-
ከሁለት አስፈሪ አራዊት ጋር መታገልራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
25. (ሀ) ዮሐንስ ወደ ዓለም መድረክ ስለ ወጣ ሌላ ምሳሌያዊ አውሬ የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) የአዲሱ አውሬ ሁለት ቀንዶችና አውሬው ከምድር መውጣቱ ምን ያመለክታሉ?
25 አሁን ደግሞ አንድ ሌላ አውሬ በዓለም መድረክ ላይ ብቅ አለ። ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይነግረናል:- “ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፣ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር። በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቁስል ተፈወሰለት ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል። እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰው ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል።” (ራእይ 13:11-13) ይህ አውሬ ሁለት ቀንዶች አሉት። ይህም የሁለት ፖለቲካዊ ኃይላት ጥምር መሆኑን ያመለክታል። በተጨማሪም ይህ አውሬ የወጣው ከባሕር ሳይሆን ከምድር እንደሆነ ተገልጾአል። ስለዚህ ቀድሞውኑ ተቋቁሞ ከነበረው ከሰይጣን ምድራዊ ሥርዓት ውስጥ የወጣ ነው። ከዚህ በፊት የነበረና በጌታ ቀን ደግሞ ግንባር ቀደም የሥራ ድርሻ የሚኖረው የዓለም ኃያል መንግሥት መሆን ይኖርበታል።
26. (ሀ) ባለ ሁለት ቀንዱ አውሬ ምንድን ነው? ከመጀመሪያውስ አውሬ ጋር ምን ዝምድና አላቸው? (ለ) የአውሬው ሁለት ቀንዶች የበግ ቀንድ የሚመስሉ የሆኑት በምን መንገድ ነው? ሲናገርስ “እንደ ዘንዶ” የሆነው እንዴት ነው? (ሐ) ብሔራዊ ስሜት ያላቸው ሰዎች የሚያመልኩት ማንን ነው? ብሔራዊ ስሜትስ በምን ተመስሎአል? (የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።)
26 ታዲያ የትኛው የዓለም ኃያል መንግሥት ሊሆን ይችላል? የአንግሎ አሜሪካን የዓለም ኃያል መንግሥት ነው። በሌላ አነጋገር የመጀመሪያው አውሬ ሰባተኛ ራስ ሲሆን እዚህ ላይ ልዩ ሚና ይኖረዋል። በራእዩ ውስጥ የተለየ አውሬ ሆኖ ተነጥሎ መታየቱ በዓለም መድረክ በተናጠል የሚፈጽማቸውን ነገሮች በግልጽ እንድንመለከት ያስችለናል። ይህ ምሳሌያዊ ባለ ሁለት ቀንድ አውሬ አብረው ከሚኖሩ፣ ነጻና የፖለቲካ ኃይላቸውን ለማስተባበር ፈቃደኛ በሆኑ ሁለት መንግሥታት የተቋቋመ ነው። ሁለቱ ቀንዶቹ “የበግ ቀንዶች የሚመስሉ” መሆናቸው ሰዎችን የማይጋፋና ልዝብ፣ ዓለም በሙሉ በምሳሌነት የሚመለከተው የሰለጠነ መንግሥት እንደሆነ አድርጐ ራሱን ማቅረቡን ያመለክታል። ይሁን እንጂ የአገዛዝ ሥርዓቱ ተቀባይነት ባላገኘባቸው ሥፍራዎች በኃይል፣ በዛቻና በተለያየ ተጽእኖ ስለሚጠቀም “እንደ ዘንዶ” ይናገራል። ሰዎች ሁሉ በአምላክ በግ ለሚተዳደረው የአምላክ መንግሥት እንዲገዙ አይገፋፋም። እንዲያውም የታላቁን ዘንዶ የሰይጣንን ዓላማና ፍላጎት ያስፈጽማል። ብሔራዊ ጥላቻንና መከፋፈልን ያስፋፋል። ይህ ሁሉ ድርጊት የመጀመሪያውን አውሬ አምልኮ የሚያስፋፋ ነው።c
-
-
ከሁለት አስፈሪ አራዊት ጋር መታገልራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
c የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ብሔራዊ ስሜት ከሃይማኖት ተለይቶ የሚታይ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ስለዚህ ብሔራዊ ስሜት ያላቸው ሰዎች በሚኖሩበት አገር የሚወከለውን የአውሬ ክፍል ያመልካሉ ማለት ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ስላለው ብሔራዊ ስሜት እንዲህ እናነባለን:- “ከሃይማኖት ተለይቶ የማይታየው ብሔራዊ ስሜት ከሌሎቹ ታላላቅ ሃይማኖቶች ጋር የሚመሳሰልባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉት። . . . ዘመናዊው የብሔራዊ ስሜት ሃይማኖተኛ በብሔራዊ አምላኩ ላይ እንደሚተማመን ይሰማዋል። የዚህ አምላክ ኃያል እርዳታ እንደሚያስፈልገው ይገነዘባል። ከዚህ አምላክ ፍጹምነትና ደስታ እንደሚያገኝ ያስባል። በሃይማኖታዊ ስሜት ሙሉ በሙሉ ይገዛለታል። . . . ብሔሩ ዘላለማዊ እንደሆነና የታማኝ ልጆቹም ሞት ለማይሞተው ብሔራዊ ዝናና ክብር አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያምናል።”—ካርልተን ጄ ኤፍ ሄይስ ዋት አሜሪካንስ ቢሊቭ ኤንድ ሀው ዜይ ዎርሽፕ በተባለው የጄ ፖል ዊልያምስ መጽሐፍ በገጽ 359 ላይ እንደጠቀሱት።
-