የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ያለህን አጽንተህ ያዝ”
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 17 በ1918 የዮሐንስ ክፍል አባሎች የሆኑት ቅቡዓን ክርስቲያኖች በፊልድልፍያ እንደ ነበረው ጠንካራ ጉባኤ ከዘመናዊው “የሰይጣን ምኩራብ” የሚደርስባቸውን ተቃውሞ መቋቋም ነበረባቸው። መንፈሳዊ አይሁዳውያን ነን ይሉ የነበሩት የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖታዊ መሪዎች ገዥዎችን በማሳሳትና በመጠምዘዝ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ለማፈን መሣሪያ አድርገው ተጠቀሙባቸው። ይሁን እንጂ እነዚህ ክርስቲያኖች የኢየሱስን የጽናት ቃል ጠብቀው ለመኖር ብርቱ ጥረት አድርገዋል። ስለዚህ በተሰጣቸው መንፈሳዊ እርዳታ ያላቸውን ‘ትንሽ ኃይል’ ጠብቀው ስለተገኙ ተከፍቶ ይጠብቃቸው በነበረው በር ለመግባት ተነሳሱ። ግን ወደዚህ በር የገቡት እንዴት ነው?

      “የተከፈተ በር”

      18. ኢየሱስ በ1919 ምን ዓይነት ሹመት ሰጠ? ተሿሚውስ ታማኝ እንደነበረው የሕዝቅያስ መጋቢ የሆነው እንዴት ነው?

      18 ኢየሱስ በ1919 እነዚህን እውነተኛ የቅቡዓን ክርስቲያኖች ቡድን ‘ታማኝና ልባም ባሪያው’ አድርጎ በመሾም የገባላቸውን ቃል ፈጸመላቸው። (ማቴዎስ 24:45-47) እነዚህ ክርስቲያኖች በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ታማኝ መጋቢ የነበረው ኤልያቄም የተሰጠውን መብት የመሰለ መብት አገኙ።d ይሖዋ ስለ ኤልያቄም ሲናገር እንዲህ አለ:- “የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ። እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም፤ እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።” ኤልያቄም የዳዊት ንጉሣዊ ልጅ ለሆነው ለሕዝቅያስ ከባድ ኃላፊነት ተሸክሞ ነበር። ዛሬም በተመሳሳይ የዮሐንስ ክፍል በሆኑት ቅቡዓን ጫንቃ ላይ “የዳዊት ቤት መከፈቻ” ተጭኖአል። የመሲሐዊውን መንግሥት ፍላጎቶች የማስከበር ኃላፊነት ተጭኖባቸዋል። ይሖዋ አገልጋዮቹን ለዚህ መብታቸው ብቁ ሆነው እንዲገኙ አበርትቶአቸዋል። ያላቸውን ትንሽ ኃይል በጣም ስለጨመረላቸው ከፍተኛ ለሆነው ምድር አቀፍ የምሥክርነት ሥራ አብቅቶአቸዋል።—ኢሳይያስ 22:20, 22፤ 40:29

      19. የዮሐንስ ክፍል ኢየሱስ በ1919 የሰጠውን ኃላፊነት የተወጣው እንዴት ነው? ምንስ ውጤት አስገኘ?

      19 ቅቡዓን ቀሪዎች ከ1919 ጀምሮ የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል የመንግሥቱን ምሥራች የማወጅ ዘመቻ ጀምረዋል። (ማቴዎስ 4:17፤ ሮሜ 10:18) በዚህም ዘመቻቸው ምክንያት ዘመናዊ የሰይጣን ምኩራብ ከሆነችው ከሕዝበ ክርስትና ውስጥ የወጡ አንዳንድ ሰዎች ንስሐ ገብተው በመስገድ ለባሪያው የተሰጠውን ሥልጣን ተቀብለዋል። እነዚህም ሰዎች ቀደም ካሉት የዮሐንስ ክፍል አባሎች ጋር በመተባበር ይሖዋን ማገልገል ጀምረዋል። ይህ ሥራ የኢየሱስ ቅቡዓን ወንድሞች ቁጥር እስከ ሞላበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎአል። ከዚያም በኋላ ‘ከአሕዛብ ሁሉ የተውጣጡ እጅግ ብዙ ሰዎች’ ለቅቡዓን ባሮች መስገድ ጀምረዋል። (ራእይ 7:3, 4, 9) ባሪያውና እነዚህ እጅግ ብዙ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች በመሆን አንድ መንጋ ሆነው ያገለግላሉ።

  • “ያለህን አጽንተህ ያዝ”
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 25. እያንዳንዱ ግለሰብ ክርስቲያን ኢየሱስ ለፊልድልፍያ ጉባኤ የሰጠው ምክር የተመሠረተበትን መሠረታዊ ሥርዓት በሥራ ላይ የሚያውለው እንዴት ነው

      25 ይህ ቃል በፊልድልፍያ የነበሩትን ታማኝ ክርስቲያኖች በጣም ሳያበረታታቸው አልቀረም። በዚህ የጌታ ዘመን ለሚኖሩት የዮሐንስ ክፍል አባሎችም ጠንካራ ትምህርት ይዟል። መሠረታዊ ሥርዓቶቹ ግን ለማንኛውም ግለሰብ ክርስቲያን፣ የተቀባም ሆነ የሌሎች በጎች ክፍል ለሁሉም አስፈላጊ ናቸው። (ዮሐንስ 10:16) ሁላችንም ብንሆን በፊልድልፍያ እንደነበሩት ክርስቲያኖች የመንግሥቱን ፍሬዎች እያፈራን ብንኖር በጣም ጥሩ ነው። ሁላችንም እጅግ ቢያንስ ጥቂት ኃይል አለን። ሁላችንም በይሖዋ አገልግሎት የምንሠራው ሥራ ሊኖረን ይችላል። በዚህ ኃይላችን እንጠቀም። የመንግሥት መብታችንን በማስፋት ረገድ በሚከፈትልን በር ሁሉ ለመግባት ንቁዎች እንሁን። እንዲያውም ይሖዋ እንዲህ ያለውን በር እንዲከፍትልን ልንጸልይ እንችላለን። (ቆላስይስ 4:2, 3) የኢየሱስን የጽናት ምሳሌ ስንከተልና ለስሙ እውነተኞች ሆነን ስንገኝ የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ለጉባኤዎች የሚለውን እንደምንሰማ እናሳያለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ