-
“ከሁሉ የላቀውን” የፍቅርን መንገድ ለመከተል ጥረት ታደርጋለህ?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ሐምሌ 15
-
-
ፍቅርና አንድነት ባለው ቤተሰብ ውስጥ መኖር እንዴት የሚያስደስት ነው! ስቶርጌ አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ቤተሰብ አባላት መካከል ያለውን ተፈጥሯዊ ፍቅር ለማመልከት ይሠራበት የነበረ የግሪክኛ ቃል ነው። ክርስቲያኖች በቤተሰባቸው መካከል ያለው ፍቅር እንዳይጠፋ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ። ጳውሎስ በመጨረሻዎቹ ቀኖች አብዛኞቹ ሰዎች “ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው” እንደሚሆኑ አስቀድሞ ተናግሯል።b—2 ጢሞ. 3:1, 3
በቤተሰብ አባላት መካከል ሊኖር የሚገባው ተፈጥሯዊ ፍቅር በዛሬው ጊዜ እየጠፋ መሆኑ ያሳዝናል። በርካታ ነፍሰ ጡር ሴቶች ውርጃ የሚፈጽሙት ለምንድን ነው? ብዙ ቤተሰቦች በዕድሜ ለገፉ ወላጆቻቸው አሳቢነት የማያሳዩት ለምንድን ነው? የፍቺ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ያለውስ ለምንድን ነው? ሰዎች ተፈጥሯዊ ፍቅር በማጣታቸው እንደሆነ ምንም አያጠያይቅም።
-