቶች ለማሟላት ጥረት ሲያደርጉ መላው ጉባኤ የሚጠቀመው እንዴት ነው?

አንድ ወጣት ወንድም በዕድሜ የገፉን አንድ ወንድም ተሽከርካሪ ወንበር እየገፋላቸው አብረው ሲያገለግሉ

አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቅህስ? “የይሖዋ ምሥክሮች ለሥራቸው የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያገኙት እንዴት ነው?”

  • ምን ብለህ ትመልሳለህ?

ማጠቃለያ

ይሖዋ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን እና ገንዘባችንን ተጠቅመን ጉባኤውን ለመርዳት የምናደርገውን ጥረት ከፍ አድርጎ ይመለከታል።

ክለሳ

  • ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን ተጠቅመን ጉባኤውን መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?

  • ገንዘባችንን ጉባኤውን ለመደገፍ ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ጉባኤውን በየትኞቹ መንገዶች መደገፍ ትፈልጋለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

አምላክ በአሁኑ ጊዜ ያሉ አገልጋዮቹ አሥራት እንዲያቀርቡ የማይጠብቅባቸው ለምንድን ነው?

“መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አሥራት ምን ይላል?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ኃላፊነቶችን የሚሰጠው ለተጠመቁ ወንዶች ነው። ሆኖም አንዲት የተጠመቀች እህት እነዚህን ኃላፊነቶች መወጣት ቢኖርባትስ?

“በጉባኤው ውስጥ ስላለው የራስነት ሥርዓት ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘት” (መጠበቂያ ግንብ የካቲት 2021)

ደፋር የይሖዋ ምሥክሮች ለወንድሞቻቸው ጽሑፎች ለማድረስ ሲሉ ምን መሥዋዕትነት ይከፍላሉ?

በኮንጎ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ማሰራጨት (4:25)

ለሥራችን የሚያስፈልገውን ገንዘብ የምናገኝበት መንገድ ከሌሎች ሃይማኖቶች የሚለየው እንዴት ነው?

“የይሖዋ ምሥክሮች ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት እንዴት ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ