-
የብልግና ሥዕሎችን መመልከት ምንም ጉዳት የሌለው የጊዜ ማሳለፊያ ነውን?ንቁ!—2002 | ነሐሴ 8
-
-
ወሲባዊ ቅዠቶች ለአምላክ የምናቀርበውን አምልኮ ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ። ጳውሎስ እንደሚከተለው ሲል የጻፈው በዚህ ምክንያት ነው:- “እንግዲህ . . . ብልቶቻችሁን ግደሉ፣ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ መጐምጀት ነው።”—ቆላስይስ 3:5
እዚህ ላይ ጳውሎስ ፍትወትን ከመጎምጀት ጋር አዛምዶታል።a መጎምጀት ደግሞ አንድን ያልተገኘ ነገር ከመጠን በላይ መፈለግ ማለት ነው። መጎምጀት የጣዖት አምልኮ ነው። ለምን? ምክንያቱም አንድ የሚጎመጅ ሰው የሚጎመጅለትን ነገር ከማንኛውም ነገር፣ ከአምላክም ጭምር አስበልጦ ስለሚመለከት ነው። ወሲባዊ ሥዕሎች አንድ ሰው ላላገኘው ነገር የፍትወት ስሜት እንዲያድርበትና እንዲጎመጅ ያደርጋሉ። አንድ ሃይማኖታዊ ጸሐፊ “የሌላውን ሰው ወሲባዊ ሕይወት ትመኛለህ። . . . ነጋ ጠባ የምታስበው ስለዚያ ነገር ብቻ ይሆናል። . . . የምንጎመጅለትን ነገር እናመልካለን” ብለዋል።
-
-
የብልግና ሥዕሎችን መመልከት ምንም ጉዳት የሌለው የጊዜ ማሳለፊያ ነውን?ንቁ!—2002 | ነሐሴ 8
-
-
a ጳውሎስ እዚህ ላይ የተናገረው ተፈጥሯዊ ስለሆነው ወሲባዊ ፍላጎት ማለትም አንድ ሰው ለትዳር ጓደኛው ስለሚኖረው ተፈጥሯዊ የጾታ ስሜት አይደለም።
-