-
በሕዝበ ክርስትና ላይ የሚወርደው የይሖዋ መቅሠፍትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
29. ‘እንደ መብራት የሚነደው’ ትልቅ ኮከብ ምሳሌ የሆነው ለማን ነው? ለምንስ?
29 ከዚህ ቀደም ኢየሱስ ለሰባቱ ጉባኤዎች በላከው መልእክት ኮከብ የጉባኤ ሽማግሌዎችን እንደሚያመለክት ተመልክተን ነበር።b (ራእይ 1:20) ቅቡዓን “ኮከቦች” ከሌሎች ቅቡዓን ክርስቲያኖች ጋር ሆነው ሰማያዊ ውርሻ የማግኘታቸው ምሳሌ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ከተቀበሉበት ጊዜ ጀምሮ የሚኖሩት በመንፈሳዊ አነጋገር በሰማይ ነው። (ኤፌሶን 2:6, 7) ይሁን እንጂ ከእነዚህ ኮከብ መሰል ሰዎች መካከል መንጋውን የሚያስቱ መናፍቃንና ከሃዲዎች እንደሚነሱ ሐዋርያው ጳውሎስ አስጠንቅቆ ነበር። (ሥራ 20:29, 30) እንዲህ ያለው የታማኝነት ጉድለት ትልቅ ክህደት ያስከትላል። እነዚህ የወደቁ ሽማግሌዎች እንደ አንድ አካል በመሆን ራሱን በሰው ልጆች መካከል በአምላክ ደረጃ ላይ ያስቀመጠው የዓመፅ ሰው ክፍል ይሆናሉ። (2 ተሰሎንቄ 2:3, 4) የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት በምድር መድረክ ላይ ብቅ ባሉ ጊዜ የጳውሎስ ማስጠንቀቂያ ተፈጽሞአል። ይህ የቀሳውስት ቡድን “እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ” በሚል ምሳሌ መጠራቱ ተገቢ ነው።
-
-
በሕዝበ ክርስትና ላይ የሚወርደው የይሖዋ መቅሠፍትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
31. (ሀ) የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት “ከሰማያዊ” ደረጃቸው የወደቁት መቼ ነበር? (ለ) በቀሳውስቱ ይሰጥ የነበረው ውኃ “እሬት” የሆነው እንዴት ነው? ይህስ በብዙ ሰዎች ላይ ምን ውጤት አስከትሎአል?
31 የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት ክርስትናን በካዱ ጊዜ ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን 2:6, 7 ላይ ከገለጠው ከፍ ያለ ‘ሰማያዊ’ ስፍራ ወደቁ። ጣፋጭ የሆነውን የእውነት ውኃ ከማቅረብ ይልቅ እንደ “እሬት” መራራ የሆኑትን እንደ ሥላሴ፣ የሲኦል እሳት፣ መንጽሔና የአርባ ቀን እድል የመሰሉትን የሐሰት ትምህርቶች መመገብ ጀመሩ። ጥሩ ሥነ ምግባር ያላቸው የአምላክ አገልጋዮች ነን እንደማለታቸው ሕዝብን ከማነጽ ይልቅ ወደ ጦርነት መሩአቸው። ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ? በእነዚህ ውሸቶች የሚያምኑ ሁሉ መንፈሳዊነታቸው ተመረዘ። ሁኔታቸው በኤርምያስ ዘመን ከነበሩት ከሃዲ እስራኤላውያን ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል ነው። ይሖዋ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ብሎ ነበር:- “እነሆ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኩሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ፣ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።”—ኤርምያስ 9:15፤ 23:15
-