-
ዮሐንስ ክብር የተቀዳጀውን ኢየሱስን ተመለከተራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
12. ‘በሁለት በኩል የተሳለው ረዥም ሠይፍ’ ምን ትርጉም አለው?
12 “በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፣ ከአፉም ከሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፣ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ።” (ራእይ 1:16, 17ሀ) የሰባቱን ከዋክብት ትርጉም ኢየሱስ ራሱ ቆየት ብሎ ይገልጻል። አሁን ግን ከአፉ የሚወጣው ምን እንደሆነ አስተውል። “ከሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ።” ይህም ለእርሱ በጣም የሚስማማ መግለጫ ነው። ይሖዋ በጠላቶቹ ላይ የሚያመጣውን የመጨረሻ ፍርድ እንዲያስታውቅ ሥልጣን የተሰጠው ኢየሱስ ነው። ከአፉ የሚወጡት ወሳኝ ቃላት ክፉዎችን በሙሉ እንዲደመሰሱ ያደርጋሉ።—ራእይ 19:13, 15
13. (ሀ) ብሩሕ የሆነው የኢየሱስ አንፀባራቂ ፊት ምን ነገር ያስታውሰናል? (ለ) ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ከሰጠው መግለጫ ምን አጠቃላይ ግንዛቤ እናገኛለን?
13 የኢየሱስ ፊት ብሩሕ ሆኖ ማንጸባረቁ ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ከይሖዋ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ፊቱ ማብራት የጀመረበትን ጊዜ ያስታውሰናል። (ዘጸአት 34:29, 30) በተጨማሪም ኢየሱስ የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ በሦስት ሐዋርያቱ ፊት በተለወጠ ጊዜ ‘ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ፣ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ’ ሆኖ ነበር። (ማቴዎስ 17:2) አሁን ደግሞ ኢየሱስ በጌታ ቀን የሚኖረውን ሁኔታ በሚያሳየው ራእያዊ ትዕይንት ላይ ፊቱ በይሖዋ ፊት የቆየ ማንኛውም ፍጡር የሚኖረውን አንፀባራቂ ግርማ ያሳያል። (2 ቆሮንቶስ 3:18) እንዲያውም ዮሐንስ የተመለከተው ራእይ ታላቅ የግርማ ጨረር ነበር ለማለት ይቻላል። እንደ በረዶ ከነጣው ፀጉር፣ እንደ እሳት ፍም ከሚያበራው ዓይንና ብሩሕ ከሆነው ፊት ጀምሮ እሳት እስከሚመስለው እግር ድረስ የታየው ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ “ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን” የሚኖረውን ኢየሱስን የሚያመለክት ከፍተኛ ራእይ ነበር። (1 ጢሞቴዎስ 6:16) መላው ትዕይንት በጣም እውን ሆኖ የሚታይ ነበር። ባየው ነገር ሁሉ በጣም የተደነቀውና የደነገጠው ዮሐንስ ምን አደረገ? ሐዋርያው “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ” በማለት ይነግረናል።—ራእይ 1:17
-
-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
2. (ሀ) ኢየሱስ ራሱን የገለጸው እንዴት ባለ የማዕረግ ስም ነው? (ለ) ይሖዋ “የመጀመሪያና የመጨረሻ እኔ ነኝ” ሲል ምን ማለቱ ነው? (ሐ) “የመጀመሪያውና የመጨረሻው” የሚለው የኢየሱስ የማዕረግ ስም የሚያመለክተው ምንን ነው?
2 ይሁን እንጂ አድናቆታችን ከልክ ወዳለፈ ፍርሐትና መርበትበት መድረስ አይኖርበትም። ሐዋርያው ቀጥሎ እንደሚነግረን ኢየሱስ ዮሐንስን አበረታቶት ነበር። “ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፣ እንዲህም አለኝ፣ ‘አትፍራ፣ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ።’” (ራእይ 1:17ለ, 18ሀ) ይሖዋ በኢሳይያስ 44:6 ላይ የራሱን ደረጃ ሲገልጽ “እኔ ፊተኛ ነኝ፣ እኔም ኋለኛ ነኝ፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም” ብሎ ነበር።a ኢየሱስ ራሱን “ፊተኛውና መጨረሻው” ሲል ራሱን ከታላቁ ፈጣሪ ከይሖዋ ጋር ማስተካከሉ አልነበረም። አምላክ የሰጠውን የማዕረግ ስም መጠቀሙ ነበር። ይሖዋ በኢሳይያስ ላይ የተናገረው ቃል በእውነተኛ አምላክነት ደረጃው ረገድ ያለውን ብቸኛና ልዩ ቦታ የሚያመለክት ነበር። ይሖዋ የዘላለም አምላክ ሲሆን ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም። (1 ጢሞቴዎስ 1:17) ኢየሱስ ግን በራእይ ላይ ያለውን ቃል የተናገረው የተሰጠውን የማዕረግ ስም ለመጥቀስና ስለተሰጠው ልዩ ዓይነት ትንሣኤ ለማመልከት ነበር።
3. (ሀ) ኢየሱስ “የመጀመሪያውና የመጨረሻው” የሆነው በምን መንገድ ነው? (ለ) ኢየሱስ “የሞትና የሲኦል ቁልፍ” መያዙ ምን ትርጉም አለው?
3 በእውነትም ወደማይሞት ሰማያዊ ሕይወት ለመነሳት “የመጀመሪያው” ሰው ኢየሱስ ነበር። (ቆላስይስ 1:18) ከዚህም በላይ ይሖዋ በግል ያስነሳው ኢየሱስን ብቻ ስለሆነ እርሱ “የመጨረሻው” ነው። በዚህም መንገድ “ሕያው” ሆኖአል። “ከዘላለም እስከ ዘላለምም ሕያው” ነው። ያለመሞት ባሕርይ ተሰጥቶታል። በዚህም ባሕርዩ “ሕያው አምላክ” ከተባለው ከአባቱ ጋር ይመሳሰላል። (ራእይ 7:2፤ መዝሙር 42:2) ለቀሩት የሰው ዘሮች ግን ኢየሱስ “ትንሣኤም ሕይወትም” ነው። (ዮሐንስ 11:25) ከዚህም ጋር በመስማማት ለዮሐንስ እንዲህ ብሎታል:- “ሞቼም ነበርሁ እነሆም፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ። የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።” (ራእይ 1:18ለ) ይሖዋ ሙታንን የማስነሳት ሥልጣን ሰጥቶታል። ኢየሱስም በሞትና በሲኦል (በመቃብር) የታሰሩትን ከፍቶ የሚለቅበት ቁልፍ እንዳለው የተናገረው በዚህ ምክንያት ነው።—ከማቴዎስ 16:18 ጋር አወዳድር።
-