-
የመጨረሻውን ዘመን በተመለከተ የሚነሱ አራት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውመጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 1
-
-
ከታሪክ መማር። ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “[አምላክ] የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ፈሪሃ አምላክ ባልነበራቸው ሰዎች በተሞላው ዓለም ላይ የጥፋት ውኃ ባመጣ ጊዜ የጥንቱን ዓለም ከመቅጣት ወደኋላ አላለም።” (2 ጴጥሮስ 2:5) የሚያሾፉትን ሰዎች በተመለከተ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ “ከጥንት ጀምሮ ሰማያት እንደነበሩ እንዲሁም ደረቁ ምድር በአምላክ ቃል ከውኃ በላይ ጸንቶ እንደቆመና በውኃ መካከል እንደነበረ ለማስተዋል ፈቃደኞች አይደሉም። በዚያ ጊዜ የነበረው ዓለም በውኃ ተጥለቅልቆ ጠፍቷል። ሆኖም በዚያው ቃል አሁን ያሉት ሰማያትም ሆኑ ምድርb ለእሳትና ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ለሚጠፉበት የፍርድ ቀን ተጠብቀው ይቆያሉ።”—2 ጴጥሮስ 3:5-7
-
-
የመጨረሻውን ዘመን በተመለከተ የሚነሱ አራት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውመጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 1
-
-
b ጴጥሮስ እዚህ ላይ ምድር የሚለውን ቃል የተጠቀመበት ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የነበረው ሙሴም በተመሳሳይ ምድር የሚለውን ቃል በምሳሌያዊ መንገድ ተጠቅሞበት ነበር። “ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” ሲል ጽፏል። (ዘፍጥረት 11:1 የ1954 ትርጉም) ግዑዟ ምድር “አንድ ቋንቋ” እንደማትናገር ሁሉ የምትጠፋውም ግዑዟ ምድር አይደለችም። ከዚህ ይልቅ ጴጥሮስ እንደተናገረው ጥፋት የሚደርስባቸው ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
-