የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንጸባራቂዋ ከተማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 19. (ሀ) ዮሐንስ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለሰው ልጆች በሙሉ በረከት አስተላላፊ እንደምትሆን የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) “የሕይወት ውኃ ወንዝ” የሚፈሰው መቼ ነው? ይህንንስ እንዴት እናውቃለን?

      19 አንጸባራቂዋ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በምድር ላይ ለሚኖሩት የሰው ልጆች ታላላቅ በረከቶችን ታስተላልፋለች። ለዮሐንስም ቀጥሎ የተነገረው ነገር ይህ ነው:- “በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።” (ራእይ 22:1) ይህ “ወንዝ” የሚፈሰው መቼ ነው? ወንዙ የሚፈስስው “ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን” ስለሆነ የጌታ ቀን ከጀመረበት ከ1914 በኋላ መሆን ይኖርበታል። በሰባተኛው መለከት መነፋት የታወጀውና “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ክርስቶስ ሆነች” የሚለው ማስታወቂያ የተነገረለት ይህ ጊዜ ነበር። (ራእይ 11:15፤ 12:10) በመጨረሻው ዘመን፣ መንፈስና ሙሽራይቱ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች የሕይወትን ውኃ በነፃ እንዲወስዱ ሲጋብዙ ቆይተዋል። የወንዙ ውኃ እስከ ሥርዓቱ መደምደሚያ ድረስ እንደዚህ ላሉት ሰዎች የሚቀርብ ሲሆን ከዚያም በኋላ በአዲሱ ሥርዓት ውስጥ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ‘ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ በምትወርድበት’ ጊዜም መፍሰሱን ይቀጥላል።—ራእይ 21:2

  • አንጸባራቂዋ ከተማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 23. (ሀ) የሕይወት ውኃ ወንዝ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም አደባባዮች መፍሰሱ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) የሕይወት ውኃ ወንዝ በብዛት ሲፈስስ የትኛው ለአብርሃም የተሰጠ መለኮታዊ ተስፋ ይፈጸማል?

      23 በሺው ዓመት ግዛት ዘመን የቤዛው ጥቅሞች ሙሉ በሙሉ ለሰው ልጆች የሚዳረሱት በኢየሱስና በ144,000ዎቹ የበታች ካህናት ክህነት አማካኝነት ነው። ስለዚህ የሕይወት ውኃ ወንዝ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም አደባባይ መካከል መፍሰሱ ተገቢ ነው። አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የተገነባችው እውነተኛዎቹ የአብርሃም ዘሮች በሆኑት በኢየሱስና በመንፈሣዊ እስራኤላውያን አባልነት ነው። (ገላትያ 3:16, 29) ስለዚህ የሕይወት ውኃ ወንዝ በምሳሌያዊቱ ከተማ አደባባይ መካከል ሞልቶ ሲፈስስ “የምድር አሕዛብ ሁሉ” በአብርሃም ዘር አማካኝነት ራሳቸውን የመባረክ አጋጣሚ ያገኛሉ። ይሖዋ ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል።—ዘፍጥረት 22:17, 18

      የሕይወት ዛፎች

      24. ዮሐንስ በሕይወት ውኃ ወንዝ ዳርና ዳር ምን ተመለከተ? እነርሱስ ምን ያመለክታሉ?

      24 በሕዝቅኤል ራእይ ውስጥ ወንዙ ትልቅ ጎርፍ ሆኖ ነበር። ነቢዩም በወንዙ ዳርና ዳር ብዙ ዓይነት ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን ተመልክቶአል። (ሕዝቅኤል 47:12) ዮሐንስስ ምን ተመለከተ? “በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፣ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ [አሕዛብ] መፈወሻ ነበሩ።” (ራእይ 22:2) እነዚህ የሕይወት ዛፎችም ይሖዋ ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች የዘላለም ሕይወት ለመስጠት ያደረገውን ዝግጅት በከፊል ማመልከት ይኖርባቸዋል።

      25. ይሖዋ ለታዛዥ የሰው ልጆች በምድር አቀፉ ገነት ምን የተትረፈረፈ ዝግጅት ያደርግላቸዋል?

      25 ይሖዋ ስጦታዎቹን ለሚቀበሉ ሰዎች በጣም ብዙ የሆነ ዝግጅት አድርጎላቸዋል። ከዚህ ጥም አርኪ ከሆነ ውኃ ለመጠጣት ከመቻላቸውም በላይ ከእነዚህ ሕይወት አዳሽ ከሆኑ ዛፎች የተለያዩ ፍሬዎች እየቀነጠሱ ሊበሉ ይችላሉ። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን በኤደን ገነት ቀርቦላቸው በነበሩት ዝግጅቶች ረክተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ የተሻለ ነበር! (ዘፍጥረት 2:9) አሁን ግን ምድር አቀፍ ገነት ተዘርግቶአል። እንዲያውም ይሖዋ በእነዚህ ምሳሌያዊ ዛፎች ፍሬዎች አማካኝነት ‘አሕዛብ እንዲፈወሱ’ ዝግጅት አድርጎአል።c ዛሬ ከሚሰጡት የዕፅዋትም ሆነ ሌሎች መድኃኒቶች በጣም የበለጠ ፈዋሽነት ያላቸው እነዚህ ምሳሌያዊ ቅጠሎች ያመኑትን የሰው ልጆች ወደ መንፈሣዊና አካላዊ ፍጽምና ያደርሱአቸዋል።

      26. የሕይወት ዛፎች የምን ሌላ ነገር ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ? ለምንስ?

      26 እነዚህ ከወንዙ የሚጠጡት ዛፎች የበጉን ሚስት 144,000 አባሎች ሊጨምሩ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች በምድር ላይ በነበሩበት ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከተደረገላቸው የሕይወት ዝግጅት ጠጥተው ነበር። በመንፈስ የተቀቡት እነዚህ የኢየሱስ ወንድሞች በትንቢት “የጽድቅ ዛፎች” ተብለው መጠራታቸው ትኩረት የሚስብ ነው። (ኢሳይያስ 61:1-3፤ ራእይ 21:6) ቀደም ብሎም ቢሆን ለይሖዋ ውዳሴ ብዙ መንፈሣዊ ፍሬ አፍርተዋል። (ማቴዎስ 21:43) በሺው ዓመት ግዛት ዘመን ደግሞ አሕዛብን ከኃጢአትና ከሞት የሚፈውሰውን የቤዛ ዝግጅት ለሰው ልጆች በማዳረስ ሥራ ይካፈላሉ።—ከ⁠1 ዮሐንስ 1:7 ጋር አወዳድር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ