የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
    • 4. ጳውሎስ ከምን ችግር ጋር እየታገለ መኖር አስፈልጎት ነበር? ይህ ሁኔታ እኛንስ እንዴት ሊነካን ይችላል?

      4 እስቲ ሐዋርያው ጳውሎስ ምን እንዳጋጠመው ተመልከት። እንዲህ ሲል ጽፏል:- “የሥጋዬ መውጊያ፣ እርሱም የሚያሠቃየኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ። ይህ ነገር ከእኔ እንዲወገድልኝ፣ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንሁት።” ይሖዋ የጳውሎስን ልመና የሰማ ቢሆንም ለችግሩ ተአምራዊ መፍትሔ እንደማይሰጠው ነግሮት ነበር። በመሆኑም ጳውሎስ ያለበትን ‘የሥጋ መውጊያ’ መቋቋም እንዲችል የአምላክ ኃይል እንደሚረዳው መተማመን ነበረበት።b (2 ቆሮንቶስ 12:7-9) አንተም እንደ ጳውሎስ መፍትሔ የሌለው የሚመስል ችግር ይኖርብህ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ‘ይሖዋ እየደረሰብኝ ላለው ችግር ምንም መፍትሔ አለመስጠቱ ያለሁበትን ሁኔታ እንደማያውቅ ወይም ስለ እኔ እንደማያስብ የሚያሳይ ነው?’ የሚል ጥያቄ ታነሳ ይሆናል። መልሱ በጭራሽ አይደለም የሚል ነው! ይሖዋ ለእያንዳንዱ ታማኝ አገልጋዩ ከልብ እንደሚያስብ ኢየሱስ ሐዋርያቱን ከመረጣቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በነገራቸው ነገር ላይ ጎላ አድርጎ ገልጾታል። ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት በዚህ ዘመን ያለነውን እንዴት እንደሚያበረታቱን እንመልከት።

  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
    • b መጽሐፍ ቅዱስ ጳውሎስ የነበረበት ‘የሥጋ መውጊያ’ ምን እንደሆነ በግልጽ አይናገርም። ምናልባትም አጥርቶ የማየት ችግርን የመሰለ አንድ ዓይነት አካላዊ ሕመም ሊሆን ይችላል። አሊያም ደግሞ “የሥጋዬ መውጊያ” ብሎ የጠራቸው፣ ሐሰተኛ ሐዋርያትንና የእርሱን ሐዋርያነትም ሆነ አገልግሎቱን የሚቃወሙ ሌሎች ሰዎችን ሊሆን ይችላል።—2 ቆሮንቶስ 11:6, 13-15፤ ገላትያ 4:15፤ 6:11

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ