የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሄኖክ ፈሪሃ አምላክ በሌለው ዓለም ውስጥ አካሄዱን ከአምላክ ጋር አድርጓል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መስከረም 15
    • አምላካዊ አክብሮት ስለሌላቸው ሰዎች የተነገረ ትንቢት

      አምላካዊ አክብሮት በሌላቸው ሰዎች መካከል ስንኖር ከፍተኛ የአቋም ደረጃዎችን መጠበቅ በጣም አስቸጋሪ ይሆንብናል። ሆኖም ሄኖክ በክፉዎች ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ጠንካራ የፍርድ መልእክት ተናግሯል። በአምላክ መንፈስ ተመርቶ “እነሆ፣ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፣ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል” በማለት ትንቢት ተናግሯል።​—⁠ይሁዳ 14, 15

      ይህ መልእክት ጠማማ አካሄድ ይከተሉ በነበሩ የማያምኑ ሰዎች ላይ ምን ለውጥ ያስከትል ይሆን? እነዚህ ከባድ ቃላት ሄኖክ እንዲጠላ ምናልባትም ማፌዣና ማላገጫ እንዲሆን እንዲሁም እንዲዛትበት አድርገውታል ብሎ ማሰቡ ከእውነታው መራቅ አይሆንም። አንዳንዶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጸጥ ሊያሰኙት ሳይፈልጉ አልቀረም። ይሁን እንጂ ሄኖክ ይህ ሁኔታ አላርበደበደውም። ጻድቁ አቤል ምን እንደደረሰበት ያውቅ የነበረ ሲሆን እሱም የመጣው ቢመጣ አምላክን ከማገልገል ዝንፍ ላለማለት ቆርጦ ነበር።

  • ሄኖክ ፈሪሃ አምላክ በሌለው ዓለም ውስጥ አካሄዱን ከአምላክ ጋር አድርጓል
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መስከረም 15
    • [በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

      መጽሐፍ ቅዱስ ከመጽሐፈ ሔኖክ ይጠቅሳልን?

      መጽሐፈ ሄኖክ የአዋልድ መጽሐፍ ነው። ሄኖክ ጽፎታል የሚባለው ሐሰት ነው። በሁለተኛው ወይም በአንደኛው መቶ ዘመን ከዘአበ አካባቢ እንደተጻፈ የሚገመተው ይህ መጽሐፍ በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ በአጭሩ የተገለጸውን የሄኖክ ታሪክ መሠረት ያደረገ የተጋነነ የአይሁድ አፈ ታሪክ ነው። በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈውን የአምላክ ቃል የሚያፈቅሩ ሰዎች ይህን ማወቃቸው ብቻ መጽሐፉን እንዳይቀበሉት ያደርጋቸዋል።

      በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሄኖክ “እነሆ፣ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፣ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል” በማለት የተናገራቸውን ትንቢታዊ ቃላት የያዘው የይሁዳ መጽሐፍ ብቻ ነው። (ይሁዳ 14, 15) ብዙ ምሁራን ሄኖክ በዘመኑ ስለነበረው አምላካዊ ፍርሃት የሌለው ትውልድ የተነገረው ይህ ትንቢት በቀጥታ የተጠቀሰው ከመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ነው ብለው ይከራከራሉ። ይሁዳ ተአማኒነት የሌለውን የአዋልድ መጽሐፍ እንደ ምንጭነት ይጠቀምበታል ማለት ይቻላል?

      ይሁዳ ሄኖክ የተናገረውን ትንቢት እንዴት እንዳወቀ በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ አልተገለጸም። በሰፊው ተቀባይነት ያገኘና ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የታመነ ታሪክ እንደ ምንጭ ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል። በፈርኦን ፊት ሙሴን የተቃወሙትን ጠንቋዮች ኢያኔስንና ኢያንበሬስን ጳውሎስ በስም ሲጠቅስ ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ነገር ማድረጉ እንደነበረ ግልጽ ነው። የመጽሐፈ ሄኖክ ጸሐፊ እንደዚህ ያለ ጥንታዊ ምንጭ አግኝቷል ከተባለ ይሁዳ ማግኘት አይችልም የምንልበት ምን ምክንያት አለን?a​—⁠ዘጸአት 7:​11, 22፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:​8

      ሄኖክ አምላካዊ አክብሮት የሌላቸውን ሰዎች አስመልክቶ የተናገረውን መልእክት ይሁዳ ከየት እንዳገኘው ማወቁ እምብዛም አስፈላጊ አይደለም። ይሁዳ መልእክቱን በመለኮታዊ መንፈስ አነሳሽነት መጻፉ አስተማማኝነቱን ያረጋግጣል። (2 ጢሞቴዎስ 3:​16) የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር እንዳይጽፍ ጠብቆታል።

      [የግርጌ ማስታወሻ]

      a ደቀ መዝሙሩ እስጢፋኖስም እንዲሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሌላ ቦታ ላይ የማይገኝ ሐሳብ ጠቅሷል። ይህ ሐሳብ ሙሴ በግብፅ አገር ስላገኘው ትምህርት፣ ከግብፅ ሲሸሽ ዕድሜው 40 ዓመት እንደነበረ፣ በምድያም 40 ዓመት እንደቆየና የሙሴን ሕግ በማስተላለፍ ረገድ መልአክ የተጫወተውን ሚና የሚገልጽ ነው።​—⁠ሥራ 7:​22, 23, 30, 38

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ