የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 3/15 ገጽ 30
  • በእምነት ጸንታችሁ ኑሩ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በእምነት ጸንታችሁ ኑሩ!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአምላካዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ የተመሠረተ አኗኗር
  • ጽናት በረከቶችን ያመጣል
  • ሴቶች ውበታቸውን መደበቅ ይኖርባቸዋል?
    ንቁ!—2005
  • ውድ የሆነውን እምነታችንን አጽንተን እንያዝ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ለባለ ትዳሮች የሚሆን ጥበብ ያዘለ መመሪያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • መጽሐፍ ቅዱስ መኳኳልንና ጌጣጌጥ ማድረግን በተመለከተ ምን ይላል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 3/15 ገጽ 30

በእምነት ጸንታችሁ ኑሩ!

በአንደኛው ጴጥሮስ ላይ ጎላ ብለው የሚታዩ ነጥቦች

የይሖዋ ምስክሮች የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ወይም የእምነታቸው ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል። በአንዳንድ አገሮች የመንግሥት ስብከት ሥራቸው የሚካሄደው ታላቅ ስደት እያለ ነው። ከአምላክ ጋር ያላቸውን ዝምድና ለማጥፋት ከሚደረጉት ከእነዚህና ከሌሎች መከራዎች በስተ ጀርባ ያለው ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። ይሁን እንጂ ይሖዋ አገልጋዮቹን ስለሚያጸናቸው አዎን በእምነት ስለሚያጠነክራቸው ዲያብሎስ አይሳካለትም።

ሐዋርያው ጴጥሮስ “በተለያየ ፈተና አዝነው” የነበሩትን “ወንድሞቹን እንዲያጸና” መብት አግኝቶ ነበር። (ሉቃስ 22:32፤ 1 ጴጥሮስ 1:6, 7) ይህንንም ያደረገው በ62-64 እዘአ ከባቢሎን በተጻፈው የመጀመሪያ መልእክቱ ነበር። ጴጥሮስ በመልእክቱ ውስጥ አይሁዳዊና አሕዛብ ክርስቲያኖችን የሰይጣንን ጥቃት እንዲቋቋሙ ለመርዳትና “በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ” መክሯቸዋል፤ አጽናንቷቸዋል፤ አበረታቷቸዋልም። (1 ጴጥሮስ 1:1, 2፤ 5:8, 9) አሁን ዲያብሎስ የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑና ጥቃቶቹም ይበልጥ ክፉ ስለሆኑ የይሖዋ ሕዝቦች በመንፈስ መሪነትና አነሳሽነት ጴጥሮስ ከጻፋቸው ቃላት በእርግጥ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

በአምላካዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ የተመሠረተ አኗኗር

ተስፋችን ሰማያዊም ይሁን ምድራዊ የጴጥሮስ መልእክት በፈተናዎች እንድንጸናና በአምላካዊ መንገድ እንድንመላለስ ሊረዳን ይገባል። (1:1 እስከ 2:12) ቅቡዓኑን እምነታቸውን የሚያነጥር ፈተና ሲያጋጥማቸው የሰማያዊው ውርሻ ተስፋ እንዲደሰቱ ምክንያት ይሆናቸዋል። በክርስቶስ መሠረት ላይ የተገነቡ መንፈሳዊ ቤት እንደመሆናቸው መጠን ለአምላክ ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ያቀርባሉ። ለሱ ክብር በሚያመጣ ጠባይም ኑሯቸውን ይመራሉ።

ከሰዎች ሁሉ ጋር ባለን ግንኙነት በአምላካዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመራት አለብን። (2:13 እስከ 3:12) ለሰብአዊ ባለ ሥልጣኖች መገዛት እንዳለብን ጴጥሮስ ገልጿል። የቤት ባሮች ለጌቶቻቸው ሚስቶችም ለባሎቻቸው እንዲገዙ ታዘዋል። የአንዲት ክርስቲያን ሚስት አምላካዊ ጠባይ የማያምን ባሏን ወደ እውነተኛው እምነት ሊስበው ይችላል። አማኝ ባልም ሚስቱን ልክ ለደካማ ዕቃ እንደሚደረገው ሊያከብራት ይገባዋል። ሁሉም ክርስቲያኖች የወዳጅነት ስሜት እንዲያሳዩ፣ የወንድማማች ፍቅር እንዲኖራቸው መልካም የሆነውን እንዲያደርጉና ሰላምን እንዲከተሉ ተመክረዋል።

ጽናት በረከቶችን ያመጣል

የእውነተኛ ክርስቲያኖች መከራን በታማኝነት መቋቋም በረከቶችን ያመጣል። (3:13 እስከ 4:19) ስለ ጽድቅ መከራን የምንቀበል ከሆነ መደሰት አለብን። ከዚህም በላይ ክርስቶስ እኛን ወደ አምላክ ለማቅረብ ሲል በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ እኛም ከእንግዲህ የሥጋችንን ፍላጎት ለማርካት መኖር የለብንም። ፈተናዎችን በታማኝነት ከተቋቋምን በኢየሱስ መገለጥ ጊዜ በታላቅ ደስታ ተካፋዮች እንሆናለን። ስለ ክርስቶስ ስም ወይም ደቀ መዛሙርቱ በመሆናችን ስድብ ቢደርስብንና ብንታገሥ ያ የይሖዋ መንፈስ እንዳለን ስለሚያረጋግጥ ሊያስደስተን ይገባል። እንግዲያው የአምላክን ፈቃድ አድርገን መከራ ብንቀበል ራሳችን በሱ ፊት ብቁ አድርገን እናቅርብ፤ መልካም ማድረጋችንንም እንቀጥል።

ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ኃላፊነቶቻችንን በታማኝነት መወጣትና ከአምላክ ኃያል ክንድ በታች ራሳችንን ማዋረድ ያስፈልገናል። (5:1-14) ሽማግሌዎች የአምላክን መንጋ በበጎ ፈቃድ መጠበቅ አለባቸው፤ ሁላችንም ደግሞ እሱ እንደሚያስብልን በመገንዘብ ጭንቀታችንን በይሖዋ ላይ መጣል አለብን። ወንድሞቻችን ሁሉ በእኛ ላይ የሚያደርስብን መከራ ስለሚደርስባቸው ዲያብሎስን ጸንተን መቃወም አለብን እንጂ ፈጽሞ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። ይሖዋ አምላክ ጽኑ እንደሚያደርገንና በእምነት ጠንካሮች ለመሆን እንደሚያስችለን ሁልጊዜ አስታውሱ።

[በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]

የሴት ማጌጫ፦ ክርስቲያን ሴቶችን ሲመክር ጴጥሮስ እንዲህ አለ፦ “ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።” (1 ጴጥሮስ 3:3, 4) በመጀመሪያው መቶ ዘመን አረማውያን ሴቶች ረጅም ሰዓት ወስዶ ፀጉራቸውን የሚሠራላቸው ወንድ ሲሆን፣ ረጅሙን ፀጉራቸውን በልጦ ለመታየት በሚያስችል ዓይን የሚስብ አሠራር ይሠሩና በሽሩባው ላይ ደግሞ የወርቅ ጌጦች ያንጠለጥሉ ነበር። ብዙዎች ለታይታ ያደርጉት ስለነበር ለክርስቲያኖች የማይገባ ሆኖ ነበር። (1 ጢሞቴዎስ 2:9, 10) ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ጌጥ ስሕተት ነው ማለት አይደለም፣ ምክንያቱም ጴጥሮስ አስፈላጊ የሆነውን “የውጪ ሽልማት (ነጠላ)” ጨምሮ ጠቅሶታል። በጥንት ዘመን የነበሩ የአምላክ አገልጋዮችም ጭምር በጌጣ ጌጦች ተጠቅመዋል። (ዘፍጥረት 24:53፤ ዘፀዓት 3:22፤ 2 ሳሙኤል 1:24፤ ኤርምያስ 2:32፤ ሉቃስ 15:22) ይሁን እንጂ፣ አንዲት ክርስቲያን ብልጭልጭና ስሜትን የሚቀሰቅስ አለባበስንና ጌጥን በጥበብ ትርቃለች እንዲሁም የምትጠቀምባቸው ቅባቶችና ኩሎች የሚስብና ስሜት ቀስቃሽ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባታል። የሐዋርያዊው ምክር ዋናው ቁም ነገር ስለ ውጪያዊ ውበቷ ሳይሆን ስለ ውስጣዊ ውበቷ ጎላ ያለ ትኩረት ትስጥ የሚል ነው። በእውነት ማራኪ ለመሆን ከፈለገች በልከኝነት መልበስና አምላክን እንደምትፈራ የሚያሳይ ሁኔታ መያዝ አለባት።​—ምሳሌ 31:30፤ ሚክያስ 6:8

[ምንጭ]

Israel Department of Antiquities and Museums; Israel Museum/​David Harris

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ