የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በጽናት የተቋቋመውን እሱን በጥሞና አስቡ”
    “ተከታዬ ሁን”
    • ‘የእሱን ፈለግ በጥብቅ ተከተሉ’

      20, 21. ከጽናት ጋር በተያያዘ ይሖዋ ከእኛ የሚጠብቀው ምንድን ነው? ቁርጥ ውሳኔያችንስ ምን መሆን ይኖርበታል?

      20 ኢየሱስ የእሱ ተከታይ መሆን ጽናትን የሚጠይቁ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያስከትል እንደሚችል ያውቃል። (ዮሐንስ 15:​20) የእሱ ምሳሌ ሌሎችን ሊያበረታታ እንደሚችል ስለሚያውቅ መከራን በጽናት በማለፍ ረገድ ፈር ቀዳጅ ሆኗል። (ዮሐንስ 16:​33) እርግጥ ነው፣ ኢየሱስ በጽናት ረገድ ፍጹም ምሳሌ ትቶልናል፤ እኛ ግን ከፍጽምና የራቅን ነን። ታዲያ ይሖዋ ከእኛ የሚጠብቀው ምንድን ነው? ጴጥሮስ “ክርስቶስ . . . የእሱን ፈለግ በጥብቅ እንድትከተሉ አርዓያ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራ ተቀብሏል” ሲል ገልጿል። (1 ጴጥሮስ 2:​21) ኢየሱስ ፈተናዎችን በመወጣት ረገድ ልንኮርጀው የሚገባ “አርዓያ” ትቶልናል።a በጽናት ረገድ ያስመዘገበው ታሪክ ‘ከእሱ ፈለግ’ ወይም ከእግሩ ዱካ ጋር ተመሳስሏል። የኢየሱስን የእግር ዱካ ፍጹም በሆነ መንገድ መከተል ባንችልም “በጥብቅ” ማለትም በቅርበት መከተል ግን እንችላለን።

  • “በጽናት የተቋቋመውን እሱን በጥሞና አስቡ”
    “ተከታዬ ሁን”
    • a “አርዓያ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል በቀጥታ ሲፈታ “ከሥር የተጻፈ” ማለት ነው። ከክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ጸሐፊዎች መካከል ይህን ቃል የተጠቀመው ሐዋርያው ጴጥሮስ ብቻ ነው፤ ቃሉ “አንድ አስተማሪ፣ ተማሪው በተቻለ መጠን እሱ የጻፈለትን አስመስሎ እንዲገለብጥ በተማሪው ደብተር ላይ የሚያሰፍርለትን በትክክል የተጻፉ ፊደላት” ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ