የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሁለተኛው ወዮታ፣ የፈረሰኞች ሠራዊት
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 6. ዮሐንስ ቀጥሎ የተመለከተውን የፈረሰኞች ጭፍራ የገለጸው እንዴት ነው?

      6 “የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር እልፍ ጊዜ እልፍ፣ እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ። ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው። የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፣ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ። ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ።”—ራእይ 9:16-18

      7, 8. (ሀ) ፈረሰኞቹ የሚነጉዱት በማን አመራር ሥር ሆነው ነው? (ለ) ፈረሰኞቹ ከእነርሱ በፊት ከታዩት አንበጦች ጋር የሚመሳሰሉት በምን መንገዶች ነው?

      7 ይህ የፈረሰኞች ጭፍራ ወደፊት የሚተምመው በአራቱ መላእክት እየተመራ እንደሆነ ግልጽ ነው። በጣም የሚያስፈራ ትዕይንት ነው! ይህን የሚያክል የፈረሰኞች ጭፍራ አንተን ለማሳደድ ቢመጣ ምን እንደሚሰማህ ገምት። ይህን ማየትህ ብቻውን ልብህ በፍርሐት እንዲሸበር ያደርጋል። ይሁን እንጂ ይህ የፈረሰኞች ጭፍራ ከእርሱ በፊት ከታየው የአንበጣ መንጋ ጋር እንደሚመሳሰል አስተውለሃልን? አንበጦቹ ፈረስ ይመስሉ ነበር። በፈረሰኞቹም ጭፍራ ውስጥ ፈረሶች አሉ። ስለዚህ አንበጦቹም ሆኑ የፈረሰኞቹ ጭፍራ ለቲኦክራቲካዊ ውጊያ የተሰለፉ ናቸው። (ምሳሌ 21:31) አንበጦቹ ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር። የፈረሰኞቹ ፈረሶች ደግሞ ራሳቸው የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር። ስለዚህ ሁለቱም መሪያቸው፣ አዛዣቸውና ምሳሌያቸው ከሆነው ከይሁዳ ነገድ አንበሳ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ዝምድና አላቸው ማለት ነው።—ራእይ 5:5፤ ምሳሌ 28:1

      8 አንበጦቹም ሆኑ ፈረሰኞቹ በይሖዋ የፍርድ ሥራ ይካፈላሉ። አንበጦቹ የወጡት በሕዝበ ክርስትና ላይ የሚወርደው ወዮታና ጥፋት ምሳሌ ከሆነው ጢስ ውስጥ ነው። ከፈረሶቹ አፍ ደግሞ እሳት፣ ጢስና ዲን ይወጣል። አንበጦቹ የብረት ጥሩር ነበራቸው። ይህም ልባቸው በማያወላውል የጽድቅ ፍቅር የተጠበቀ መሆኑን ያመለክታል። ፈረሰኞቹ ደግሞ ቀይ፣ ሰማያዊና ቢጫ ቀለም ያለው የደረት ጥሩር ለብሰዋል። እነዚህ ቀለሞች ከፈረሶቹ አፍ እያፈተለከ የሚወጣው ቀሳፊ የፍርድ መልእክት ምሳሌ የሆኑት የእሳት፣ የጢስና የድኝ ቀለሞች ናቸው። (ከ⁠ዘፍጥረት 19:24, 28⁠ና ከ⁠ሉቃስ 17:29, 30 ጋር አወዳድር።) አንበጦቹ ሰዎችን የሚያሰቃዩባቸው ጊንጥ የመሰለ ጅራት ነበራቸው። ፈረሶቹ ደግሞ ሰዎችን የሚገድሉባቸው እንደ እባብ ያሉ ጅራቶች አሉአቸው። አንበጦቹ የጀመሩትን ሥራ ፈረሰኞቹ በበለጠ ኃይልና ጥንካሬ ሰርተው ወደ ፍጻሜው ማድረስ ያለባቸው ይመስላል።

      9. ፈረሰኞቹ የምን ምሳሌ ናቸው?

      9 ታዲያ ይህ የፈረሰኞች ጭፍራ የምን ምሳሌ ነው? በሕዝበ ክርስትና ላይ የወረደውን መለከት መሰል የይሖዋ የፍርድና የመለኮታዊ በቀል መልእክት ማወጅ የጀመሩትና ‘ለመንደፍና ለመጉዳት’ ሥልጣን የተሰጣቸው የተቀቡት የዮሐንስ ክፍል አባሎች ስለሆኑ ‘እንዲገድሉ’ ማለትም ሕዝበ ክርስትናና ቀሳውስትዋ በመንፈሳዊ ረገድ ሙሉ በሙሉ በድን መሆናቸውን፣ ይሖዋ ፈጽሞ የጣላቸውና ‘ለእቶን እሳት’ ማለትም ለዘላለም ጥፋት የተጠበቁ መሆናቸውን እንዲያውጁ ይሖዋ የሚጠቀመው በእነዚሁ ቅቡዓን ክርስቲያኖች መሆን እንደሚኖርበት ለመገመት እንችላለን። በእርግጥም መላው የታላቂቱ ባቢሎን ድርጅት መጥፋት ይኖርበታል። (ራእይ 9:5, 10፤ 18:2, 8፤ ማቴዎስ 13:41-43) ታላቂቱ ባቢሎን ከመጥፋትዋ በፊት ግን የዮሐንስ ክፍል አባሎች የሕዝበ ክርስትናን በድንነት ለማጋለጥ ‘የመንፈስ ሠይፍ በሆነው የአምላክ ቃል’ ይጠቀማሉ። ይህን “በሰዎች ሲሶ” ላይ የሚፈጸመውን ምሳሌያዊ ግድያ የሚመሩት አራቱ መላእክትና ፈረሰኞቹ ናቸው። (ኤፌሶን 6:17፤ ራእይ 9:15, 18) ይህም በጣም ብዙ የሆነው የመንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች ሠራዊት ወደ ጦርነቱ በሚዘምትበት ጊዜ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የበላይ ጥበቃ ሥር ሆኖ ተገቢ የሆነ ቲኦክራቲካዊ አመራርና አደረጃጀት እንደሚያገኝ ያመለክታል።

      ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ

      10. ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ ፈረሰኞች የኖሩት በምን ሁኔታ ነው?

      10 እነዚህ ፈረሰኞች እንዴት ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ ሊሆኑ ቻሉ? አንድ እልፍ ቃል በቃል ከተወሰደ 10,000 ነው። ስለዚህ ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ 200 ሚልዮን ይሆናል ማለት ነው።a እርግጥ በአሁኑ ጊዜ በሚልዮን የሚቆጠሩ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች አሉ። ይሁን እንጂ ቁጥራቸው በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር ለመሆን ገና ብዙ ይቀረዋል። ቢሆንም በ⁠ዘኍልቁ 10:36 ላይ የሚገኘውን የሙሴ ቃል እናስታውሳለን። “አቤቱ፣ [“ይሖዋ፣” NW] ወደ እሥራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ” ብሎ ነበር። (ከ⁠ዘፍጥረት 24:60 ጋር አወዳድር።) ይህን አነጋገር ቃል በቃል ከተረዳን ‘በአሥር ሚልዮን ወደሚቆጠሩት የእስራኤል ሕዝብ ተመለስ’ ማለት ይሆናል። ይሁን እንጂ በሙሴ ዘመን የእሥራኤላውያን ቁጥር ገና ከሁለት እስከ ሶስት ሚልዮን ብቻ ይደርስ ነበር። ታዲያ ሙሴ ምን ማለቱ ነበር? እስራኤላውያን “እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ” ሊቆጠሩ የማይችሉ እንደሚሆኑ አስቦ የተናገረው ቃል እንደሆነ እርግጠኛ ነው። (ዘፍጥረት 22:17፤ 1 ዜና 27:23) ስለዚህ “እልፍ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው የቁጥር ወሰን የሌለውን ብዛት ለማመልከት ነው። በዚህም ምክንያት ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል “ጌታ ሆይ፣ ሊቆጠሩ የማይችሉትን እስራኤላውያን አሳርፍ” ሲል ተርጉሞአል። ይህም በግሪክኛና በዕብራይስጥ መዝገበ ቃላት “እልፍ” ለሚለው ቃል ከተሰጠው ሁለተኛ ትርጉም ጋር ይስማማል። እልፍ “ሊቆጠር የማይችል ብዙ ሕዝብ፣” “እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ” የሚል ትርጉም አለው።—የኒው ቴየር የአዲስ ኪዳን ግሪክኛ ወደ እንግሊዝኛ መፍቻ፣ የጀሰንየስ የብሉይ ኪዳን ዕብራይስጥ ወደ እንግሊዝኛ መፍቻ መዝገበ ቃላት በኢድዋርድ ሮቢንሰን የተተረጎመ።

      11. የዮሐንስ ክፍል በምሳሌያዊ ሁኔታ እንኳን እልፍ እንዲሆን ከተፈለገ ምን ያስፈልጋል?

      11 ይሁን እንጂ በምድር ላይ የቀሩት የዮሐንስ ክፍል አባሎች ከ10,000 ወይም ከአንድ እልፍ ያነሱ ናቸው። ታዲያ ሊቆጠሩ በማይችሉ እጅግ ብዙ የፈረሰኞች ጭፍራ ሊመሰሉ የሚችሉት እንዴት ነው? በምሳሌያዊ አነጋገር እንኳን እልፍ አእላፋት እንዲሆኑ ማጠናከሪያ ኃይል አያስፈልጋቸውምን? አዎ፣ ያስፈልጋቸዋል። ይሖዋም በቸርነቱ ተጨማሪ ኃይል በመስጠት አጠናክሮአቸዋል። እነዚህ ኃይሎች የተገኙት ከየት ነው?

      12, 13. የማጠናከሪያ ኃይል የተገኘበትን ምንጭ የሚያመለክቱን ከ1918 እስከ 1935 የተፈጸሙ የትኞቹ የታሪክ ክንውኖች ናቸው?

      12 የዮሐንስ ክፍል አባሎች ከ1918 እስከ 1922 ባለው ጊዜ በጭንቅ ለተዋጠው የሰው ልጅ “በአሁኑ ጊዜ በሕይወት ከሚኖሩት መካከል ሞትን ፈጽሞ የማያዩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይኖራሉ” የሚል አስደሳች ተስፋ ዘርግተው ነበር። በ1923 ደግሞ በ⁠ማቴዎስ 25:31-34 ላይ የተጠቀሱት በጎች በአምላክ መንግሥት ሥር ሆነው በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት እንደሚወርሱ ታወቀ። በ1927 ተደርጎ በነበረው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ የወጣው የሕዝቦች ነፃነት የተባለው ንዑስ መጽሐፍም ስለ ተመሳሳይ ተስፋ አብራርቶ ነበር። በ1930ዎቹ ዓመታት መጀመሪያ ላይም ቅን የነበረው የኢዮናዳብ ክፍልም ሆነ በሕዝበ ክርስትና ውስጥ በሚታየው አሳዛኝ መንፈሳዊ ሁኔታ ‘የሚያዝኑትና የሚተክዙት ሰዎች’ የምድራዊ ሕይወት ተስፋ ካላቸው ምሳሌያዊ በጎች ጋር አንድ እንደሆኑ ተገለጸ። (ሕዝቅኤል 9:4፤ 2 ነገሥት 10:15, 16) የነሐሴ 15, 1934 መጠበቂያ ግንብ እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ወደ ዘመናዊው “የመማጸኛ ከተማ” በመምራት እንዲህ አለ:- “የኢዮናዳብ ክፍል አባሎች የአምላክን የመለከት ድምፅ ሰምተው ወደ አምላክ ድርጅት በመሸሻቸውና ከአምላክ ሕዝቦች ጋር በመተባበራቸው ማስጠንቀቂያውን የተቀበሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በዚያም ለዘላለም ይኖራሉ።”—ዘኁልቁ 35:6

      13 በ1935 ደግሞ እነዚህ የኢዮናዳብ ክፍል አባሎች በዋሽንግተን፣ ዲ.ሲ፣ ዩ.ኤስ.ኤ በሚደረገው የይሖዋ ምሥክሮች ታላቅ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋበዙ። በዚያም ግንቦት 31 ቀን ዐርብ ዕለት ጄ ኤፍ ራዘርፎርድ “እጅግ ብዙ ሰዎች” የተባለውን ዝነኛ ንግግር አደረገ። በዚህም ንግግሩ በ⁠ራእይ 7:9 ላይ የተገለጹት እጅግ ብዙ ሰዎች በ⁠ማቴዎስ 25:33 ላይ ከተጠቀሱት በጎች ጋር አንድ እንደሆኑና ምድራዊ ተስፋ ያላቸውን ራሳቸውን የወሰኑ ሰዎች እንደሚያመለክቱ በግልጽ አስረዳ። በዚሁ ስብሰባ ላይ ወደፊት በብዛት ለሚፈጸመው ሥራ መንገድ ጠራጊ በመሆን 840 የይሖዋ ምሥክሮች ተጠመቁ። ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ የእጅግ ብዙ ሰዎች አባላት ነበሩ።b

      14. እጅግ ብዙ ሰዎች በፈረሰኞቹ ዘመቻ ይካፈላሉን? በ1963 ምን ዓይነት ውሳኔ ተገልጾአል?

      14 ታዲያ ይህ ታላቅ ሕዝብ በ1922 በጀመረውና በ1927 በቶሮንቶ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ ልዩ ትኩረት በተሰጠው የፈረሰኞች ዘመቻ ተካፍሎአልን? በእርግጥም በአራቱ መላእክት ማለትም በቅቡዓኑ የዮሐንስ ክፍል አባሎች አመራር ሥር ሆኖ በዘመቻው ተካፍሎአል። በ1963 በመላው ዓለም ተደርጎ በነበረው “የዘላለሙ ምሥራች” የወረዳ ስብሰባ ላይ እጅግ ብዙ ሰዎች ከዮሐንስ ክፍል ጋር አንድ ሆነው ቀስቃሽ የሆነ ውሣኔ አስተላልፈዋል። ውሣኔው ዓለም “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የምድር መናወጥ እንደተደቀነበትና የዓለም የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉና ዘመናዊቷ ሃይማኖታዊ ባቢሎን ፈጽመው እንደሚናወጡ” የሚገልጽ ነበር። በተጨማሪም መግለጫው የሚከተለውን አስታውቆ ነበር:- “አለምንም አድልዎና ምርጫ ለሰው ሁሉ የአምላክን መሲሐዊ መንግሥትና፣ ፈጣሪ አምላክን በመንፈስና በእውነት ለማምለክ የሚፈልጉትን ሰዎች ነፃ የሚያወጣውን በአምላክ ጠላቶች ላይ የሚወርድ የቅጣት ፍርድ መናገራችንን እንቀጥላለን።” ይህ ውሣኔ በምድር ዙሪያ በተደረጉ 24 ስብሰባዎች ላይ በተገኙ 454, 977 ተሰብሳቢዎች በጋለ ስሜት ጸደቀ። ከእነዚህ መካከል 95 በመቶ የሚያክሉት የእጅግ ብዙ ሰዎች ክፍል ነበሩ።

      15. (ሀ) በ2005 እጅግ ብዙ ሰዎች ይሖዋ በመስክ የሚጠቀምበት ኃይል ስንት መቶኛ ያክሉ ነበር? (ለ) በ⁠ዮሐንስ 17:20, 21 ላይ የተመዘገበው የኢየሱስ ጸሎት እጅግ ብዙ ሰዎች ከዮሐንስ ክፍል ጋር ያላቸውን አንድነት የገለጸው እንዴት ነው?

      15 እጅግ ብዙ ሰዎች በሕዝበ ክርስትና ላይ መቅሰፍት በማውረድ ሥራ ከዮሐንስ ክፍል ጋር ፍጹም አንድነትና ህብረት እንዳላቸው ማሳወቃቸውን ቀጥለዋል። በ2005 እጅግ ብዙ ሰዎች ይሖዋ በመስኩ ሥራ ከሚገለገልበት ኃይል 99.8 በመቶ የሚሆነውን ክፍል ይዘው ነበር። እነዚህ እጅግ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በ⁠ዮሐንስ 17:20, 21 ላይ የሚከተለውን ጸሎት ካቀረበለት የዮሐንስ ክፍል ጋር ሙሉ ስምምነት አላቸው። “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፣ ከቃላቸው የተነሳ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፣ አንተ፣ አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፣ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።” ቅቡዓን የዮሐንስ ክፍል አባሎች የኢየሱስን አመራር በመከተል በግንባር ቀደምትነት ሲሰለፉ ቀናተኞቹ እጅግ ብዙ ሰዎች ደግሞ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከተደረጉት የፈረሰኛ ዘመቻዎች ሁሉ በአጥፊነት ተወዳዳሪ በሌለው ዘመቻ ተካፍለዋል።c

  • ሁለተኛው ወዮታ፣ የፈረሰኞች ሠራዊት
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • a በሄንሪ ባርክሌይ የተዘጋጀው የራእይ መጽሐፍ ማብራሪያ “ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ” ስለሚለው ቁጥር ሲያትት “ቁጥሩ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ቃል በቃል ፍጻሜ ይኖረዋል ብለን እንዳናስብ ያግደናል። ከዚህ የሚቀጥለው መግለጫም ቢሆን ይህን ይደግፍልናል” ብሎአል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ