-
ወላጆች—“ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ” እንዲያገኙ ልጆቻችሁን እርዷቸውመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ታኅሣሥ
-
-
3. (ሀ) ጢሞቴዎስ ወደ ክርስትና የመጣው እንዴት ነው? ለተማራቸው ትምህርቶችስ ምን ምላሽ ሰጥቷል? (ለ) ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ትምህርት ከመቅሰም ጋር በተያያዘ የትኞቹን ሦስት ነጥቦች ጠቅሷል?
3 ጢሞቴዎስ ስለ ክርስትና የተማረው በ47 ዓ.ም. ሐዋርያው ጳውሎስ ልስጥራን ለመጀመሪያ ጊዜ በጎበኘበት ወቅት ሊሆን ይችላል። በወቅቱ ጢሞቴዎስ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም፤ ያም ቢሆን የተማረውን በተግባር ለማዋል ጥረት አድርጓል። በመሆኑም ከሁለት ዓመት በኋላ የጳውሎስ የጉዞ ጓደኛ መሆን ችሏል። ይህ ከሆነ ከ16 ዓመታት በኋላ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ሲል ጽፎለታል፦ “በተማርካቸውና አምነህ በተቀበልካቸው ነገሮች ጸንተህ ኑር፤ ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች እነማን እንዳስተማሩህ ታውቃለህ፤ እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንድታገኝ የሚያስችሉህን ቅዱሳን መጻሕፍት [የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት] ከጨቅላነትህ ጀምሮ አውቀሃል።” (2 ጢሞ. 3:14, 15) ጳውሎስ (1) ቅዱሳን መጻሕፍትን ስለማወቅ፣ (2) የተማሩትን ነገር አምኖ ስለመቀበል እንዲሁም (3) በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ ስለማግኘት እንደተናገረ ልብ ማለት ያስፈልጋል።
-
-
ወላጆች—“ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ” እንዲያገኙ ልጆቻችሁን እርዷቸውመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ታኅሣሥ
-
-
‘አምኖ መቀበል’
5. (ሀ) ‘አምኖ መቀበል’ ሲባል ምን ማለት ነው? (ለ) ጢሞቴዎስ ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች አምኖ እንደተቀበለ እንዴት እናውቃለን?
5 የቅዱሳን መጻሕፍት እውቀት አስፈላጊ እንደሆነ ጥያቄ የለውም። ይሁንና ለልጆች መንፈሳዊ ነገሮችን ማስተማር ሲባል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሱ ግለሰቦችና ክንውኖች እንዲያውቁ ከመርዳት ያለፈ ነገር ማድረግን ይጨምራል። ጢሞቴዎስ የተማራቸውን ነገሮች ‘አምኖ መቀበል’ እንዳስፈለገው እናስታውስ። ‘አምኖ መቀበል’ የሚለው ሐረግ በግሪክኛ “አንድ ነገር እውነት መሆኑን ተረድቶ ማመንና እርግጠኛ መሆን” የሚል ትርጉም አለው። ጢሞቴዎስ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን ከጨቅላነቱ ጀምሮ ያውቅ ነበር። መሲሑ፣ ኢየሱስ መሆኑን የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ሲያገኝ ደግሞ ይህን አምኖ ተቀበለ። በሌላ አባባል፣ እውቀት በማካበት ብቻ ሳይወሰን የተማረው ነገር ትክክል ስለመሆኑ እርግጠኛ ሆኖ ነበር። እንዲያውም ጢሞቴዎስ ስለ ምሥራቹ የተማረውን ነገር አሳማኝ ሆኖ ስላገኘው፣ ለመጠመቅ ከዚያም ከጳውሎስ ጋር በሚስዮናዊነት ለማገልገል ተነሳስቷል።
6. ልጆቻችሁ ከአምላክ ቃል የተማሩትን ነገር አምነው እንዲቀበሉ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው?
6 እናንተስ ልጆቻችሁ የተማሩትን ነገር ልክ እንደ ጢሞቴዎስ አምነው እንዲቀበሉ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ታጋሽ መሆን ያስፈልጋችኋል። አንድን ነገር ተረድቶ ለማመን ጊዜ ይወስዳል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እናንተ አንድን ነገር አምናችሁ ስለተቀበላችሁት ብቻ ልጆቻችሁም ያምኑበታል ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ልጅ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት አምኖ ለመቀበል ‘የማሰብ ችሎታውን’ መጠቀም አለበት። (ሮም 12:1ን አንብብ።) ልጆች ይህን እንዲያደርጉ በመርዳት ረገድ ወላጆች ቁልፍ ሚና ይኖራችኋል፤ በተለይ ደግሞ ጥያቄዎች በሚጠይቋችሁ ወቅት ይህን ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ታገኛላችሁ። እስቲ አንድ ምሳሌ እንመልከት።
7, 8. (ሀ) አንድ ክርስቲያን አባት ልጁን ሲያስተምር ትዕግሥት የሚያሳየው እንዴት ነው? (ለ) ወላጆች ልጆቻችሁን ስታስተምሩ ትዕግሥት ማሳየት አስፈላጊ እንደሆነ የሚሰማችሁ ለምንድን ነው?
7 የ11 ዓመት ሴት ልጅ ያለችው ቶማስ የተባለ አባት እንዲህ ብሏል፦ “ልጄ አንዳንድ ጊዜ እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን ታነሳለች፦ ‘ይሖዋ በምድር ላይ ሕይወት እንዲኖር ለማድረግ በዝግመተ ለውጥ ተጠቅሞ ቢሆንስ?’ አሊያም ደግሞ ‘ሁኔታዎችን ለማሻሻል ስንል ማኅበረሰቡን በሚጠቅሙ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፎ የማናደርገው፣ ለምሳሌ በምርጫ የማንካፈለው ለምንድን ነው?’ በዚህ ወቅት፣ እኔ ያመንኩበትን ነገር አምና እንድትቀበል ጫና እንዳላደርግባት መጠንቀቅ ያስፈልገኛል። ደግሞም አንድን እውነታ ማወቅ ብቻ አንድን ነገር አምኖ ለመቀበል ያስችላል ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ የተለያዩ ማስረጃዎችን መመርመር ያስፈልጋል።”
8 ቶማስ እንደተገነዘበው ልጆችን ማስተማር ትዕግሥት ይጠይቃል። በመሠረቱ ሁሉም ክርስቲያኖች ትዕግሥት ማሳየት ያስፈልጋቸዋል። (ቆላ. 3:12) ቶማስ፣ ልጁ አንድን ትምህርት አምና እንድትቀበል ለመርዳት በተለያዩ ጊዜያት መወያየት ሊያስፈልግ እንደሚችል ተገንዝቧል። በተጨማሪም ቅዱሳን መጻሕፍትን በመጠቀም ልጁን ሊያስረዳት እንደሚገባ አስተውሏል። ቶማስ እንዲህ ብሏል፦ “እኔና ባለቤቴ በተለይ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ትምህርቶች ጋር በተያያዘ ‘ልጃችን የምትማረውን ነገር በእርግጥ ታምንበታለች? ምክንያታዊ እንደሆነስ ይሰማታል?’ የሚለውን ነገር ማወቅ እንፈልጋለን። ጥያቄዎች ካሏት ደስ ይለናል። እውነቱን ለመናገር፣ ልጃችን ምንም ጥያቄ ሳታነሳ አንድን ሐሳብ ዝም ብላ ከተቀበለች ያሳስበኛል።”
9. የአምላክን ቃል በልጆቻችሁ ውስጥ መቅረጽ የምትችሉት እንዴት ነው?
9 ወላጆች፣ ልጆቻቸውን በትዕግሥት የሚያስተምሯቸው ከሆነ ልጆቹ የእውነት ‘ስፋት፣ ርዝመት፣ ከፍታና ጥልቀት ምን ያህል እንደሆነ’ ቀስ በቀስ ማስተዋል ይጀምራሉ። (ኤፌ. 3:18) ዕድሜያቸውንና የመረዳት ችሎታቸውን ባገናዘበ መልኩ ማስተማር ይኖርባችኋል። ልጆቻችሁ የሚማሩትን ነገር እያመኑበት ሲመጡ፣ አብረዋቸው ለሚማሩ ልጆችም ሆነ ለሌሎች ስለ እምነታቸው ማስረዳት ቀላል ይሆንላቸዋል። (1 ጴጥ. 3:15) ለምሳሌ ልጆቻችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን በተመለከተ ምን ብሎ እንደሚያስተምር ማስረዳት ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ማብራሪያ አሳማኝ እንደሆነ ይሰማቸዋል?a እርግጥ ነው፣ የአምላክን ቃል በልጆቻችሁ ውስጥ መቅረጽ ትዕግሥት ይጠይቃል፤ ይሁንና የምታደርጉት ጥረት ፈጽሞ የሚያስቆጭ አይሆንም።—ዘዳ. 6:6, 7
10. ልጆቻችሁን በማስተማር ረገድ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ምንድን ነው?
10 እርግጥ ነው፣ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት አምኖ በመቀበል ረገድ እናንተ ራሳችሁ ለልጆቻችሁ ምሳሌ መሆናችሁ በጣም አስፈላጊ ነው። የሦስት ሴቶች ልጆች እናት የሆነችው ስቴፋኒ እንዲህ ብላለች፦ “ልጆቼ ገና ሕፃናት ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ራሴን እንዲህ እያልኩ እጠይቅ ነበር፦ ‘ይሖዋ መኖሩን፣ አፍቃሪ መሆኑን እንዲሁም መንገዶቹ ትክክል መሆናቸውን እኔ ራሴ አምኜ የተቀበልኩት ለምን እንደሆነ ለልጆቼ እነግራቸዋለሁ? እኔ ይሖዋን ከልቤ እንደምወደው ልጆቼ በግልፅ መመልከት ይችላሉ?’ እኔ ራሴ አምኜ ያልተቀበልኩትን ነገር ልጆቼ እንዲያምኑበት መጠበቅ አልችልም።”
-